0 0
Read Time:1 Minute, 21 Second

አሸባሪው የህውሐት ቡድን በወረራ ይዞ በቆየባቸው አካባቢዎች ላይ ትምህርት ቤቶችን በማውደምና በመዝረፍ የክፋቱን ጥግ አሳይቷል የጭካኝነትና የክፋተኝነት ጥግ ማሳየቱን የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴርና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አመራሮች በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ በአሸባሪው የህወሐት ቡድን የወደሙና ጉዳት የደረሰባቸውን ትምህርት ቤቶች ጎብኝተዋል፡፡

አሸባሪው የህወሐት ቡድን የትምህርት ተቋማትን መገልገያ ቁሳቁሶችን፣ ፕላዝማ ቴሌቬዥኖች፡ የቤተሙከራ ኬሚካሎች፣ ወንበሮችና መጽሐፍትን ዘርፏል፤ ቀሪውን አውድሟል፡፡ ትምህርት ቤቶችን በከባድ መሳሪያ ደብድቧል፡፡

ኘሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማትን ከጎበኙ በኋላ አሸባሪው የህወሃት ቡድን ትምህርት ቤቶችን ከመዝረፉ ባለፈ ድጋሚ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማውደሙ የጨካኝነትና የክፋተኝነት ጥግ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡

በሽብር ቡድኑ ከፍተኛ የንብረት ዘረፋና ውድመት የደረሰባቸውን የትምህርት ተቋማት ደረጃቸውን ባሟላ መልኩ እንደገና መልሶ ለማቋቋም የፌዴራልና የክልል መንግስት ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር በመተባበር ወደ ነበሩት ለመመለስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወራሪው ሃይል በትምህርት ቤቶች ላይ አስከፊ ውድመት በመፈጸም በትክክል ከወራሪ የሚጠበቅ ተግባሩን አስመስክሯል ያሉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ማተብ ታፈረ ናቸው፡፡ አሸባሪና ወራሪው ሃይል በትምህርት ቤቶች ላይ በመማሪያ ክፍል ሳይቀር የጅምላ መቃብር በመፈጸም በትውልዱ ውስጥ መጥፎ ታሪክ ጥሎ እንደሄደም ገልጸዋል።

በአማራ ክልል ከአራት ሽህ በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉና በከፊል ውድመት ማድረሱን ገልጸው የቡድኑ አላማ የሚሳካው ትምህርት ቤቶችን በፍጥነት መልሶ ገንብቶ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ ካልተቻለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር መልሶ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ እንደሚሰራም ገልጸዋል።

በሰሜን ወሎ ዞን 912 የትምህርት ተቋማት ሙሉ በሙሉ ዝርፊያና ውድመት መድረሱን የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ጋሻው አስማሜ ተናግረዋል። አሸባሪና ወራሪው ሀይል በኢትዮጵያ ቀርቶ በአለም ላይ ተደርጎ የማይታወቅ ዘግናኝ ግፍ ፈጽሟል። የወራሪና አሸባሪ ቡድኑ ዋና አላማ በትውልድ ላይ ዘላቂ ጥቃት ማድረስና ማሸማቀቅ መሆኑን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል የወደሙና የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ መገለፁን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator