0 0
Read Time:4 Minute, 41 Second

አቻምየለህ ታምሩ

ቂጡን በቅጡ ያልጠረገ ኩታራ ሁሉ እየተነሳ ተሸክሞ የሚዞረውን የኦነጋውያን የአህይነት ጭነት ባራገፈ ቁጥር መኪና በመንዳት የመጀመሪያው ጥቁር መሪ የሆኑት ዳግማዊ ምኒልክ አህያ እንጂ ፈረስ ጋልበው የማያውቁ ቢመስለው አይፈረድበትም። አጥፊዎቹ በዘውግ ወስነው የራሳቸው ካደረጉት ኅብረተሰብ የተገኘውን ወጣት ክፍል ያራገፉበትን የፕሮፓጋንዳ ጭነት ሁሉ ሳያንገራግር ወደሚሸከም ፍጡር ያወረዱት የፕሮፓጋንዳው ፈጣሪዎች ናቸው።

እንኳን የቅርቡ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የጥንቶቹ የኢትዮጵያ ነገሥታት ሳይቀር እጅግ ግዙፍ፣ የተዋቡ፣ ቄንጠኛና እንደ መስከረም ፀሐይ ከሚያንጸባርቅ ወርቅ የተሰራ ኮርቻ የሚጫኑ ፈረሶችን ይጋልቡ የነበሩት ኦሮሞ ፈረስ ግልቢያ ከመለማመዱ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት ነበር።

ኦሮሞ ፈረስ ግልቢያ የለመደው ኢትዮጵያን መውረር በጀመረ በአርባ አመቱ ነበ። ኦሮሞ ፈረስብ ግልቢያ የለመደበት የገዳ ስም “ምችሌ” የሚባል ሲሆን ይህ ገዳ የነበረው ከ1546 ዓ.ም. – 1554 ዓ.ም. ባለው ዘመን ውስጥ ነው። ኦሮሞ ፈረስ መጋለብ የለመደው በዚህ ዘመን እንደሆነ ታሪኩን የነገሩን ብቸኛው የኦሮሞ ታሪክ ምንጭና ታሪኩ ሲፈጸም የዐይን ምስክር የነበሩት የጋሞው መነኩሴ አባ ባሕርይ “ዘናሁ ለጋላ” በሚል ባሰናዱት መጽሐፋቸው ውስጥ ነው። የዐይን ምስክሩ አባ ባሕርይ ኦሮሞ ፈረስ መጋለብ የጀመረበትን ወቅት በመጽሐፋቸው ክፍል ዘጠኝ ላይ እንዲህ ይገልጹታል፤

“ወዝንቱ ምችሌ ወጠነ ተፅዕኖ ፈረስ ወበቅል ዘኢኮነ እምቅድሜሁ፤ እስከ ይቤሎሙ ለሉባ ዘቀደምዎ፤ ለእለ ኮኑ የሐውሩ በ፪ ወ ፫ እግር ረስይክዎሙ ይሖርይ በ፬ እግር። ወብሂሎቱሰ በ፫ እግር በእንተ ዘይትመርኮዙ በኩናቶሙ ሶበ ደክሙ በፍኖቶሙ።”

ትርጉም፤

“ይህ ምችሌ [የሚባለው ገዳ] ከእርሱ በፊት ያልነበረውን በፈረስና በበቅሎ ተቀምጦ መጋለብ ጀመረ። ከእርሱ አስቀድሞ የነበሩትን ሉባ፤ በ2 ወይም በ3 አግር ይሄዱ የነበሩትን በ4 እግር እንዲሄዱ አደረግኋቸው አስኪላቸው ድረስ ሆነ። [ምችሌ] በ3 እግር ማለቱም በመንገዳቸው በደከሙ ጊዜ ጦራቸውን ስለሚመረኮዙ ነው።”

የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰንም ይህን ታሪክ ደግፎ ጽፏል። ከአምስት ዓመታት በፊት “The Oromo and the Christian Kingdom of Ethiopia: 1300-1700” በሚል ባሳተመው መጽሐፉ ገጽ 173 ላይ ኦሮሞ ፈረስ መጋለብ የለመደው አባ ባሕርይ በጠቀሱት ዘመን በምችሌ ገዳ መሆኑን ጽፏል። የቺካጎ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪንም “ Greater Ethiopia: The Evolution of a Multiethnic Society” በሚል ርዕስ በ1966 ዓ.ም. ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ ገጽ 88 ላይ ኦሮሞ ፈረስ መጋለብ የጀመረው ከ1546 ዓ.ም. – 1554 ዓ.ም. ባለው ዘመን መሆኑን ጠቅሶ ፈረስ መጋለብ የተማሩትም ከኢትዮጵያውያን እንደሆነ አውስቷል።

ኦሮሞ ፈረስ መጋለብ ስለጀመረበት ዘመን ይህን ያህል ካልሁ አሁን ደግሞ ኦሮሞ ፈረስ ግልቢያ ከመለማመዱ ከብዙ ክፍለ ዘመናት በፊት ፈረስ ይጋልቡ ስለነበሩ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ቅድመ አያቶች የሆኑ የኢትዮጵያ ነጋሥታትን ታሪክ በዘመኑ ተመዘገቦ ከምናገኘው ታሪካቸው ወደማቅረቡ ልሸጋገር።

ሸዋን ማዕከላቸው አድርገው ኢትዮጵያን ከ1308 ዓ.ም. – 1336 ዓ.ም. ያስተዳደሩት አርበኛው ዐፄ አምደ ጽዮን “አረብ አስፈሪ” የሚባል ቄንጠኛ ፈረስ ነበራቸው። ዐፄ አምደ ጽዮን “አረብ አስፈሪ” የሚባለውን ፈረሳቸውን ይጋልቡ የነበረው ኦሮሞ ዛሬ የሰፈረበትን የኢትዮጵያ ክፍል ከመውረሩና ፈረስ ግልቢያ ከመለማመዱ ከ240 ዓመታት በፊት ነበር። ታላቁ ዐፄ አምደ ጽዮን “አረብ አስፈሪ”ን አያሰገሩ ሲዘምቱ እንደኖሩ፤ የሚያስጭኑት ኮርቻ የተዋበበትን ጌጥና የሚያሰግሩ ልሎች ፈረሶች እንደነበሯቸው ማወቅ የሚሻ ቢኖር እንግሊዛዊው የታሪክ ተመራማሪ ሐንቲግፎር “Glorious Victories of ‘Amda Seyon, King of Ethiopia” በሚል ርዕስ በ1957 ዓ.ም. ባዘጋጀው የንጉሡ ታሪከ ነገሥት ገጽ 90 እና ሌላኛው እንግሊዛዊ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፈሰር ወሊስ ባጅ “A History of Ethiopia: Volume I: Nubia and Abyssinia” በሚል ርዕስ በ1920 ዓ.ም. ባዘጋጁት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ገጽ 295 ላይ የሰፈረውን ጽሑፍ መመልከት ይችላል።

ኦሮሞ ፈረስ መጋለብ ከመልመዱ በፊት በፈረስ ጋላቢነታቸው የተወቁ መሆናቸውን የተመዘገበ ታሪካቸው የሚነግረውን ሌላኛው ጥንታዊ ፈረስ ጋላቢ የኢትዮጵያ ንጉሥ ደግሞ የዐፄ አምደ ጽዮን የልጅ ልጅ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ናቸው። በነገራችን ላይ ኢትዮጵያን ከ1426 ዓ.ም. – 1460 ዓ.ም. ያስተዳደሩት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የተወለዱት ከአባታቸው ቀዳማዊ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግሥት ክብረ እግዚ በ1391 ዓ.ም. ከአዋሽ ወንዝ አጠቀብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው መንደር በጥንቱ አጠራር ፈጠገር ፤ ኦሮሞ ከወረረው በኋላ ስያሜውን ከቀየረው በኋላ ደግሞ አርሲ ተብሎ በሚታወቀው ክፍለ ሀገር ውስጥ ነው።

የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብን ታሪከ ነገሥት ጁሊየስ ፔሩኮን በ1885 ዓ.ም. “Les Chronique de Zara Ya’eqob” በሚል ርዕስ ወደ ፈረንሳይኛ ተርጉሞ ካሳተመው መጽሐፍ ገጽ 24 ላይ ማየት እንደሚቻለው ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ታዋቂ ፈረሰኛ ብቻ ሳይሆኑ ደብረ ብርሃን ከተማ የነበረውን ቤተ መንግሥታቸው አንዱን በር ከእልፍኛቸው ወርደው ፈረሳቸው ላይ በመውጣት ቀጥታ ወደ ጉግስ ሜዳ መሄድ እንዲችሉ አድርገው ያሰሩ ንጉሥ ነበሩ።

ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ በኋላ ከኦሮሞ ወረራ በፊት የነገሡ የኢትዮጵያ ነገሥታት ይጋልቧቸው ስለነበሩ ፈረሶችና ስሞቻቸው፤ ለፈረሶቹ ማደሪያ በዘመናዊ አኳኋን ስለተሰሩት ቤተ አፍራሶች፤ ነገሥታቱ ብቻ ሳይሆኑ የየአውራጃው ገዢዎች ጭምር ያረቧቸው ስለነበሩ የፈረስ ዝርያዎች፤ ነገሥታቱ ስላቋቋሟቸው ፈረስ የሚረባባቸው ማዕከላትና አውራጃዎች እንዲሁም ሰብአ አፍራስ [ፈረስ ዐዋቆች፣ ለጓሞች ወይም ባልደራሶች ማለት ነው] የሚባሉትን ሰዎች በሚመለከት በዘመኑ የተጻፉት የታሪክ ማስረጃዎችን ቆጥሮ መጨረስ አይቻልም። በዚህ ረገድ ከኦሮሞ ወረራ በፊት ወደ አገራችን የመጡት ፕርቱጋሎቹ ፍራንሲስኪ አልቫረዝና ማኑኤል ደ አልሜዳ፤ እንዲሁም ፈረንሳዊው ቻርለስ ፖሴት ወደ አገራቸው ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያ ነገሥታት ስለሚጋልቧቸው ፈረሶች ጥንካሬ፣ ምርጥ ስለሆኑ የኢትዮጵያ የፈረስ ዝርያዎች፣ በአስር ሺዎች ስለሚቆጠሩ የነገሥታቱ ፈረሰኛ ተዋጊዎች ወዘተ የጻፉትን ታሪክ ማንበብ ይቻላል።

የኦሮሞ ብሔርተኞች ጭምር የዲግሪ ማሟያቸውን ሲጽፉ ኦሮሞ ፈረስ ግልቢያ የለመደው በፈረስ ግልቢያ የሚታወቁት የኢትዮጵያ ነገሥታት የሚያስተዳድሯቸውን የኢትዮጵያ አውራጃዎችን መውረር በጀመረ በ40 ዓመቱ እንደሆነ የሚያስረግጥ የተዘመገበ ታሪክ ባለበት ሁኔታ ነው እንግዲህ አንድ ገጽ ታሪክ እንኳ ታሪክ እንብበው የማያውቁ እንጭጮች ድንቁርና በሚሰጠው ድፍረት እየተመኩ ከጥንት ጀምሮ በፈረስ ጉግስ ጥርሳቸውን የጣሉ ነገሥታት ልጅ የሆኑትን ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን ፈረስ ግልቢያ የለመዱት ከነሱ ፈረስ በመወስደው እንደሆነ አድርገው ሊነግሩን የሚፈልጉት። እውነታው ግን እንጭጮች እንደሚሉት ሳይሆን ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ እንደ ቅድመ አያቶቻቸው እንደነ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብና ዐፄ አምደ ጽዮን ፈረስ ከመጋለብ አልፈው መኪና በመንዳትም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን ጥቁር መሪ ጭምር ናቸው።

ባባቶቻቸው ርስት ላይ የቆመውን የዳግማዊ ምኒልክን ሐውልት እናፍርስ የሚሉንን ግብዝ ኦነጋውያን ሕገ ወጥ ወራሪዎች መሆናቸውን ስለረሱት ማስታወስ ያስፈልጋል። ርስት የፈለገው ሰው ቢሰፍርበት ባላቤቶቹ ጨርሰው ሰካልጠፉ ድረስ ያለ ብርቱ ነገር አይለቀቅም። ለዚህም ነው ያገራችን ሰው “ርስት በሺሕ ዓመቱ ለባለቤቱ” የሚባለው። ተወረርን የሚሉን ኦነጋውያን በሌላው ርስት ላይ መስፈራቸውን ስለረሱትና ሌት ተቀን በርስታችን ላይ ስላቆሙ ሕውልቶች ሲያቀሩ ስለሚውሉ መነቀል ካለበት የሚነቀለው አማርኛ ተወልዶ ባደገበ ባያቶቻችን ርስት በሸዋ ማዕከል የቆመው የዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት ሳይሆን ከአፍሪካ ምድር ተነቅለው የወጡት ፖርቲጋሎች አንጎላንና ሞዛምቢክን ከያዙ በኋላ ኢትዮጵያን የመውረሩት እንሱ መሆናቸውን ልናስታውሳቸው እንወዳለን።

በተረፈ ሳይመረምሩ ኦነጋውያ ያራገፉባቸውን የአህይነት ጭነት ተሸክመው እየዞሩ ኦሮሞ ፈረስ ግልቢያ ከመልመዱና ኢትዮጵያን ከመውረሩ ከዘመናት በፊት ኢትዮጵያ ያስተዳደሩ ስመ ጥር ፈረሰኛ ነገሥታት ልጅ የሆኑትን ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን ወደ ኦሮሞ ሳይመጣ አህያ እንጂ ፈረስ ጋልቦ አያውቅም ለሚሉ ወሬ ደጋሚዎች «ወሬ ሲነግሩህ ሀሳብ ጨምርበት» የሚለውን የአያቶቻችን ጥልቅ ምክር በመለገስ ልሰናበት!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator