0 0
Read Time:1 Minute, 54 Second

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ማይካድራ አካባቢ የወራሪው ትሕነግ የሽብር ቡድን ባለሃብቶችን ለማፈንና ለመዝረፍ ያደረገው ሙከራ መክሸፉ ተገልጧል።

የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው በበኩላቸው “ጠርጥሩ፣ ወጥሩ፣ መንጥሩ” እንዲሁም “ጠላት ሊገባ ይችላል፤ ግን በእርግጠኝነት አይወጣም!” የሚለው መርሃችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ነቅቶ አካባቢውን እየጠበቀ ያለው የተባበረው የወገን ጦር በርካታ የሽብር ቡድኑን አባላት ሙት እና ቁስለኛ አድርጓል፤ የተማረከ እንዳለም ለማወቅ ተችሏል።

ማይካድራ ላይ በትንሹ ከ1,600 በላይ በሚሆኑ ወገኖቻችን ላይ አሰቃቂ ግድያ የፈጸመው ተስፋ ቆራጩ የሳምረ ቡድን በወረራ ሰፊ የኢትዮጵያዊያንን መሬት በያዘችው ሱዳን ተጠግቶ እየሰለጠነ፣ በተለያዩ ጊዜያት በክህደት ጠላትን እየመራ እና እየወረረ አይቀጡ ቅጣት እየተቀጣ መመለሱ ይታወቃል።

ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ በሽንፋ በኩል ከወራት በፊት ወረራ የሞከረው አሸባሪው ትሕነግና ከሃዲውና ዘራፊው የቅማንት ኮሚቴ ቡድን በፋኖ፣በሚሊሻው፣ በልዩ ኃይሉና በመከላከያ ሰራዊት ከባድ ምት ሰዋዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ የገጠመው መሆኑን ማስታወስ በቂ ነው።

በተመሳሳይ ለበርካታ ጊዜ የማጥቃት ሙከራ አድርጎ በጀግኖች እርኩስ አላማው የከሸፈበት የሽብር ቡድኑ ታህሳስ 14 ቀን 2014 በማይካድራ ከበረከት አለፍ ብሎ አላው በሚባል አካባቢ አፈና እና ዘረፋ ለመፈጸም ሞክሮ አላማው የከሸፈበት መሆኑ ተገልጧል።

ባለሃብቶች እነ ማማይ እና ብርሃኑ አቡሃይ ታፍነዋል መባሉን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ መከላከያ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት በእለተ ሀሙስ ታህሳስ 14 ቀን 2014 ከጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ ለሰዓታት የቆዬ የተኩስ ልውውጥ በማድረግ ወራሪውን አይቀጡ ቅጣት መቅጣታቸው ተሰምቷል።

ከመጣው ወራሪ እና ዘራፊ ኃይል መካከል በጀግኖቹ አማካኝነት በርካታ ሙት እና ቁስለኛ ሲደረግ የተማረከ መኖሩና ጥቂት እድለኞችም ሮጠው ማምለጣቸው ተሰምቷል።

ከወገን ጦር አዛናው የተባለ ጀግና ተሰውቶ አስከሬኑ ወደ ምድረ ገነት ተወስዶ ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙ ተሰምቷል፤ ከ4 የማያንሱ መቁሰላቸውና የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑ ተነግሯል።

በያዝነው ታህሳስ ወር 2014 አቶ ሻረው የተባሉ የወልቃይት ጠገዴ ባለሃብት በማይካድራ አለው በሚባል አካባቢ ከነበራቸው 200 ሄክታር የማሽላ ልማት መካከል አንድ ኩንታል እንኳ ለመሰብሰብ ሳይችሉ ጁንታው ዘርፎ ባሰማራቸው የቀንድ ከብቶች እንዲወድም መደረጉም ተገልጧል።

አሚማ ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ከሆኑት ከአቶ አሸተ ደምለው ጋር ካደረገው አጭር ቆይታ እንደተረዳው የሽብር ቡድኑ ክፉ የወረራ እና የዝርፊያ አላማ እየከሸፈበት ነው፤ ጠንካራ አደረጃጀት ተፈጥሮ ጁንታውን ለመቅበርም እየተሰራ ነው።

አቶ አሸተ እንዳሉት “ጠርጥሩ፣ ወጥሩ፣ መንጥሩ” እንዲሁም “ጠላት ሊገባ ይችላል፤ ግን በእርግጠኝነት አይወጣም!” የሚለው መርሃቸው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

መንግስት የትሕነግ የሽብር ቡድን ያሰማራው ሳምረ የተባለው ጨካኝ ገዳይ ቡድን እንደ ስደተኛ ከተጠጋበት ሱዳን ተይዞ ለህግ ይቀርብ ዘንድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ በተደጋጋሚ ጥሪ መደረጉ ይታወሳል።

የሽብር ቡድኑ ማይካድራ ላይ ጥቅምት 30 ቀን 2013 የፈፀመው የዘር ፍጅት ታሪክ የማይረሳው ጥቁር ጠባሳ ሲሆን ገዳዮች በአለም አቀፍ የወንጀል ህግ እንዲጠየቁ ያላሰለሰ ትግል መደረግ እንዳለበት ብዙዎች ይናገራሉ።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator