በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ የአማራ ሚሊሻዎችን ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻው እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጧል፤ በስልክ አምባና በዙሪያ ቀበሌዎችም ተኩስ ተከፍቶ ውሏል።

በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ፣ኖኖ እና ጅባት ወረዳዎች በአማራ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸም ከጀመረ ከራርሟል፤ በዚህም በርካታ ንጹሃን አማራዎች በተለያዩ ጊዜያት ተገድለዋል፤ ተዘርፈዋል፤ ሀብት ንብረታቸው ተዘርፏል፤ተቃጥሏል።

ከዚህም በተጨማሪም በአስር ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ማንነታቸው ብቻ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለዋል።

በዳኖ እና ኖኖ ወረዳዎች ጥቃቱ ተጠናክሮ ቀጥሏል፤ ከቀናት በፊት በአዲግራት ዩኒቨርስቲ ይማር የነበረ የአማራ ተማሪ ማንነቱ እንደወንጀል ተቆጥሮ መገደሉ ተወስቷል።

በተመሳሳይ አንድ የአማራ ተወላጅ የሆነ ባለሀብትም እህል ለመጫን በሚል ከስልክ አምባ ወደ መቱስላሴ አይሱዙ ይዞ እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ በጽንፈኛ ኦነጋዊያን በግፍ ተገድሏል፤ መኪናውም ተቃጥሏል።

የሽብር ቡድኑ ተባባሪዎች በስልክ አምባ ከተማ የሁለት አማራ ባለሃብቶችን የእህል መጋዝን አቃጥለዋል።

በተጨማሪም በገጠር አካባቢ ያለ የአማራዎች ቤት እየተፈለገ እንዲወድም እየተደረገ ነው፤ በከተማው ዙሪያ ባለ ቀበሌ እንኳ 17 ቤቶች ተቃጥለዋል።

ህዳር 10 ቀን 2014 ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ የሚሊሾችን ትጥቅ በኃይል ለመንጠቅ በተደረገ ግብግብ ሁለት የኦሮሞ ተወላጆች መገደላቸውም ተሰምቷል።

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት ይህን እንደ መነሻ በማድረግ የአማራ ሚሊሾችን ትጥቅ ለማስፈታት በማለም ተኩስ ከፍተዋል።

በተለይ ስልክ አምባ ከተማ እና አካባቢው ባሉ ሚሊሾች ላይ ህዳር 10 እና 11 ቀን 2014 ተኩስ ከፍተው ውለዋል።

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት ከአምስት በላይ ሚሊሾችን ድንገት በመያዝ የጦር መሳሪያቸውን ከመግፈፍ አልፈው ክፉኛ ሲደበድቡና ወጣቶችን ሲያሳድዱ የተመለከቱ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው የአማራ ሚሊሾችም ጫካ መግባታቸው ታውቋል።

በኖኖ ወረዳ የስልክ አምባ ከተማና በገጠር ቀበሌ ያሉ አማራዎች በገፍ እየተፈናቀሉ ዳርጌ ወደተባለው የደቡብ ክልል አካባቢ እየተሰደዱ መሆኑ ተገልጧል።

የፌደራል መንግስትም በአስቸኳይ ተጨማሪ ኃይል አስገብቶ አካባቢውን እንዲያረጋጋ፣ ንጹሃንን እንዲታደግ እና ተኩሱን እንዲያስቆም ጥሪ ቀርቧል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator