0 0
Read Time:1 Minute, 9 Second

በኮምቦልቻ ከተማ የጅምላ መቃብር ተገኘ።

አሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ኃይል በከተማዋ ዘረፋ ፈፅሟል የማይፈልገውን ደግሞ በቻለው አቅም አውድሟል።

የሽብር ቡድኑ በዘረፋቸው ተቋማት ግቢ ውስጥም ጅምላ መቃብር ተገኝቷል።

የኮምቦልቻ ምክትል ከንቲባ አህመድ የሱፍ “በከተማችን የተለያዩ ቦታዎች በርካታ ንፁሃን ሰዎች በግፍ ተረሽነዋል ደብዛቸውም ጠፍተዋል” ያሉ ሲሆን “በከተማ የተለያዩ ተቋማት የጅምል መቃብር ተገኝተዋል” ብለዋል።

ዝርዝሩን መንግሥት አጥንቶ ለከተማው ማኅበረሰብም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገለፅ ይሆናል ሲሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።

ዋልታ ቴሌቪዥን በኮምቦልቻ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ የጅምላ ቀብርና ለቀብር መቆፈሪያና አፈር መመለሻ የዋለ ኤክስከባተርን ተመልክቷል።

ለጅምላ መቃብር ተቆፍሮ የተዘጋጀ ጉድጓድንም አይቷል።

እስካሁን ባለው ሂደት የጅምላ መቃብሮቹ በኮምቦልቻ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ፣ በቃሉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅና የተለያዩ አካባቢዎች እንደማገኙ የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ወራሪ ኃይሉ በኢንደስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በቆየበት አንድ ወር ከአንድ ሳምንት ተቋማትን አውድሟል፤ ዘረፋ ፈፅሟል፤ ሴቶችን ደፍሯል ንፁሃንን ገድሏል።

በከተማዋ የሚገኘውን የደረቅ ወደብ ተርማሚናል ከ800 በላይ ኮንቴነር ሙሉ ዕቃ ጭኖ ወስዷል።

በከተማዋ ከሚገኘው በተለምዶ ጢጣ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ባለ የነዳጅ ማጠራቀሚያ በየቀኑ በቦቲ ጭኖ ይወሰድ እንደነበር የአይን እማኞች ለዋልታ ተናግረዋል።

የኮምቦልቻ ማረሚያ ቤትን ሙሉ ለሙሉ በማቃጠል አውድሟል።

አሸባሪው ሃይል በኮምቦልቻ ከተማ ያደረሳቸው ጉዳቶች
▬▬▬▬▬▬▬▬
➔ምን ያህል ንጹሐን እንደተቀበሩባቸው ያልታወቁና በስካቫተር የተቆፈሩ የጅምላ መቃብሮች ተገኝተዋል

➔የኮምቦልቻ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ፣ የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅና የቃሉ የቴክኒክ ኮሌጅ የንጹሐን የጅምላ መቃብሮች ሆነው መክረማቸው ተረጋግጧል።

➔በኢንዱስትሪ ከተማው ውስጥ ያሉ ፋብሪካዎች ሁሉ ተወስደዋል። የቀረው ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

➔የኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ውስጥ የነበረ ከ800 ኮንቴነር በላይ የሆነ ሐብት ወደ ትግራይ ተዘርፎ ተወስዷል።

➔ኔትወርክ ከተለቀቀበት ጊዜ አንስቶ ስለመደፈራቸው ሪፖርት የሚያደርጉ ሴቶች ተበራክተዋል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator