መረጃ
የስንታየሁ ጠያቂ ሽባባው ዘውዱ ለአንድ ቀን ታስሮ ተፈታ!!
/
ከአለፍው ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በባሕር ዳር ፖሊስ መምሪያ 1ኛ ፖሊስ ጣቢያ በግፍ እስር ላይ የሚገኘው ስንታየሁ ቸኮል፣ አካልን ነፃ የማውጣት ክስ መመስረቱን ተከትሎ የባሕር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት ፖሊስ ስንታየሁን ይዞ ችሎት እንዲቀርብ የላከው ትዕዛዝ ሳይፈፀም ቀርቷል።
ፖሊስ ትዕዛዙን አልቀበል በማለቱ ነው የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ውድቅ የተደረገው። ፖሊስ በትዕዛዙ መሰረት የማይገኝ ከሆነ፣ ጉዳዩን በሌለበት እንደሚያየውም ፍርድ ቤቱ በማዘዣ ደብዳቤው ገልጾ ነበር። ይሁን እንጂ፣ ስንታየሁ ከታሰረበት ዕለት አንስቶ እስከዛሬ ድረስ አንድም ግዜ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ አሁንም በእስር ላይ ይገኛል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የባሕር ዳር ፖሊስ “ስንታየሁን ይደግፋሉ” ያላቸውን ሦስት የጣቢያው የፖሊስ አባላት ለቀናት አስሮ አሰናብቷል። ፖሊሶቹ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ለእያንዳዳቸው በሦስት ሺህ ብር ዋስትና ከእስር ተፈተዋል።
በተመሳሳይ፣ ስንታየሁን ፖሊስ ጣቢያ ተመላልሶ እየጠየቀ ያለው የባልደራሱ ሽባባው ዘውዱ ከትናንት በስቲያ ታስሮ ከአንድ ቀን አዳር በኋላ ተፈቷል።
‘እገድልሃለሁ’ የሚል ዛቻን ጨምሮ፣ በርካታ የመብት ጥሰቶች በስንታየሁ ቸኮል ላይ እየተፈፀሙበ ይገኛሉ።
/