0 0
Read Time:44 Second

ጋዜጠኛ ሰለሞን ሸሙዬ እና ትህትና (ቲና) በላይ ታሰሩ !!

/
ወልድያ ከተማ አዳጎ አደባባይ የሚገኘው የምስራቅ አማራ ፋኖ ሎጅስቲክ ካምፓፕ በአድማ ብተና ፖሊስና በሀገር መከላከያ ሰራዊት ተከቧል።

የምሥራቅ አማራ ፋኖ በአወጣው መግለጫ፣ “በህልዉና ትግሉ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ ከአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ጎን በመሰለፍ ታላቅ መስዋዕትነት በመክፈል አገራችንን ከመፍረስ ታድገናል።

በአሁኑ ጊዜም ራያ ግንባር ጎለሻ እና አዲስ ቅኝ ከወራሪ ሃይል ጋር ተፋጠን ምሽግ ላይ እንገኛለን። ምሽግ ላለው ሰራዊታችን የሚሆን ቀለብ የምናከማችበትን ወራሪ ሃይል አባል የሆነ ህንጻ ካለቀቃችሁ በሚል ሰበብ እኛን የማፍረስ ተግባር እየተፈጸመብን ይገኛል።

ከ 130 በላይ ቁስለኛ እና ከ 80 በላይ መስዋዕትነት የከፈሉ ጓዶቻችንን አደራ እና ቤተሰቦቻቸዉን ይዘን ባለንበት በአሁኑ ጊዜ፣ አባላቶቻችን ላይ ወከባ ከበባ አፈናና እስራት እየተካሄደብን ይገኛል። ይሄ ድርጊት በተዘዋዋሪ ፋኖን የማፍረስ ብሎም አማራን አንገት የማስደፋት እና ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የመንፈግ ተግባር መሆኑን ሁሉም የአማራ ህዝብ ሊገነዘበው ይገባል” በማለት አሳስቧል።

ይህ በእንዲህ እያለ፣ በአዲስ አበባ ጋዜጠኛ ሰለሞን ሸሙዬ እና በባህር ዳር አክትቪስት ትህትና (ቲና) በላይ ዛሬ ታስረዋል።
/

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Translator