0 0
Read Time:1 Minute, 44 Second

ቁጥር APF-/D.N 52/15
ቀን 15/01/2015 ዓ.ም

በግልጽ እንደሚታወቀው የአማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) ፕሬዘዳንት የሆኑት መሪያችን አርበኛ ታጋይ ፋኖ ዘመነ ካሤ በድርድር (በእርቅ) ሰበብ ወደ ክልላችን መናገሻ ከተማ እንዲመጣ ከተደረገ በሗላ መንግስታዊ ክህደት ተፈጽሞበት በእስር ላይ መሆኑ ይታወቃል ። ይሁንም እንጅ መንግስት የተቋረጠውን የድርድር ሒደት በማስቀጠል ያለ ጥፋቱ የታሠረው መሪያችንን እንዲፈታ ግልጽ አቅጣጫ አስቀምጠን ለመስራት የስራ አስፈጻሚው ጥያቄ የመላው የኣማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ነጻነት ናፋቂ የሆነው የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጥያቄ መሆኑን ለማሣየት እና የፍትህ እና የነጻነት ጥያቄያችን እውነትን ያነገበ መሆኑን ኣለም ተገንዝቦ ከጎናችን እንዲቆም ለማድረግ በእቅድ የሚመራ ስራ መስራት እንዳለብን ታምኗል ። ስለሆነም ስራ አስፈጻሚው በኣስቸኳይ ተወያይቶ በእቅድ የሚመራ የትግል ተግባሮችን በጋራ እስኪገለጽ ድረስ ፦

1ኛ. በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች የምትገኙ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራሮቻችን በተናጠል ከማንኛውም የህዝባዊ ሀይሉ ስራ አስፈጻሚዎች በግል በጎንዮሽ የሚመጣን ትዕዛዝ መቀበል የተከለከለ ስለሆነ ይህን ተግባራዊ ታደርጉልን ዘንድ እንጠይቃለን ።
2ኛ. የኣማራ ህዝባዊ ሀይል (ፋኖ) ስራ አስፈጻሚ አመራሮች በየግል የማህበራዊ ድረ ገጾቻቸው የሚያስተላልፉት መልዕክት የራሳቸው ሀሣብ እንጅ የተቋሙ አቋም እንዳልሆነ በማወቅ አባላችንና ደጋፊዎቻችን እንዲረዱት እንጠይቃለን ።
3ኛ. መላው የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ አመራሮች፣አባላቶች እና ደጋፊዎች በሙሉ በስራ አስፈጻሚ አመራሮች በጋራ ከሚሠጡ የትግል አቅጣጫዎችን በመቀበል እንዲፈጽሙ ነገር ግን ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ባለቤታቸው ሳይታወቅ የሚደረጉ የትግል ጥሪዎችን ባለመሣተፍ ትተባበሩን ዘንድ እንጠይቃለን ።
4ኛ. ማህበራዊ ሚዲያ ኣንቂዎች፣ጋዜጠኞች፣ጦማሪዎች ወ.ዘ.ተ ስራ አስፈጻሚው ከሚሠጣቸው የትግል አቅጣጫዎች ውጭ መነሻቸው ተቋማችን ለማፍረስ ከሚተጉ በማር የተለወሱ መርዞች የሚመጣ ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ግን ጠቃሚ የሚመሥሉ የትግል ጥሪዎችን ባለማስተጋባትና እናንተም እንዲህ ያሉ ተግባራት የሚፈጽሙ አካላትን በመከላከል የድርሻችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን ።
5ኛ. ኣስቀድሞ ተቋማችን ይጠቀምበት በነበረው የተቋሙ ድህረ-ገጽ ስራ አስፈጻሚው በግልጽ እስኪያሳውቅ ድረስ ማናቸውንም መልዕክት ማስተላለፍ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን ።
6ኛ. መሪያችን እና የድርጅታችን ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፋኖ ዘመነ ካሴን ለመጠየቅ ሁሉም በየወረዳው መዋቅር መሠረት እየተነጋገራችሁ በጋራ ኮሜቲ አዋቅራችሁ በመምጣት እንድትጠይቁት እናሳስባለን ።
7ኛ. በመላው አለም የምትገኙ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ)ደጋፊች በውጭ ከኣቋቋምነው የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ (ጋሻ) ጋር በመሆን ከእኛ የሚተላለፈውን ማንኛውንም መልዕክት በእነሱ በኩል በማግኜት በሀገር ቤት የምናደርገውን የትግል እንቅስቃሴ እንድታግዙን እንጠይቃለን!

በመጨረሻም መላው አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን በሙሉ ከላይ የተዘረዘሩትን በማክብር ለተፈጻሚነታቻው ተገቢውን ሁሉ ታደርጉልን ዘንድ እንጠይቃለን ።
ዘሜነት አማራነት!
ዘሜነት ኢትዮጵያዊነት !
የአማራ ህዝባዊ ሀይል ፋኖ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ።

አዲስ ትውልድ፣ ኣዲስ ኣስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ !!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator