ከአቶ ጣሂር ሙሐመድ የአብን ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጋር – ” የአብን እንቅስቃሴ እና በወቅታዊ የዐማራ ህልውና ጉዳይ ” ላይ ያተኮረ እና ሌሎችንም የዳሰስንበት በጥያቄ መልክ ውይይት አድርገናል። ከትንላአንት እስከ ዛሬ በዐማራው ህዝብ ላይ የዘር ጭፍጨፋ ተፈፅሞበታል። የነገው የከፋ መሆኑን በግልፅ የሚያሳዩን ነገሮች በርካታ ናቸው። አንገቱ ተቀልቷል ፣ ውጣ ተብሏል ፣ ተሳዷል ፣ ንብረት ወድሞበታል ፣ ነፍሰጡር ሆዳቸው ተቀዷል፣ በፍትህ አልባ ጉዞ እየኖረ ነው። መፍትሄ እሲመጣ ሁልጊዜም የምናነሳው ጉዳይ ነው። ማማ የውይይት መድረክ የዐማራውን ህዝብ ወደ ከፍታ ማምጣት እና እራሱንም ፣ አገሩንም ከአጥፊዎች መከላከል የሚችልበት ቁመና ኖሮት ኢትዮጵያን ሰላም ማድረግ በሚቻልበት መንገድ ላይ እንዲሰለፍ አስተዋጽዖ ማድረግ ነው ። የማማ ውይይት ይደርሶ ዘንድ ሸር ሊክ ወይም ተከታይ የሚለውን ይጫኑ ። ተሳታፊ ይሆኑዘድ የሁልጊዜ ግብዣችን ነው።