አንጋፋው የታሪክ ምሁር፣ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ታዲዮስ ታንቱ ግንቦት 10/2014 ወደ አራት ኪሎ በወጡበት ምሽት ላይ በመኖሪያ ቤታቸው አካባቢ እንደደረሱ ታፍነው ወደ 3ተኛ (ማዕከላዊ) መወሰዳቸውን ባለቤቱ ወ/ሮ ጸጋ ሞገስ አረጋግጠዋል።

ሙሉ ሌሊቱን አድራሻቸው ሳይታወቅ በጭንቀት ማደራቸውን ገልጸዋል።

ግንቦት 11/2014 ከቀኑ 5 ሰዓት ላይ ግን የመኖሪያ ቤታቸው መፈተሹንና ምንም ዓይነት ሰነድ አለመገኘቱን ወ/ሮ ጸጋ ተናግረዋል።

ግንቦት 12/2014 በአራዳ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ለአሚማ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ግንቦት 8/2014 ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ሳር ቤት አካባቢ ታፍነው ደብዛቸው የጠፉት የብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ አድራሻ ታውቋል፤ በባህር ዳር ቀበሌ 14 በ9ነኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ።

ጄኔራሉ ግንቦት 8/2014 ቦሌ ማግኖሊያ ሆቴል ከአቶ ዮሃንስ ቧያሌው ጋር ተገናኝተው ሲጫወቱ ቆይተው ከቀኑ 9:30 የራሳቸውን መኪና በማሽከርከር እየተጓዙ በነበሩበት ሳር ቤት አካባቢ መታፈናቸው የሚታወስ ነው።

በአያያዝ ወቅትም “ገጭተህናል” በሚል በውሸት በቀኝ እና በግራ የመጡ የተደራጁ አካላት ከፊታቸው መኪና በማቆም ወከባ ሲፈጥሩባቸው መቼ እና የት ነው? የገጨኋችሁ በሚል ወርደው ለማነጋገር ሲሞክሩ በፓትሮል የመጡ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ድብደባ እንደፈጸሙባቸው ተገልጧል።

ግንባራቸው አካባቢ የተመቱትም አሁንም ድረስ እብጠት እንደሚታይበት ከቤተሰብ የተገኘ መረጃ አመልክተል።

ወደ ባ/ዳር በአውሮፕላን ከወሰዱ በኋላ በ9ነኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት ጄኔራል ተፈራ ምግብ እንኳ በአግባቡ እንዳልቀረበላቸው ለማወቅ ተችሏል።

ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ በተረጠሩበት የዋስትና ጥያቄ ወንጀል ጉዳይ ፖሊስ ግንቦት 12/ 2014 ወደ ችሎት እንዲያቀርባቸው የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት መደበኛ ወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቷል።

እስካሁን ድረስም የተወሰደባቸውን መኪና ለማግኘት እንዳልተቻለ ምንጫችን ገልጸዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator