0 0
Read Time:1 Minute, 27 Second

31ዱ የታሰሩ የባልደራስ አመራሮች፣አባላትና ደጋፊዎች አዲስ የክስ ፋይል የተከፈተባቸው መሆኑ ተገልጧል።

ከ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተዘዋውረዋል።

በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙትና ለነገ ሐሙስ ፍርድ ቤት ለመቅረብ ቀጠሮ የነበራቸው 31 የባልደራስ አባላት፣ የካቲት 30/2014 ማለዳ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እንደ ድንገት አራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡

ተከሳሾቹ በ3 መዝገብ ተከፍለው ዳኛ ፊት የቀረቡ ሲሆን፣ በመጀመሪያ መዝገብ እነ ጌጥዬ ያለው ችሎት ቀርበዋል፡፡

በችሎቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መርማሪዎች ሲሆኑ፣ ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት አቤቱታ፣ “ተከሳሾች በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ በነበሩበት ጊዜ ተከፍቶባቸው የነበረው የክስ መዝገብ ተዘግቷል፡፡

አሁን እዚህ የመጣነው አዲስ የክስ መዝገብ ልንከፍትባቸው ነው” ብለዋል፡፡ ጌጥዬ ያለው አብረውት ያሉትን ተከሳሾች ወክሎ በሰጠው አስተያየት፣ “እዚህ ያመጡን እንደ ድንገት ነው፡፡ ጠበቆቻችን አልሰሙም፡፡ ጠበቆቻችን ባሉበት ጉዳዩ እንዲታይ ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጠን ”ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱም ጉደዩን ለመመልከት ለነገ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ቀጥሯል፡፡

ሁለተኛው ቡድንም በወግደረስ ጤናው መዝገብ፣ ሶሶተኛው ቡድን በመአዛ ታደሰ መዝገብ ስር ሆነው የቀረቡ ሲሆን፣ ወግደረስ ጤናውና ሰለምን አላምኔም ጠበቆቻቸው ባሉበት ክርክር እንዲረግ ለነገ እንዲቀጠር ፍርድ ቤቱን ጠይቀው፣ እነሱም ለነገ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ተቀጥረዋል፡፡

ከባልደራስ እስረኞች ጋር አብሮ በእስር ላይ የሚገኘው ናትናኤል ጌታቸው የተባለ እስረኛ በበኩሉ፣ ዜግነቱም ሆነ ነዋሪነቱ እንግሊዝ አገር መሆኑን፣ የተያዘው በአጋጣሚ በቦታው ተገኝቶ መሆኑን፣ የሁለት ልጆች አባት እንደሆነና ቅዳሜ ወደ እንግሊዝ ለመመለስ በረራ እንዳለው በመግለጽ፣ ፍርድ ቤቱ በነፃ እንዲለቀው ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ ግን፣ አጠቃላይ ጉዳዩን ነገ ጠዋት እመለከተዋለሁ በማለት የናትናኤልን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል፡፡

ችሎት ካለቀ በኋላ እስረኞቹ በቀጥታ ጊዮርጊስ ወደሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እስር ቤት የተወሰዱ ሲሆን፣ ልብስ እና እቃዎቻቸው በሙሉ በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት እንዲቀር ተደርጓል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በርካታ የአዲስ አበባ ወጣቶች ታስረው ይገኛሉ።

ከነዚያም መካከል ከ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን ቀደም ብለው የተዘዋወሩት እና የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ የተሰጠባቸው ቢኒያም ታደሰ እና ሳሙኤል ዲሚትሪ ይገኙበታል፡፡

ዜናው የባልደራስ ሚዲያ ክፍል ነው።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator