0 0
Read Time:1 Minute, 52 Second

የሰኔ 15 ጉዳይ የብአዴን በብአዴን የሆነ የውርድደታቸው መገለጫ ነው የራሳቸውን እሳት ራሳቸው ይሙቁት ብለን ስለጉዳዩ ብዙ ማለት አልፈለግነም ነበር። የእኛ ዋነኛ ትኩረት የብአዴኑ ቀውስ ወደ ህዝባችን እንዳይጋባ ህዝባችንን የማንቃትና የተለያዩ የአማራን ድል የሚያፋጥኑ አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ ነበር ነውም።

በአማራ ጠልነት በተረቀቅው ሕግ በአማራ ጠልነት የቆመው ሥርዓት ላላፉት ሦስት አሥርት ዓመታት የተለያዩ አዋጆችንና ሕጎችን እያወጣ አማራን ለመጨቆን ይጠቀም ነበር እየተጠቀመም ነው።

ከብዙዎቹ ውስጥ ብዙ የአማራ ወጣቶች ለመሰዋዕትነት ለእንግልት የተዳረጉበት አዋጅ” ፀረ ሽብር ” ብለው አውጥተው የተገበሩት ነው። ፀረ ሽብር አዋጁ አማራን ለማሸበር የረቀቀና የተተገበረ ስለመሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ሥርዓቱ ራሱ አሸባሪ በመሆኑ ፀረ ሽብር አዋጁ ሊፈፅምበት የሚገባው ራሱ ላይ ቢሆንም ፍትኅ የአምባገነኖች እስረኛ ሆና ንፁሃን የአማራ ልጆች ዋጋ ሲከፍሉበት ቆይተዋል።

ሰኔ 15 እንደ አማራ ብዙ ዋጋ ያስከፈልን ስለመሆኑ ሁሉም የሚረዳው ነው። ሥርዓቱ ተቋሞቼ ናቸው በሚላቸው የማጣራት ሥራ ሠርቺያለሁ በማለት የምርመራ መዝገቦቹ በክልልና በፌድራል ተከፍተው መሠራቱን በተደጋጋሚ ይገልፅ ነበር። የምርመራ መዝገቡን መሠረት አድርጎም በክልልና በፌድራል ክስ መሥርቺያለሁ በማለት በአደባባይ መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል።

ብአዴን ሰኔ 15 ን ፍትኅ ከማስከበር ይልቅ ለፖለቲካ መጠቀሚያ እያደረገው እንደሆነ ይሰማኛል።በአማራ ፖለቲካ ውስጥ ፀረ ብአዴንነት አቋም ያራምዱ የነበሩ ተጠርጣሪ ተደርገው ለወራት በእስር ቆይተው ነፃ ናችሁ ተብለው መፈታታቸው ይታወቃል።

የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ እስር ጉዳይም ከፖለቲካዊ ፍላጎትነት የተለየ ሆኖ እየታየኝ አይደለም።ሰኔ 15 ን እንደ ፀረ ሽብር አዋጅ የመጠቀም ዝንባሌ ከጊዜ ወደ ጊዜ ታቅዶበት እየተሠራ እንደሆነ ብዙ ማሳያዎችን መጥቅስ ይቻላል። ብአዴን ከራሱ ፖለቲካዊ ፍላጎት በተቃራኒ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲከኞችን፡አክቲቪስቶችን፡ታጋዮችን/ፋኖዎችን እና ሌሎችንም የትግሉ ባለድርሻዎች በሰኔ 15 ጠርጥሬያቸዋለሁ እያለ አዳዲስ የምርመራ መዝገቦችን መክፈቱ የዚሁ መገለጫ ተደርጎ የሚወሰድ ሆኖ አግንቼዋለሁ። ሰኔ 15 ን እንደ ፀረ ሽብር አዋጅ መጠቀም የፍትኅ ማስከበር ጉዳይ ሳይሆን ፤አጋጣሚዎችን ሁሉ አማራን ለመጨቆኛነት የመጠቀም የቆየ አስተሳሰባቸውና መገለጫቸው ነው።

ሰኔ 15 ን በተመለከተ እውነቱ ይውጣ የሚሉ ጩኸቶች ተበራክተው ዓመት አሳልፈናል። እውነትማ ለምን ይደበቃል ይውጣ እንጂ። ነገር ግን ሰኔ 15 እና ተያያዥ ጉዳዮች ለምን እንዴት በማን የሚለው በገለልተኛ አካል ተጣርቶ ማንም ሆነ ማን የሕግም ሆነ በሞራል ተጠየቅ ውስጥ እንዲገባ እስካልተሠራ ድረስ፤የብአዴን ቅጥፈት እውነት ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም።
መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ሰኔ 15 ን እንደ ፀረ ሽብር አዋጅ ለመጠቀም በሚደረገው ፖለቲካዊ ሴራ ሰለባ እየሆነ ስለመሆኑ የዛሬውን ችሎት በተመለከተ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ያረጋግጣሉ።የማስሬ ጉዳይ በመላ አማራነት ማዕቀፍ ታይቶ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል።ሲታገል በአማራነት ለአማራነት ዋጋ ሲከፍል ለብቻው የሚሆንበት ሂደት የአማራን ሁለንተናዊ መፃኢ ትግል እጅጉን የሚጎዳ ነው። መላው የአማራ ብሔርተኛና ታጋይ ማስረሻ ነፃ ከሆነ በሀቅ የተመሠረተ ፍትኅ ተከብሮለት ነፃነቱ ይረጋገጥለት የማለት ሞራላዊም አማራዊም ግዴታ አለበት።

ሻማል ዳዊት

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator