0 0
Read Time:2 Minute, 11 Second

የአድዋ እና የካራማራ የድል በዓልን ተከትሎ በዓደባባይ ስሜ ጠፍቷል በሚል የአዲስ አበባ ወጣቶችን በጅምላ ሰብስቦ እያሰረ ያለው የአዳነች አቤቤ መንግስት ግፉን ቀጥሏል። የባልደራስ አባላት ቢኒያም ታደሰ እና ሳሙኤል ዲሚትሪ /ኩባ/ ጨምሮ፣ በደረጀ ይበይን የክስ መዝገብ የተካተቱት የ15 የአዲስ አበባ ወጣቶች ዛሬ ጠዋት አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀረበዋል፡፡ ታሳሪዎቹ ፍርድ ቤት የቀረቡት ከ15 ቀን እስር በኋላ ሲሆን፣ ዛሬ ቢያንስ በዋስትና ይለቀቃሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ እስረኞቹ በግምት 4፡00 ሰዓት ላይ ችሎት ፊት ሲቀርቡ፣ ከፊሎቹ በዓድዋ ክብረ በዓል ጊዜ አድርገውት የነበረውን ቲሸርት ለብሰው ቀርበዋል፡፡
ፖሊስ “የበርካታ የምስክሮችን ቃል ተቀብያለሁ፣ ስልኮች እንዲመረመሩ ለመረጃ እና ደህንነት ልኬያለሁ፣በቤት ብርበራ ያገኘኋቸውን ማስረጃዎች እየተመለከትኩ ነው፡፡ ሆኖም፣ አሁንም ተጨማሪ የምስክሮችን ቃል ለመቀበል ጊዜ ያስፈልገኛል፣ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን እያፈላለኩኝ ነው፣ የቪዲዮ ማስረጃዎችን ከመገናኛ ብዙሃን እንዲሰጡኝ ጠይቄ መልስ እየጠበኩኝ ነው፣ የተጠርጣሪዎችን የጀርባ ታሪክ እያጠናሁ ነው፣ እስረኞቹ ቢለቀቁ ምስክሮችን እና ማስረጃዎችን ስለሚያጠፉብኝ በእስር ላይ ቆይተው የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይጨመርልኝ ” ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
የተከሳሽ ጠበቆች ምላሽ በበኩላቸው ደንበኞቼን እየተበቀላችሁ ነው ፣ “እስረኞቹ የሚገኙት በቤተሰቦቻቸው ጥየቃ በማያመቸው እና በምርመራ ላይ ያሉ ተጠርጣሪዎች በማይታሰሩበት በአባ ሳሙኤል መሆኑ ወጣቶቹን የመበቀል አጀንዳ እንዳለ ያመላክታል፣ እንደ ክሱ ጥፋተኛ ቢሆኑ እንኳን የቅጣቱ ጣራ 300 ብር ወይም 3 ወር እስራት ስለሆነ ዋስትና የሚያስከለክል አይደለም፣ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት መሞከር ጭራሽ ወንጀል ነው ተብሎ በህግ የተደነገገ ነገር የለም፣ባለሥልጣናት የግል አቤቱታ ባለቀረቡበት ሁኔታ ፖሊስ በስማቸው ምርመራ የሚያደርገው በህግ አግባብ አይደለም፣ እስረኞቹ ማስረጃ እና ምስክሮች ሊያጠፉ የሚችሉበት የተለየ መንገድ ስለመኖሩ ፖሊስ አሳማኝ መከራከሪያ አላቀረበም፣ ከእስረኞቹ መካከል በደም ግፊት፣ በስኳር እና በተለያዩ ህመሞች እየተሰቃዩ የሚገኙ አሉ፡፡ ስለዚህም፣ተጠርጣሪዎቹ ተጨማሪ 14 ቀን በእስር ላይ የሚቆዩበት ህጋዊ ምክንያት ስለሌለ በነፃ ይሰናበቱ፣ አልያም በዋስትና ዛሬውኑ እንዲለቀቁ ይደረግልን” በማለት አቤቱታቸውን አቅርበዋልል ሲል ባልደራስ ሚዲያ ገልጿል፡፡
የባልደራስ አባልና ታዋቂ የጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊ የሆነው ቢኒያም ታደሰ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው አቤቱታ፣ “የታሰርንበት ሁኔታ በጣም ከባድ ነው፣ ታስረን የምንገኘው በሽንት ቤት ላይ ነው፣ ህክምናም የለም፣ ጥየቃው በሳምንት 3 ጊዜ ብቻ ሲሆን፣ ከእነዚህ ቀናት መካከል እሁድ ስላልተካተተ ቤተሰቦቻችንን በአግባቡ ማግኘት አልቻልንም ” ብሏል፡፡
ሌላ እስረኛ በበኩሉ፣ “ የታሰርኩት ታማሚ እናቴን የምንከባከበው እኔ ብቻ በሆንኩበት ሁኔታ ውስጥ ሆኜ ነው፣ እናቴ መንቀሳቀስ አትችልም፣ በጣም ችግር ላይ ትገኛለችና የዋስትና መብቴ ተጠብቆ እናቴን ወደመንከባከብ ልመለስ ይገባል ” በማለት ሲቃ እየተናነቀው ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡ ሌላ እስረኛ ደግሞ፣ “እኔ በሙያዬ ነገረ ፈጅ ነኝ፣ ስለ ህግ አውቃለሁ፡፡ አሁን ምርመራ እየተደረገብን ያለው አዳነች አበቤን ብቻ ተሳደባችሁ ተብለን ነው፡፡ ስለ አንድ ባለሥልጣን እንጂ ስለ ብዙ ባለሥልጣናት እየተጠየቅን አይደለም፡፡ ግለሰቧ አቤቱታ ባላቀረቡበት ሁኔታ ፖሊስ ምርመራ ማድረግ አይችልም” ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ ሁለቱን ወገን ካዳመጠ በኋላ፣አስቀድሞ ወስኖ የቆየ በሚያስመስለው ሁኔታ የቀረቡትን ክርክሮች በቂ ምላሽ ሳይሰጥባቸው ተጨማሪ 10 ቀናት በመፍቀድ፣ ለመጋቢት 22 2014 ዓ.ም ጠዋት ቀጠሮ ሰጥቷል ፡፡ ተጠርጣሪዎቹ ከችሎት ሲወጡ ፍርድ ቤቱ ለነበሩት ቤተሰቦቻቸው፣ የባልደራስ አመራሮችና አባላት፣ እንዲሁም የችሎቱን ሂደት ለመከታተል በቦታው ለተገኙት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጥተዋል፡፡ “አንሰበርም፣ አንሸነፍም” በማለትም ተናግረዋል፡፡

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator