ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቃል ገብቶ፤ ከአማራ ህዝብ ጋር ሂሳብ ሊያወራርድ ዝቶ በክልሉ ወረራ የፈጸመው አሸባሪው ህወሓት ያልፈጸመው ግፍ፣ ይህ ቀረኝ የሚለውም ወንጀል እንደሌለ ነጻ ከወጡ ከተሞች እየተመለከትን ነው።
በኮምቦልቻ የተገኙት የኢፕድ ዘጋቢዎች የኮምቦልቻ ሆስፒታል በአሸባሪው ታጣቂዎች መዘረፉን፤ የተረፈው ንብረት ደግሞ መውደሙን ተመልክተዋል።
ይህ አሸባሪ ቡድን በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ ንጹሀንን በጅምላ ገድሏል፤ ከህጻን እስከ አዛውንት የለምንም ምህረትና ልዩነት ሴቶችን ደፍሯል፣ ንብረት ዘርፏል፤ አቃጥሏል፤ በጅምላ ገድሏል።