0 0
Read Time:1 Minute, 15 Second

“ፋኖ መከላከያ ሰራዊትን እየገደለ ትጥቅ እንደሚታጠቅ የቀረበው ንግርት ሀሰት ነው፤ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር መልካም የሆነ ቅንጅት እንዳይኖረን ማድረጉም ለሀገር አይጠቅምም” ሲል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር አወገዘ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሰኔ 9 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ጠሚ አብይ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት በፋኖ ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ በሚከተለው መልኩ አውግዟል:_

ፋኖ የክብር ስም ነው በጣም እንጂ !! ፋኖ ለአማራ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ትልቅ ኮራት ነው ሆኖማ ኢትዮጵያን ከመፍረስ አድኗል።

ፋኖ በጀግንነት ተዋግቷል!! አሁንም እየተዋጋ ነው!! ነገም ለህዝብና ለአገራችን ሲል ከጠላት ጋር ይዋጋል የአደባባይ ሃቅ ነው።

ትናንት ፓርላማ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ለፓርላማ አባላት ከሰጡት ማብራሪያ ውስጥ ፋኖ መከላከያ ሰራዊትን እየገደለ ትጥቅ እንደሚታጠቅ የቀረበው ንግርት ሀሰት ነው።

ቀዩን ጥቁሩን መሳሪያ ፋኖ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እጅ ወስዶ አያውቅም። ይህ እንደቀላል ሊታይ አይገባም።

ምክንያቱም በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ መሪ የነበሩት መለስ ዜናዊ በስልጣን ዘመናቸው ከሰሩት እኩይ ተግባር መካከል በሀሰት ትርክት አማራው የኦሮሞ እናቶችን ጡት ቆራጭ እንደሆነ ማስረዳት የሚችል የአኖሌ ሃውልት ተሰርቶ ቋሚ የጠብ አጫሪ መሳሪያ ተደርጎ መወሰዱ ነው።

ፋኖ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጋር ከአንድ ምሽግ አብሮ በርሃብ አለንጋ የተገረፈ፣በዝናብ ፣በብርድ ቆፈን የተሰቃየ፣በጠላት ጥይት አብሮ መስዋትነትን የተቀበለ፣የትግል ጓድ ሆኖ ደጀንነቱን በአስተማማኝ ሁኔታ የተወጣ እንጂ ጠቅላዩ እንዳሉት ብልሹ ስነምግባር የታየበት ፋኖ የለነም። ወደ ፊትም ሊኖረን አይችልም።

ፋኖ ዉሃ የተጠማን መከላከያ ሰራዊት ውሃ ያጠጣል፣የተራበን ሰራዊት ምግብ ይመግባል፣የቆሰለን ሰራዊት አቅፎ ደግፎ ወደ ህክምና ያደርሳል፣የተሰዋን ሰራዊት በክብር ይቀብራል እንጂ ፖለቲከኞች ለፖለቲካዊ ትርፍ ሲባል ስማችን ለማጠልሸት የሄዱበት እርቀት ፈፅሞ ከእውነት ያረቀ መሆኑን እራሱ መከላከያ ሰራዊቱ ይረዳዋል።

ለማንኛውም ከመከላከያ ሰራዊት ጋር መልካም የሆነ ቅንጅት እንዳይኖረን ማድረጉ ለሀገር አይጠቅምም!!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator