0 0
Read Time:1 Minute, 13 Second

የባለአደራው ምክር ቤት ምሥረታ ታስቦ ዋለ!

“በአዲስ አበባ ያለው የተረኝነት መንፈስ ከመቼውምጊዜ በላይ ተባብሷል” እስክንድር ነጋ

“የታሰሩት በመንፈስ ከእኛ ጋር ናቸው” ስንታየሁ ቸኮል

/
መጋቢት 1 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ በባልደራስ የስብሰባ አዳራሽ የተመሠረተው የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት 3 ኛ አመት ክብረ በዓል በባልደራስ ዋና ጽ/ቤት ሻማ በማብራት ታስበ፡፡ የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት በኢንጀር ታከለ ኡማ የከንቲባነት ዘመን የተጀመረውን የተረኝነት አካሄድ በመቃወም መቋቋሙ ይታወሳል፡፡

ህወሓትን ተክቶ ገዥውን ፓርቲ በመምራት ላይ የሚገኘው ኦህዴድ፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት በመደፍጠጥ ከተማዋን በሃይል የኦሮሚያ አካል የማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ የከተማውን ሕዝብ መብት የባለአደራው ምክር ቤት በነበረው የሲቪክ ማህበር ቁመና ማስጠበቅ የማይቻል ስለነበር፣ በሕዝቡ ጥያቄ በየካቲት 2012 ዓ.ም ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ እንደ ፖለቲካ ድርጅት ሆኖ መወለዱ ይታወሳል፡፡

ትላንት በነበረው ሥነ ስርዓት የታደሙት የባልደራስ አባላት፣ በአሁኑ ጊዜ በእስር ላይ የሚገኙትን እህትና ወንድሞቻቸውን በማስታወስ፣ በግፍ መታሰራቸውን ጠቅሰው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እስከሚፈቱ ድረስ ያላሰለሰ ትግላቸውን ለማጠናከር ቃል ገብተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ያለው የተረኝነት እንቅስቃሴ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተባብሶ እንደሚገኝ የጠቀሱት የፓርቲው ፕሬዘደንት እስክንድር ነጋ፣ “ገዥዎቻችን ጠብመንጃ ይዘዋል፣ እኛ ደግሞ እውነትን ይዘናል፡፡ እነሱ በጠብመንጃቸው ይመኩ፣ እኛ ደግሞ፣ ኃይል የእግዚአብሔር ነው እያልን በያዝነው እውነት እንመካለን፤ ያለጥርጥርም እናሸንፋቸዋለን” ብለዋል፡፡

የባልደራስ አደረጃጀት ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል በበኩላቸው “በግፍ የታሰሩት የባልደራስና የአዲስ አበባ ወጣቶች በአካል ከእኛ ጋር ባይኖሩም በመንፈስ ግን ከእኛ ጋር መሆናቸውን አውቀን አደራቸውን ተቀብለን መታገል አለብን፡፡ እነሱ ታስረው እኛ እዚህ የደመቀ ስነ ስርዓት ለማድረግ ስለከበደን ለብዙዎች ጥሪ ከማድረግ ተቆጥበናል” ብለዋል፡፡

በመጨረሻም፣ ስነ ስርዓቱ ሻማ በማብራት እለቱ ታውሶ የእለቱ መርሃ ግብር ተፈጽሟል፡፡

ዜና #ኢትዮጵያ #ባልደራስ

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator