0 0
Read Time:45 Second

በምዕራብ ሸዋ ዞን በዳሮ ወረዳ፤ ነዶ ወረዳና ጅባት ወረዳ የሚገኙ ዐማሮች የካቲት 11/2014 ዓ.ም በኦሮሚያ ልዩ ኃይል በድሽቃ፣ በስናይፐርና በሞርታር ተደብድበዋል፡፡ በጥቃቱ አራት ሰዎች እንደሞቱ፣ ከቦታው ተፈናቅለው ደብረብርሃን የገቡ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

ምስል፣ ከኦሮሚያ ተፈናቅለው ዐማራ ክልል የተጠለሉ

በሶስቱ ወረዳዎች በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዐማሮች በከተማና በገጠር የሚኖሩ ሲሆን፣ ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ሥልጣን በያዙ ማግስት ኦነግ/ሸኔ በአካባቢው መንቀሳቀስ እንደጀመረ ደብረብርሃን የገቡት ተፈናቃዮች ይናገራሉ፡፡ ኦነግ/ሸኔ ወደ አካባቢው መጀመሪያ ሲገባ የታጠቃቸው መሳሪያዎች ብሬን፣ ስናይፐርና ክላሽ የነበሩ ሲሆን፣እስከ ሶስት መቶ ተዋጊዎችን የያዘ ኃይል ሆኖ ይንቀሳቀስ ነበር፡፡

ይህ ኃይል በአካባቢው እንደደረሰ ዐማራን እየለየ እየገደለ፣ እያፈናቀለና ንብረት እያወደመ ቢቆይም ፣ መንግሥት ምንም እርምጃ ባለመውሰዱ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በግል መሳሪያ እየገዛ ራሱን ከመከላከል አልፎ ኦነግ/ሸኔን ለማዳከም ችሎ ነበር፡፡ በዚህ የተቆጡትና በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ያሉት የኦነግ/ሸኔ ሰርጎ ገቦች፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልን ወደ አካባቢው በመላክ በህዝቡ ላይ ከባድ የቡድን መሣሪያ በሆነው ዲሽቃ ያልታጠቀውን ህዝብ አስመትተውታል፡፡ በዚህ ጥቃት ሰዎች ሞተዋል፣ በርካታ ጉዳትም ደርሷል፡፡


About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator