የአንድ ቤተሰብ አባላትን ገድሎ ቤታቸውን አውድሞ አስከሬናቸውን እዛው ቀብሯል‼️
በሃይቅ ከተማ ጨረቃ ሰፈር ነዋሪ የሆኑት የከተማዋ አፈጉባኤ ወይዘሮ ኮከቤ ሰዒድና ባለቤታቸው አቶ ሰዒድ ከረቤ የአሸባሪው ህወሓት የክፋት በትር ካረፈባቸው ንጹሀን ነዋሪዎች መካከል ናቸው፡፡
የቡድኑ ታጣቂዎች በግለሰቦቹ ቤት ላይ ሆን ብሎ በፈጸመው ጥቃት አቶ ሰዒድ ከረቤን፤ የ9ኛ ክፍል ተማሪ የነበረችው ልጃቸውን ኢልሃም ሰዒድን ጨምሮ አራት የቤተሰቡን ህይወት በጭካኔ ጨፍጭፏል፡፡
በሌሎች ሁለት የቤተሰቡ አባላት ላይም ከባድና ቀላል ጉዳትን አድርሷል፡፡
የወራሪው እና አሸባሪው ታጣቂዎች በግድያው አልረካ ብለው፤ ዘመድ አዝማድ ተሰብስቦም እርሙን እንዳያወጣ ከልክለው ሁሉንም በአንድ ላይ ደጃቸው ላይ ቀብረዋቸዋል፡፡ ይህንንም የኢፕድ ዘጋቢዎች በከተማዋ ተገኝተው አረጋግጠዋል።
በዘላለም ግዛው (ከሀይቅ)