የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አሰልጣኝ ጀግናው አዲሱ ቢተውን ጨምሮ አምስት ፋኖዎች ከማቻክል ወረዳ በተሰማራው የፌደራል ፖሊስ፣ህዝባዊ ፖሊስ፣አማራ ልዩ ኃይል፣ አድማ በታኝና ሚሊሾችን ባካተተው ጥምር ኃይል
ተገድለዋል።
በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻክል ወረዳ ምንጨቀስ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቆልቆሌ ላይ መጋቢት 3/2014 በግምት ከቀኑ 7 ሰዓት አካባቢ በፋኖዎች ላይ በጥምር ኃይሉ ግድያ ተፈጽሟል።
የተገደሉት የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ አመራር እና አባላት:_
1) አዲሱ ቢተው
2) እናውጋው ታደለ
3) አጃናው አዲሱ
4) ጸሀይ አላምነህና
5) አናጋው በላይ በግፍ ተገድለዋል።
የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት ምንጨቀር ቀበሌ ቆልቆሌ በተባለ አካባቢ ጥላ ስር አርፈው በተቀመጡበት ነው ድንገት ከበባ በማድረግ የገደሏቸው።
ከተገደሉት መካከል “የዓመት በዓል በግ ይመስል እጄን እና እግሬን ታስሬ ሳትንፈራገጥ ታረድ የሚል መልዕክት ነው እነሱ እየሰጡን ያለ፤ እኔ ደግሞ ተንፈራግጨ ነው የምሞት እያልኩ ነው።” በሚል የብልጽግና ተሿሚዎችን ትጥቅ የማስፈታት አካሄድ ያወገዘ እና እጅ አልሰጥም ያለው የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አሰልጣኝ አዲሱ ቢተው ይገኝበታል።
ከማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማ 30 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ህዝባዊ ፖሊስ፣ ፌደራል ፖሊስ፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ አድማ በታኝና ከማቻክልና ከደምበጫ ዋዴ ዘለቃ የተወጣጡ ሚሊሻዎች ጥምር ኃይል ነው ጥቃቱን የፈጸመው ተብሏል።
አስከሬናቸው ወደ አማኑኤል ከተማ እየተወሰደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
11 ዓመታት በመከላከያ ሰራዊት አባልነት ያገለገለውን፤ በርካታ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አባላትን ያሰለጠነውን እና አሁን ላይም ያለ ጥፋቴ ትጥቅ ካልፈታህ ተብያለሁ በሚል ከየካቲት 13/2014 ጀምሮ እንጅባራ ላይ ከተደረገበት ከበባ ሸሽቶ እየተሳደደ የሰነበተው አሰልጣኙ መጋቢት 3/2014 ከሰዓት በኋላ ከሌሎች 4 ፋኖዎች ጋር በግፍ ተገድሏል።
ከአሚማ ጋር በአፈና ወቅት በነበረው ቆይታ “ገና ጁንታ መጥቶ ይመራኛል” የሚል አስተሳሰብ ያለው አመራር እንዳለ መናገሩ ይታወሳል።
ነፍስ ይማር፤
መጽናናትን ተመኘን!