እነ እስክንድር ነጋ ህዳር 16 ቀን 2014 ፍ/ቤት አለመቅረባቸውን ተከትሎ ለማነጋገር የሄዱት የባልደራስ አባላትና ደጋፊዎች ከጅምሩ ወደ ማ/ቤቱ ገብተው እንዳይጠይቁ ጠባቂዎች ሲከለክሏቸው እንደነበር፤ ነገር ግን በኋላ ላይ በተደረገ ውይይት ለመግባት መቻላቸውን በደብዳቤያቸው ገልጸዋል።
ከቂሊንጦ እስር ቤት እነ እስክንድር ነጋንና ስንታየሁ ቸኮልን ጠይቀው ሲወጡ እንዳይገቡ ሲከለክሏቸው በነበሩ የፖሊስ አባላት ተይዘው
ከቃሊቲ ማ/ቤት ፊት ለፊት፣ ከክራውን ሆቴል ጀርባ ባለ የፖሊስ መምሪያ በግፍ መታሰራቸው ተገልጧል።
ህዳር 16 ቀን 2014 የታሰሩት 5 የባልደራስ አባላትና ደጋፊዎች በላኩት ደብዳቤ እንደገለጹት ከቤተሰብ ጋር እንዳይገናኙ መደረጉን አስታውቀዋል።
ከቤተሰብ ያነጋገርነው ምንጭ እንደገለጸው በአካላቸው ላይ የደረሰ ድብደባም ሆነ ጉዳት የለም። ከእነሱ ውጭ በፖለቲካ ኬዝ የተያዙ ትልቅ ድብደባ እና የአይን መጥፋት ጭምር የደረሰባቸው እንዳሉም በደብዳቤው ላይ ተመላክቷል።
ከመካከላቸውም 3ቱ ማለትም:_
1.ምትኩ ካሳሁን
- ብሩክ ጫኔ እና
- ፋሲል ውሐብ ከሳምንታት በፊት በእነ እስክንድር ችሎት በተገኙበት ታስረው አንድ አንድ ሽህ ብር የዋስትና ከፍለው የተፈቱ መሆናቸውን የአሚማ ምንጭ ነግሮናል።
የግፍ እስረኞች ለአቶ እስክንድር ነጋ የጻፉት ደብዳቤ በግፍ እስር ላይ የምትገኘው የወ/ሮ ቀለብ ስዩም ባለቤት መ/ር በለጠ ጌትነት Belete Getenet እንዳጋሩት የሚከተለው ነው:_
ይድረስ ለአቶ እስክንድር ነጋ
ቀን 18.03.2014
በቀን 16 03 2014 እነ እስክንድርን ጠይቀን ስንወጣ ማለትም ከግቢው ውስጥ ከወጣን በኃላ በእግረኛ መንገድ ስንሄድ እርስ በእርስ ፎቶ በምንነሳሳበት መጀመሪያ በር ላይ አትገቡም ሲሉን የነበሩት ፖሊሶች ተከታትለውን ይዘውን ማለተም ፦
- ምትኩ ካሳሁን
- ብሩክ ጫኔ
- ፋሲል ውሐብ
- ዮርዳኖስ እንዳለ
- ሰላም የባለድራሷ ….. እነዚህ እነ እስክንድር ችሎት ላይ የማይቀሩ ናቸው በማለት ምንም አይነት አገልግሎት እንዳናገኝ ቤተሰብም ጠያቂም ጭምር አለማግኘታችን ምግብም ባለማግኘታችን ትልቅ ተፅእኖ ደርሶብናል።
አብረውን ከታሰሩትም ምንም አይነት አገልግሎት እንዳናገኝ ተደርገናል። እንዲሁም በፖለቲካ ኬዝ የተያዙ ትልቅ ድብደባ እና የአይን መጥፋት ደርሶባቸዋል።
እኛም ተራችንን እየጠበቅን ነው!! የታሰርነበትም ቦታ ምንም ማረፊያ የሌለው ሲሆን ፤ አንድ ክፍል ውስጥ ያለነው 20 ሰው የሚይዘው ቤት ላይ ከ100 እስከ 110 ሰዎች ታስረንበታል።
እኛን መርጠው ሌላ ቦታ ወደ ማናውቀው ቦታ ከ1000 ሰው ባላይ ከታሰረበት ሊወስዱን እንደሆነ ሰምተናል! ከፍተኛ ችግር ላይ ነን!!