1 0
Read Time:2 Minute, 29 Second

Sep. 27, 2022
መስከረም 17፣ 2015 ዓ/ም
የአቋም መግለጫ
በመስከረም 15 2015 ዓ.ም የጋሻ አማራ ሕዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ በበይነ መረብ ከአባላት፣
ደጋፊዎችና ባጠቃላይ ከአማራ ተወላጆች ጋር ባደረገው አስቸኳይ ህዝባዊ ውይይትን መሰረት አድርጎ የወጣ
የአቋም መግለጫ።

አማራን በሚኖርበት አፅመርስቱ ሁሉ በወለጋና በመተከል በመጨፍጨፍ፣ እንዲሁም ከጭፍጨፋ የተረፈውን አፈናቅሎ ለርሃብና
በሽታ በማጋለጥ እንዲያልቁ በማድረግ፤ አካባቢውን የጦር አውድማ አድርጎ በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ የተፈጥሮ ሀብቱን፣ የግልና
የማህበራዊ ተቋማት ንብረቱን፣ የእምነትና የታሪክ ቅርሱን በማውደምና በመዝረፍ አማራን አንበርክኮና አጥፍቶ ታላቋን ትግራይና
ኦሮሚያ የሚባሉ ክፋይ አገሮችን በአማራና በሌሎች ነባር ህዝቦች አፅመርስት ላይ ለማዋለድ፣ በብአዴን መሪነት ለሚፈጸሙት
ሁሉን አቀፍ የአማራን ዘር የማጥፋት ወንጀሎች በመከላከልና የአማራን ህልውና በማስጠበቅ ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታድግ
ቆርጠው የተነሱ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆችን መረሸን፣ ማሰርና ማሳደድ ከምንጊዜውም በላይ ተጠናክሮ በመቀጠሉ፤ ዛሬ ላይ
የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) መስራችና መሪ፣ የስልሳ ሁለት ሚሊዮን አማራ ወኪልና ድምፅ የሆነውን ፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴን
ድሮን፣ ሄሊኮፕተርና ታንክ ከልዩ ኮማንዶ ጋር በጎጃም አርሶ አደር ላይ በማዝመት በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ በንብረት ላይ
ከፍተኛ ውድመት ሲያደርስ፤ በጀግናው የአማራ ህዝብ ፋኖዎች ተመክቶ ሲመለስ የአማራን እምነት ባህልና እሴት በመጠቀም
በተላላኪዎች የማታለል ሴራ በእንነጋገር ሰበብ ታስሯል።
ስለሆነም የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ እስር የመላው ስልሳ ሁለት ሚሊዮን አማራ መታሰር መሆኑን የአማራ ህዝብና ደጋፊዎቹ
በሙሉ በአሀገር ውስጥና በውጭ አገራት ማስጠንቀቂያ አዘል ድምፃቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
ጋሻ የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ በተላላኪዎች የማታለያ ክህደት የእስር ወንጀሉ
በተፈፀመበት ወቅት የወጣነውን መግለጫ ተከትሎ በውጭ አገራት ለሚኖረው አማራና ሰላምና ደህንነት ወዳጅ ለሆነው
ኢትዮጵያዊ ጥሪ በማድረግ የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበርና ኢትዮጵያን ከአፍራሾቿ ብአዴን፣ ኦነግ/ብልፅግናና ትህነግ
የተቀናጀና የተወሳሰበ ሴራ ለመታደግና ግባችንን ለማሳካት በሚያስችሉ ህዝባዊ ትግሎች ላይ በመምከር የትግላችን ፈር ቀዳጅ
የሆኑትን የትግል ምራፎች እንደሚከተለው በማስቀመጥ ለተግባራዊነታቸው የሁሉንም አማራና አገረ ወዳድ ኢትዮጵያውያንን
እርብርብ እንጠይቃለን።

 1. የፋኖ አርበኛ ዘመነ ካሴ መታሰርን ተከትሎ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ሥራ አስፈጻሚዎች መስከረም 15፣ 2015
  ዓ/ም የወጡትን መግለጫ ሙሉ በሙሉ በመቀበል፣ ለተፈጻሚነቱ በጽናት ለመስራት እና በተከታታይነት ለሚታቀዱ
  የትግል እንቅስቃሲዎች ሁሉ ከአማራ ህዝባዊ ኃይል ሥራ አስፈጽሚዎች ጋር በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት
  በቁርጠኝነት መቆም።
 2. የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የትግል መሪያችን ፋኖ ዘመነ ካሴን፣ በተለያየ እስርቤት የሚገኙ ፋኖዎችን፣ የጎበዝ
  አለቆችን፣ ጋዜጠኞችንና የሰባዊ መብት ተሟጋቾችን መግደል፣ ማሰርና ማሳደድ፤ የአማራን ጅምላ ጭፍጨፋ፣
  ማፈናቀል፣ ማስራብና በበሽታ እንዲያልቁ ማድረግን በዘላቂነት ማስቆም የሚችለው የአማራው ተናቦ ተባብሮ
  የሚያደርገው ህልውና የማስከበር ትግል ዋንኛው ቢሆንም፤ የሰብአዊ መብት ተማጋቾች ወይም በሰብአዊ አያያዝ ላይ
  የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰላማዊ እስረኞቹን እንዲጎበኙ እና በብልጽግናው የአብይ አገዛዝ ላይ ጫና በማሳደር
  እስረኞቹ እንዲፈቱ ይረዱ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።
 3. ሁሉን አቀፍ የህዝባዊ እንቢተኝነትን ትግል በሁሉም መስክ ማቀጣጠል።
 4. በወለጋ በመተክልና በሌሎች አካባቢዎች የሚደረግን የአማራን ጅምላ ጭፍጨፋና ማፈናቀል በልጆቹ ቆራጥ ትግል
  ለማስቆም እና ለአለም አቀፉ ህብረተሰብ በሚቻለው ሁሉ ማጋለጥና ለተጨፍጫፊና ተፈናቃይ ወገኖች መድረስ።
 1. በውጭ አህጉራትና አገራት የሚገኙ በግልፅና በድብቅ የሚንቀሳቀሱ የብአዴን ቀጥታና ስልታዊ ደጋፊ አደረጃጀቶችን፣
  ማህበረትን፣ ቡድኖችን፣ ዩቲዩበሮችንና ግለሰቦችን በስም በማጋለጥ ፀረ አማራ ተግባራቸውን ለህዝብ በማሳወቅ ከእኩይ
  ተልኮ እንዲታቀቡ ማድረግ።
 2. በቅርብ ቀን የተጀመረውን በሳምንት አራት ቀን በ15360 ኪሎ ኸርዝ አጭር ሞገድ (በ19 ሜትር ባንድ) የሚተላለፈውን
  የጋሻ አማራ ድምፅ ራዲዮ ብቃትና ጥራትን በማሳደግ ተደራሽንትና ወደ ሳተላይት ቴሌቪዥን ለማሳድግ በሁሉም
  አህጉራትና አገራት ድጋፍ ሰጭ አደረጃጀቶችን ለተቋምነት ማብቃት።
 3. ከውጭ አገራት ወደ ኢትዮጵያ በግልና በተራ ቁጥር 4 ላይ በተዘረዘሩ የፀረ አማራውና ፀረ ኢትዮጵያው አገዛዝ
  የሚላክን ገንዘብ በማቆም ማንበርከክ።
  ለስር ነቀል ለውጥ ስርነቀል አስተሳሰብ!!!
  አማራው ለዘለቄታው ያሸንፋል!!!

መስከረም 17 ቀን 2015 ዓ/ም
ጋሻ አማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator