0 0
Read Time:1 Minute, 23 Second

ትግራይ ክልል ምርጫ ለማድረግ ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ውድቅ አደረገው

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ÷ ሰኔ 17/2012 ዓ/ም

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የትግራይ ክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲፈጸምለት ለቦርዱ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን አስታውቋል። ቦርዱ አመሻሹን በማሕበራዊ ድረገፁ ባወጣው መግለጫ በማንኛውም የምርጫ ዑደት የሚፈጸሙ ዋና ዋና ክንዋኔዎች ማለትም የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ማውጣት፣ ለምርጫ የሚወዳደሩ የፓለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ መቆጣጠር እና ማስተዳደር፣የምርጫ አስፈፃሚዎችን መልምሎ ማሰማራት፣ ጣቢያዎችን ማቋቋም፣ ምርጫውን ከተጽእኖ ነጻ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ማስፈጸም በመጨረሻም የውድድሩን ውጤት አረጋግጦ ለህዝብ ይፋ ማድረግ እና የመሳሰሉት ከማንኛውም የመንግስት ተቋም በተለየ ለቦርዱ የተሰጠ እና ከማንም አካል ጋር የማይጋራው ህጋዊ ስልጣኑ ነው ሲል የትግራይ ክልል ምርጫ ማድረግ እንደማይችል ገልፆአል።
6ኛው አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ እንዲራዘም ምክንያት የሆነው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሁኔታ እንደገና ተገምግሞ ምርጫ ማካሄድ የሚያስችል ሁኔታ መፈጠሩ እስኪረጋገጥ ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በየትኛውም የአገሪቱ ክልል ምርጫ አያካሄድም ብሏል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓለቲካ ፓርቲዎችን መመዝገብ፣ መቆጣጠር እና ማስተዳደር፣ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳን ማውጣት፣ የምርጫውን ከተጽእኖ ነጻ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ ማስፈጸም ስልጣን ያለው ብቸኛ ተቋም ነው ያለው ቦርዱ፣ የትግራይ ክልል ምክር ቤት በክልሉ ውስጥ 6ተኛውን ዙር የክልል ምክር ቤት ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም ቦርዱ ይህንን ውሳኔውን ተቀብሎ ሊያስፈጽም ይገባል የሚልበት ህጋዊ መሠረት የለም ብሏል። ቦርዱ የትግራይ ክልል ምክር ቤት የክልል ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ እንዲያውቅለትም ሆነ ምርጫ እንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄ ያልተቀበለው መሆኑን ጠቅሶ፣ የተጠየቀውን የሰው ሀይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የሚሰጥበት የህግ አግባብ አለመኖሩን በመግለጫው አሳውቋል።

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ወልቃይት ጠገዴ ውስጥ ያለው ሁኔታ ከቅኝ ግዛት የባሰ በመሆኑ ሕዝብ ምርጫ ማካሄድ ስለማይችል ምርጫ ቦርድና ሌሎች ተቋማት ህወሓት አካሂደዋለሁ ያለውን ምርጫ እንዲያስቆሙ መጠየቃችን ይታወሳል። በተመሳሳይ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ላይ ምርጫ ማድረግ እንደማይቻል ገልፆ ጉዳዩን በሕግ ለማስቆም እንደሚሰራ መግለፁ ይታወቃል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator