0 0
Read Time:3 Minute, 58 Second

ደረጅ ከበደ

ከሁሉም ከሁሉም የሚያስሳስቡኝ እነኝህ ችግር እያለ የለም የሚሉ ህዝብ እያለቀ ነገ የተሻለ ይሆናል የሚሉ ናቸው። የወደፊቱን የተሻለ ለማድረግ ወይም ዘለቄታ ያለው ሰላም በኢትዮጵያ እንዲሰፍን ወይም ብሄሮች እርስበርስ ሳይጫረሱ በአንድ አገር መኖር እንዲችሉ የሚያመቻች የህገመንግስት፣ የመዋቅርና የመረሆ ለውጥ ሳይደረግ እንዲያው በምኞት ብቻ ኢትዮጵያ አትፈርስም የሚሉ ያሳስቡኛል። ምክንያቱም ኢትዮጵያ አትፈርስም እያሉ ኢትዮጵያ ስትፈርስ አፋቸውን ዘግተው አሁንም እያዩዋት ነው። አንድ የምእራባውያን ፊልም ላይ አንድ የሆነ ሰው በጥይት እየደበደቡት አልሞትኩም (I Am still Alive) አልሞትኩም አልሞትኩም እንዳለ የሞተበት ትዝ ይለኛል። ወኔው ለጊዜው ይደነቃል ነገር ግን ከሞት ያማያድን ባዶ ወኔ ነበር። በሃገራችን የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተገበረ ነው ። አማራው በግላጭ ከወያኔ ጊዜ ጀምሮ እንዲጠፋ በተፈረደበት መሰረት ለ 27 አመታት ከዛም ለዶ/ር አቢይ ስርአቱ ተላልፎ የአማራው ግድያ በተጡዋጡዋፈ መልኩ ቀጥሎአል። ይህንን ሃቅ ማድበስበስና እንዳላዩ ለመሆን ማስመሰል ትልቅ ዋጋ ያስከፍላል። ሃገር እየተሸራረፈች ይህንን ሂደት እንደማስቆም የአቢይ ደጋፊዎች አቢይ ያሻግረናል ይላሉ። ወዴት ነው የምትሻገሩት? ሃገር እኮ በምኞት ወይም በአስማት ከመበታተን አትድንም። ብሄር በብሄር ላይ እንዲነሳና እንዲጨካከን ያደረገው ምንድነው? ብሎ ሰው ለምን አይጠይቅም? ከኦሮሞ ክልል ውጡ እየተባሉ የተጨፈጨፉት፣ እሬሳቸው ጎዳና ላይ የተጎተተው አማራዎችና ጉራጌዎች ጉዳይ እውን አይደለም እንዴ? ደግ መመኘት ከተግባር ጋር ካልተዋሃደ እንዲያው ፈረንጆች “Wishful thinking” እንደሚሉት ምኞት ሆኖ ይቀራል።

አሁን ኢንተርኔት ተዘግቶ የተፈፅመውን ጭካኔ ምንም አላየንም ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ በአቢይ አስተዳደር ወደ ለየለት የዘር ማጥፋት ተግባር በይፋ ገብታለች። ምናልባት በሩዋንዳው ደረጃ መቶ በመቶ እልፈነዳም (Fullblown scale) ይባል ይሆናል እንጅ ጄኖሳይዱ ከተጀመረ ቆይቶአል። ልብ ብላችሁ ከሆነ ደግሞ ለምሳሌ የቅርብ ጊዜ ምሳሌ ብንወስድ ባለፉት ጥቂት ወራቶች የተፈፀመው በጃዋር የተከብቤአለሁ ለቅሶ ሳቢይ የተፈፀመው ዘርን መሰረት ያደረገው ቄሮዎች ያካሄዱት ጭፍጨፋ በስኬሉና በመጠኑ ወይም ያዳረሰው አካባቢ ስፋትና ቁጥር ከአሁነኛው ያነሰ ነበር። በዚህ በአሁነኛው፣ መንግስትን ከበስተሁዋላው ባደረገ፣ የቄሪዎችና የኦነጎች ጥቃት ወደ 300 ሰዎች ተገድለዋል ቢባልም እውነታውን ፈጣሪ ይወቀው። እንደሚታወቀው መንግስት ከወቀሳ ለመዳን ጥፋቶችንና የሙዋቾችን ቁጥር እጅግ በጣም አሳንሶ እንደሚያወራ ማንም ያውቀዋል። በጀዋር ሳቢያ 80 ሰዎች ተገደሉ የተባለውም የመንግስት ሚዲያዎች በሉ የተባሉት ነው እንጅ በግል ታዛቢዎች የሙዋቾቹ ቁጥር አልተቆጠረም። መንግስትም አይፈቅድም። ቁም ነገሩ የሃገራችን ነገር በየጊዜው እየባሰበት የተገዳዮችም ቁጥር እየጨመረ ነው የሚሄደው እንጅ የተሻለ ጊዜ አይመጣም ። ምክንያቱም አስተዳደሩ የችግሩን መሰረት (Root cause) ሊነካው ፈቃደኛ ስለአይደለ ነው። ያም በብሄርና በቁዋንቁዋ ላይ የመሰረቱት ክልል የሚሉት ሴይጣናዊ መዋቅር ነው። በነገራችን ላይ የፌዴራሊዝምና የኤትኒክ ፌዴራሊዝም ልዩነት ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል ምክንያቱም ሁለቱ ስርአቶች የብርሃንና የጨለማን ያህል ልዩነት አላቸው። በፌዴራሊዝም ስርአት የሴንታራሉ መንግስት ስልጣን ከሁሉ የበላይ ነው። በኢትዮጵያ የምናየው ግን ብሄር ዜግነትን ደፍጥጦት፣ የክልል ስልጣን ከማእከላዊው አስተዳደር ስልጣን መቶ እጥፍ በልጦ ያለበት ሁኔታ ነው። ብሄርና ቁዋንቁዋን ያማከለ ፌዴራሊዝም ግን ለጠላታችንም የማንመኘው መቅሰፍት ነው።

ወደ ዋናው ጉዳዬ ስገባ አሁን እያየነውና እየሰማነው ያለው እልቂት ከበስተሁዋላው የመንግስት እጅ አለበት የምንልበት ምክንያት ህዝቡ ቄሮን ለመመከት በተነሳበት አካባቢ ሁሉ የአቢይ ወታደሮች ከገዳዮቹ ጋር በመተባበትር ወይም ገዳዮቹን በመደገፍ ራሱን ለማዳን የወጣውን ህዝብ ሲያዋክቡ፣ሲደበድቡና ሲያስሩ እንደነበር መረጃዎች በብዛት እየወጡ ነው። ባለፉትም የቄሮዎች ጥቃት የመንግስት ሰራዊቶች ተጠቂዎችን እያሰሩ አጥቂዎችን እያጀቡ ያሉበት የምስልና የድምፅ ማስረጃዎች አሉ። እንግዲህ የመንግስቱ ደጋፊዎች የሆናችሁ ይህንን እንዴት ነው የምትገልፁልን??/መንግስት የዜጎችን ደህንነት መጠበቅና ማስጠበቅ ሲገባው እጆቹን አጣጥፎ እያየ ባለበት ክፉ ሁኔታ ውስጥ፣ ዜጎችም ዝም ብለን የቆንጨራ እራት አንሆንም ብለው ለመከላከል ያላቸውን መሳሪያ ይዘው ሲወጡ፣ የመንግስት ሰራዊት ጥቃት ፈፃሚዎቹን ትቶ ተጠቂዎቹን ማጥቃቱ ከቶ ምን ይባላል????የመንግስት እጅ ባይኖርበትማ ኖሮ ፖሊሱ፣ሚሊሻው፣ልዩ ሃይሉ፣ ባጠቃላይ በመንግስት እዝ ስር ያለው ወደ 500 000 የታጠቀ ሃይል አሽባሪዎቹን በግማሽ ቀን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ የሙዋቾቹን ህይወት ባዳነ ነበር።

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የዶ/ር አቢይ ሃይል የኦነግ፣ የቄሮ፣ የትህነግና የህወሃት ጦሮች ተደምረው እንኩዋን ከሚኖራቸው ሃይል የበለጠ እንደሆነ ነው። በዚያ ላይ ዶ/ር አቢይ የኤርትራው መሪ የኢሳያስ ሙሉ ድጋፍ እንዳለው ይታወቃል። ታዲያ በዚህ ሁሉ አቅም ለምንድነው ዶ/ር አቢይ ህዝቡን የማያድነው? ለምንድነው ገዳዮችን የሚወዳጀው? ለምንድነው የገዳዮችን ቤተሰቦች እግዜር ያፅናችሁ እንኩዋን የማይለው?? ለምሳሌ ያህል ባለፈው በጃዋር ለቅሶ ህዝብን የጨፈጨፉት (አማራውንም፣ ኦሮሞ ኦርቶዶክሶችን፣ ጉራጌውን፣ጋማውን የገደሉት) ገዳዮች ምነው አንዳቸውም ወደፍርድ አልመጡም?? ምነው በግድያቸው አልተጠየቁም? አያችሁ ወገኖቼ ምነው በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሽኝ እንደሚባል ቄሮዎች ገና ከጠዋቱ ከተማ ሲያሸብሩ ቆንጠጥ የሚያደርጋቸው መሪ ቢኖረን ኖሮ ይህንን ያህል ጥፋት ባላመጡ ነበር። በህግ የሚጠይቃቸው ቢኖር አርፈው በሰላም ይቀመጡ ነበር። ነገር ግን እውነት ለመናገር ጠ/ሚኒስትሩ ቄሮንና ኦነግን ካጠቃሁ የኦሮሞዎችን ድምፅ አጥቼ ከስልጣኔ እሰናበታለሁ በሚል ፍራቻ ባይያዝ ኖሮ ሃገሪቱን ከአሸባሪዎች ለማዳን አቅም ባልቸገረው ነበር።

እንደእውነቱ ከሆነ በእኔ ግምት የኢትዮጵያ ነገር አክትሞለታል። ትንቢት ፈጣሪዎቹ የዘመኑ ሃዋሪያትና ነቢያት የሚናገሩትን “የብልፅግና ዘመን ይሆንልናል” “የመጎብኘት ዘመን ፊታችን አለ” የሚሉት ከኪሳቸው የሚተነብዩት ትንቢት አያታላችሁ። ፊታችን ያለው ዘመን የመበታተን፣ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፣ የእሬሳ ክምር፣ የሙሾ አውራጆች ዘመን ነው የሚሆነው። የምናገረው ትንቢት አይደለም፣ ተንባይም ባለራእይም አይደለሁም። መሬት ያሉትን አሰራሮች በማየት ጭንቅላቴን ተጠቅሜ ነው የምናገረው። ኢትዮጵያን የምትቀጥለዋ ዩጎዝላቪያ፣ ሶማልያና ሶሪያ የሚያደርጋት ብቻ ሳይሆን ከዛም በባሰ መልኩ የማንም መሳለቂያ እንድትሆን የሚያደርጋት ዘመን በደጅ ነው። ዶ/ር አቢይ የብሄርና የቁዋንቁዋን ድንበር እስካልገረሰሰ ድረስ፣ በአማራው ላይ የተጣለው ቅጥ ያጣ ጥላቻ ውንጀላና ግድያ እስካልቆመ ድረስ፣ ሃገሪቱዋ የእልቂት ቀጠና ነው የምትሆነው። ምክንያቱም አማራውና ጉራጌው፣ጋሞው ወዘተ የቄሮዎችን የኦነጎችንና የህወሃትን ጥይት ፣ሜንጫና ገጀራ ተንጋለው የሚቀበሉበት ጊዜ ማክተሚያው ሩቅ አይደለም። እነኝህ የጥቃት ታርጌቶች በተለይም አማራው፣ ብረትን በብረት፣ ሜንጫን በሜንጫ፣ ዱላን በዱላ እንዲመክቱ የሚያስገድዳቸው መገፋትና ጥቃት መፍለቅለቂያው ግለት ላይ ደርሶአል። ይህ እንዳይሆን መንግስት ከወንጀለኞች ጋር ማበሩን ትቶ ሃይሉን ተጠቅሞ ፀጥታን ያስከብር።

ዶ/ር አቢይ በእጅህ ያለውን ሃይል ተጠቀምበት አለበለዛ ህዝቡም ሃገሪቱዋም አንተም በፊታችሁ ቀና ጊዜ አይሆንላችሁም!!!!!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator