0 0
Read Time:3 Minute, 46 Second

ከአማራ ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም የተላለፈ የአቋም መግለጫ።

      Email:[email protected]

      www.amhcouk@org

አለም በኮሮና ቫይረስ ጭንቀት ውስጥ ወድቆ በሚገኝበት ሰአት፤ ፤ግለሰቦች፤ድርጅቶችና መንግሥታት በመካከላቸው ያለውን ችግር ወደኋላ በመተው፤ ህዝባቸውን ከዝህ አስከፊ ወረራ ለማዳን እየተረባረቡ በሚገኙበት ሰአት ብአዴን(አዴፓ) ፤ፋኖን የማጥፋት፣/የማስጠፋት/ ዘመቻ የጀመርበት/ያስጀመረበት/ ፤አማራ የህልውና አደጋው ከግዜ ግዜ አየከፋበት እንደመጣ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ አለመኖሩን ነው። ፋኖ አማራን ከጅብ ጅቦች እየተከላከለ ያቆየና ወደፊትም የአማራን ሕልውና ጠባቂ ነው። በዚህ ሰዓት፣ ዐማራው የታፈኑ ልጆቼ ይመለሱ ብሎ ጥያቄ አቅርቦ መልስ እንዲሰጠው እስካሁንም ድረስ በመጠባበቅ ላይ እያለ፣ ዐማራው በተለያየ አቅጣጫ የጥፋት ድግስ እየተደገሰለት ሰላም ማጣቱ እና በፈለገው መልክ ተደራጅቶ ሃሳቡን በሰላም እንዲገልፅ በሚሰሩት ላይ የሚደርሰው እንግልትና ወከባ የአደባባይ እውነት ነው።

‘ብአዴን’ የሚል ስም በመለስ ዜናዊ ወጥቶለት የዐማራን ሕዝብ ዘላለማዊ ዕረፍት እንዲነሳ በዐማራ ላይ የተጫነው የዐማራ ጠል ተላላኪ ቡድን፡ ዛሬም በአዲሶቹ ጌቶቹ አዴፓ ከዚያም ‘ብልጽግና’ በሚል ስያሜ የተላላኪነት ስራውን በመቀጠል ከመጋቢት መግቢያ ጀምሮ በዐማራ ፋኖ ላይ ግልጽ ጦርነት አውጇል።

ዐማራን ትጥቅ ለማስፈታት ፋኖን መምታት በሚል ብአዴን ከኦዴፓ/ኦነግ መንግስት ጋር እየሰሩት ያለው ጥቃት ዐማራው በከፍተኛ ሁኔታ ሰላሙን እንዲያጣና መረጋጋት እንዳይኖረው ለማድረግ ነው። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ክልሉም ሆነ ዐማራነት ከፍተኛ የህልውና ፈተና ውስጥ በወደቁበት ወቅት ጦር አሰማርቶ ፋኖን ለማጥፋት መሞከር ወደ ባሰ ችግር እንድንገባ የታቀደ መሆኑ በግልፅ ይታያል። ብአዴንም መቼም የማይለወጥ የዐማራነት ጠላት መሆኑን አረጋግጦአል።

የፋኖ ትግል አሁን ስልጣን ላይ ያሉትን መሪዎች ወደ ስልጣን እንዲመጡ ወያኔን በማንበርከክ ለውጡን እንዳፋጠነ ይታወቃል። ህይወት የተገበረበት የፋኖ ትግል ሽልማት ሲገባው ተክዶ ጦር ተሰብቆበታል።
በዳባት በተቃጣው ጥቃት በፋኖዎች ራስን የመከላከል እርምጃ ቢከሽፍም በጎንደር በሰላማዊ መንገድ ጥቃቱን ለመቃወም ባዶ እጃቸውን አደባባይ በወጡ ወጣቶች ላይ በኦነግና በወያኔ ገዳዮች በ’መከላከያ’ ስም በከባድ መሳሪያ ተኩስ ከፍተው ሦስት ወጣቶቾን ገድለው አራቱን አቁስለዋል።

ቀድሞ የወያኔ አሁን የአብይ/የኦነግ ተላላኪ የሆነው የብአዴን የጎንደር አስተዳደርም ፋኖ እስከ መጋቢት ሀያ መሣሪያውን እንዲያስረክብና እጁን እንዲሰጥ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ይህንንም ለማስፈጸም ኦሮሚያ ተብሎ በሚጠራው ክልል የሰለጠነና የወያኔ ጥምር ጦር በ’መከላከያ ‘ ሽፋን አብዛኛው ጎንደር ገብቷል።

የዓለም መንግሥታት የኮሮናን ወረርሽኝ ለመግታትና ሕዝባቸውን ከዚህ መቅሰፍት ለማትረፍ ሁሉንም እንቅስቃሴ ዘግተው ሀብት ንብረታቸውን ሕይወት ለማትረፍ እየተጠቀሙ ባሉበት ወቅት አብይ አህመድና የብአዴን ቅጥረኛች ወደ ሀምሳ ሺህ የሚጠጋ ገዳይ ሰራዊት ዐማራው ላይ አዝምተዋል።

የእሩቁን ትተን ከ2008 ዓ ም ጀምሮ በዐማራው አካባቢ ከወያኔ ነፍሰገዳዮች ጋር በተደረገው ትንቅንቅ ጠላት ጥለው በመውደቅ ዛሬ ለደረስንበት የተስፋ ጭላንጭል ያበቁን የዐማራ ፋኖ አርበኞች ናቸው። ፋኖ የዐማራነት ትልቁ እሴት ሲሆን ሁሉም ዐማራ በሰላም ጊዜ አርሶአደር በክፉ ግዜ አርበኛ ነው። ፋኖን ማጥቃት ዐማራነትን ማጥቃት ነው።

በጎንደር የተቀጣጠለውን የአማራ የሕልውና ትግል ለማዳፈን በጎንደር በባህርዳርና በሌሎች አካባቢዎች የተፈጸመውን ጭፍጨፋ ተከትሎ እንደ አርበኛው ጎቤ ያሉ በሺዎች የሚቆጠሩ ፋኖዎች የሞቀ ቤታቸውንና የሚወዱትን ቤተሰብ ትተው ዱር ቤቴ ብለው ወያኔን ከዐማራው ጫንቃ ላይ አውርደው በጀግንነት ወድቀዋል ።

ተረኛው የአብይ አህመድ ጽንፈኛ የኦሮሞ ቡድን ገና ወደ ሥልጣን እንደመጣ የዐማራውን የሕልውና ትግል ለማኮላሸት ዕቅድ አውጥቶ በረቀቀ ሴራ አማራን የመሪ አልባ የማድረግ ዘመቻውን ቀጥሎበታል። በሰኔ 15ቱ ከፍተኛ የአማራ መሪወችና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ጀነራሎች ግድያ የጅምሩ ማሳያ ሲሆን የጀነራል አሳምነው ግድያ የዚህ ዕቅድ ዋናው አካል ነው። ጀነራል አሳምነው ጽጌ ዐማራው ላይ ያንጃበበው አደጋ የገባው ብቸኛ ዐማራ ነበር። ተከበናል ሲል ማንም አልተረዳውም። የዐማራን የጸጥታ ኃይል አደራጅቶ ፋኖን አቀናጅቶ ዐማራው ላይ የተቃጣውን ጥቃት በመመከቱ ነው የገደሉት። በአጣዬ በከሚሴ በመተከል ላይ በዐማራ ወገኑ ላይ የተከፈተውን ጥቃት የመከተውና ድባቅ የመታው በጀነራል አሳምነው መሪነት የዐማራ ፋኖ ነው። የዐማራ ፋኖ በሰላም ጊዜ አርሶ አደር በክፉ ቀን ወታደር ሆኖ ለሺህ አመታት የኖረ የወገኑ ጠባቂ ነው። በራሱ ስንቅና ትጥቅ ወገን ሲደፈር ሀገር ሲወረር ዘምቶ ወገን ያኮራ ሀገር ያስከበረ በወርቅ ቀለም የተጻፈ ደማቅ ታራክ ያለው ነው። ከከሀዲና ከባንዳው በቀር ሁሉም ዐማራ ፋኖ ነው። ለዚህም ነው አሁን ፋኖ ላይ የታወጀው ዘመቻ በሁሉም ዐማራ ላይ የታወጀ ጦርነት ነው የምንለው። ፋኖን ለማጥፋት የታቀደው ዐማራውን ጠባቂ ለማሳጣትና ባለፈው 30 ዓመታት በላይ ሲያደርጉ እንደኖሩት ዐማራውን በተናጠል ከየቤቱ እየጎተቱ ለመግደል፣ ለማሰር፣ ለማፈናቀል እና ለማሳደድና በአጠቃላይ ለጅብጅቦች አሳልፎ ለመስጠት ነው።

አብይ አህመድ በራሱ የኦሮሞ ጽንፈኞች የታገቱ 17 የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ የዐማራ ተማሪዎችን አብዛኛዎቹ ሴቶች ጦር ልኮ ማስለቀቅ ሲገባው ወላጆቻቸው ደብቀዋቸው ነው እያሉ የሚያላግጡት ፅንፈኞች ደጋፊነቱን በግልጥ እያሳየ ነው። ። የታገቱ ተማሪዎችን ለማስለቀቅ ያላሰማራውንና የሱዳን ድምበር ሲወረር የተደበቀውን ጦር በህግ አስከባሪ ስም ፋኖና ዐማራ ሕዝብ ላይ ያዘምታል። የታጋቱ ልጆችን ቤተሰብ እያሳደደ ያስራል። ይህ የሚያሳየው በዐማራ ላይ ያለውን የጥላቻ ጥልቀት ነው።

የአማራ ማህበር በእንግሊዝ/ ዩናይትድ ኪንግደም በፋኖዎቻችን ላይና ብሎም በያንዳንዱ ዐማራ ላይ የታወጀውን ዘመቻ በጽኑ ይቃወማል፤ ያወግዛል። ከፋኖና ከዐማራው ወገናችን ጎን በጽናት እንደሚቆም ያረጋግጣል።

የኦዴፓ/ኦነግ መንግስትና ተላላኪው ብአዴን በፋኖና ዐማራ ላይ የላኩትን የጥፋት ጦር ወደ መጣበት እንዲመልሱ ጥሪ ያቀርባል።

ዛሬ ፋኖ ላይ የተከፈተው ዘመቻ ነገ ለዐማራው በቆሙ አደረጃጀቶች ላይ መቀጠሉ ስለማይቀር ለዐማራው ሕዝብ ቆመናል የምትሉ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያላችሁ ድርጅቶችና ስብስቦች ብትችሉ በአንድነት ባትችሉ በተናጠል ፋኖ ላይ የተከፈተውን የማጥፋት ዘመቻ እንድታወግዙና ከፋኖና ከዐማራው ሕዝብ ጎን በቃልም በተግባርም እንድትቆሙ እንጠይቃለን።

እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ያላችሁ የመገናኛ ብዙኃንና የሚዲያ ባለሙያዎች ለእውነት እንድትቆሙና ለተገፋ ህዝብ ድምፅ እንድትሆኑ ጥሪ እናስተላልፋለን።

ከባንዳ በስተቀር ሁሉም ዐማራ ፋኖ ነው!
እኛም ፋኖዎች ነን!
ዐማራ በረጅሙ ድል ያደርጋል!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator