ዴቭ ዳዊት።

የሰርቢያ ልሂቃን፥ ሰርቢያንና ሰርብነትን መስዋዕት አድርገን ዩጎዝላቭያን እንገነባለን የሚል ከንቱ ቅዠት ነበራቸው።

የድንዛዜያቸውና የአጉል ቅዠታቸው ልክ ወሰን ከማጣቱ የተነሳ፥ በ1974 በፀደቀው የዩጎዝላቪያ ህገመንግስት ላይ፥ ከሌሎች ግዛቶች በተለየ ሁኔታ ልክ እንደዛሬው “የአማራ ክልል” የሰርቢያን ግዛታዊ አንድነት አደጋ ላይ በሚጥል ደረጃ ሰርቢያን በ internally imposed federation (ቮይቮዲና፣ Serbia proper እና ኮሶቮ) በሚል ሸነሸኗት። እነ ክሮሽያና ቀሪ ግዛቶች ግን እንደ ትግራይና ኦሮሚያ ክልሎች የግዛት አንድነታቸው ላይ አደጋ የማይጥል ህገመንግስታዊ አሰራር አሰፈኑ። (የሰርቢያን ግዛታዊ አንድነት አደጋ ውስጥ የከተተው የዩጎዝላቪያ ህገመንግስት ሲሆን፥ በአንፃሩ አሁን “የአማራ ክልል” የሚባለውን ግዛት territorial integrity ዘግናኝ አደጋ ውስጥ የከተተው ብአዴን “በ1992 ተሻሽሎ የወጣው የአማራ ብሔራዊ ክልል ህገመንግስት” በሚለው ክልላዊ ህገመንግስቱ ነው‼‼‼ ሲቀጥል የአማራን ታሪካዊ ግዛቶች አንድነት በማሳጣትና በመንጠቅ ረገድ የሀገሪቱ ህገመንግስት ተብዬው ነገር የተጫወተው ሚናም ዋነኛው ነው። አሳዛኙ ነገር፥ የሀገሪቱን ህገመንግስት ሳናስለውጥ እንቅልፍ የለንም ሲሉን የነበሩ ሁሉ፥ “ለህገመንግስቱ ታማኝ ነኝ” በማለት እጃቸውን በዚያ የጥፋት ሰነድ ላይ በመጫን ትርፍራፊ ሹመት ሲያገኙ ታዝበናል። አሁን ያለው “የአማራ ክልል” እንኳ ግዛታዊ አንድነቱን አስጠብቆ እንዳይቀጥል፥ ጠላት-ብአዴን በ1992 “አሻሽዬ አወጣሁት” ያለውን የአማራን ቀሪ ርስት የሚበታትን “ክልላዊ ህገመንግስት” እንዲያሻሽሉት ወይም እንዲለውጡት መጮህ ከጀመርን ድፍን አራት አመት ቢሞላንም ህዝቡም ልሂቁም ከመብላት፣ መራባትና መዳራት በዘለለ የተሰነቀለት ጥፋት ላይ በትኩረት መረባረብን የሚሸሽ ሆኗል። ቤቱን አፅድቶ ክፍተቱን ሞልቶ ወደቀጣይ ምዕራፍ ከመሸጋገር ይልቅ፥ ጥፋትን በጫንቃው ያመጣበትን ብአዴንን እንደ የስዕለት ልጅ ሲንከባብ፣ የእሱ መንደር ብአዴናዊ ከሌላኛው መንደር ብአዴናዊ ይልቅ ፃድቅ መሆኑን ለማሳየት ጉልበት፣ ጊዜና አቅሙን ሲጨርስ ይውላል።)

  • ተመፃዳቂው፣ ሆዳሙና ቅዠታሙ የሰርቢያ ልሂቅ፥ የዩጎዝላቪያ ህገ-መንግስት ብሔሮችን እስከመገንጠልና ሀገር መመስረት እስከመቻል እየፈቀደ እያየ፣ ዩጎዝላቪያን የመሠረቱ ሪፐብሊኮች ሩጫም ያንን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሽቀዳደሙ እንደሆነ እያወቀ፥ “Weak Serbia for strong Yugoslavia” (ወይም የአማራ ሆዳም ልሂቅ “ከኢትዮጵያዊነት አንወርድም” እያለ እንደሚመፃደቀው፤ አልያም የብአዴን ባለሁለት እግር አህዮች “የብሔር ፖለቲካ የዝንጀሮ ፖለቲካ ነው” እያሉ መሬት ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚጣረስ የማዘናጊያ አስተምህሮ እንደሚያሰራጩት አይነት) በማለት ህዝባቸውን ያደነዝዙት ነበር።
  • የሰርቢያው ልሂቅ ከአማራ ልሂቅ ጋር ያለው ሌላኛው ተማስሎ ደግሞ፥ ዩጎዝላቪያን አተርፋለሁ በሚል አጉል ቅዠት ሌሎች ብሔሮች የሰርቢያን ህዝብ historical guilt ተሸካሚ ያደረጉበትን ትርክት በይሁንታ አልያም በዝምታ ተቀብሎ ተባባሪ መሆኑ፥ የሰርቢያ ህዝብ አንገቱን ደፍቶ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅሙ እየተነጠቀ እስከጫፍ እንዲገፋ አድርጎታል።
  • የሰርቢያው ልሂቅ በራሱ ህዝብ ላይ የፈፀመው ሌላኛው ወንጀልና ማደንዘዣ ደግሞ፥ “ሰርቦች በመላው ዩጎዝላቪያ ተበትነን ስለምንገኝ፥ ብሔርተኛ መሆን የለብንም” የሚል መከራከሪያ ነበር። እውነታው ግን፥ የሰርቢያ ህዝብ ብሔርተኛ ሆነም አልሆነ፥ ከቀሪ የዩጎዝላቪያ ሪፐብሊኮች በማንነቱ ብቻ እየታደነ ከመሳደድና መጨፍጨፍ፣ ሀገሪቱም ከመበታተን አልዳነችም።

=> በነገራችን ላይ ከረፈደም ቢሆን ነገሮች እየተበለሻሹ ሲሄዱ The Serbian Academy of Arts and Sciences የሚባለው ተቋም፥ በተለምዶ “የሳኑ ሜሞራንደም” የሚል የሰርቢያ ህዝብ የገጠመውን ተግዳሮትና፥ በህገመንግስት የተደገፈውን የሰርቢያን ሰቆቃ “ይበጃል” ከሚለው የመፍትሔ ሀሳብ (ህገመንግስቱን መከለስ…) ጋር ይዞ ወጥቷል። ዳሩ ነገሮች ከተበለሻሹ በኋላ መሆኑ፥ ሰርቢያና ሰርቦች ዛሬም ግዛቶቻቸውን ተነጥቀውና በውስጣቸውም የጊዜ ቦምብ ተሸክመው አለማቀፋዊ ገፅታቸው ከእውነታው በተቃራኒ ተበለሻሽቶ መራራ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ።

  • የሰርቦች በመላው ዩጎዝላቪያ ተበትኖ መኖር፣
  • የሰርብ ልሂቃን “A weak Serbia for the Strong Yugoslavia” የሚል አጉል መመፃደቅ፣
  • ከናዚ ጋር ወግኖ ንፁሃንን ሲያርድ ከነበረው የክሮሽያ ባንዳና ፋሽስት ብሔርተኛ ኃይል ይልቅ፥ “ነፍጠኛና ቡርዧ” ተብሎ በተፈረጀው የሰርቢያ ገዢ ቡድን ምክንያት፥ መላው የሰርቢያ ህዝብ የ historical guilt ሰለባ ተደርጎ በቀሪ የዩጎዝላቭያ ህዝቦች ሲፈረጅ፥ የሰርቢያ ልሂቃን “ለዩጎዝላቪያ አንድነት” በሚል ሀሰተኛ ፍረጃን ህዝባቸው አሜን ብሎ ተቀብሎ አንገቱን ደፍቶ እንዲኖር ማድረጋቸው፣
  • ከሌሎች የዩጎዝላቭያ ግዛቶች በተለየ ሁኔታ የሰርቢያ የግዛት አንድነትን አደጋ ውስጥ የጣለ ህገመንግስታዊ አወቃቀር በላያቸው ላይ ሲጫን፥ የሰርቢያ ልሂቃን አጉል ዴሞክራትና ለህዝቦች ነፃነት የቆሙ ለመምሰል በህዝባቸው መሠረታዊ ጥቅሞች ላይ መቆመራቸው፣

1ኛ. እነሱ የተመኟት ጠንካራዋ ዩጎዝላቪያ እውን አልሆነችም። ይልቁንም ተበታተነች እንጂ‼

2ኛ. በወረቀት ላይ ከሰፈረው ይልቅ፥ በቅዠታምና ተመፃዳቂ ልሂቃን ተረት የሚፀና ነገር እንደሌለ በተግባር ታየ‼

3ኛ. እኔ እየጠፋሁ ሀገር እገነባለሁ፣ በእኔ ኪሳራ ሀገር ትገነባለች የሚል አጉል ተረት ተረት የራስ ህዝብን ዘላቂ መከራ ውስጥ ጥሎ ከማለፍ በቀር የሚያስገኘው ገሃዳዊ ውጤት ፈፅሞ አይኖርም‼

4ኛ. የሀገሪቱ ህገመንግስት ዋነኛው የጨዋታ ህግ ነው። ህገመንግስቱ ሉዓላዊነትን ለብሔሮች በሰጠበትና መብታቸውም ነፃ ሀገር እስከመመስረት መሆኑን አውጆ ሲያበቃ፥ አንድ ህዝብ ብቻ በተለየ ሁኔታ የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ብሆን “ሀገርን ከመበተን አተርፋለሁ” በሚል ቅዠት የሚጓዘው ጉዞ ራሱን ሰለባ ከማድረግ በዘለለ የሚያመጣው ውጤት አይኖርም‼‼‼

5ኛ. “ለሀገራዊ አንድነት” በሚል ተረት ተረት የተነሳ የሌሎች ህዝቦች መሠሪ ልሂቃን የሚደፈድፉበትን የታሪክ ውንጀላና ክስ “አሜን” ብሎ በመቀበል፥ ከመሳደድ የሚድን ህዝብ አይኖርም‼‼

6ኛ. የሰርቢያ ልሂቅ፥ “በመላው ዩጎዝላቪያ ተበትነን የምንኖር በመሆኑ፥ አርፈን እንቀመጥ” ብሎ በራሱ ህዝብ ላይ ልጓም ማጥለቁ፥ የሰርቢያን ህዝብ ከቀሪው ዩጎዝላቪያ ተሳድዶ ከመባረርና ከመገደል፣ ዩጎዝላቭያንም ከመበታተን አልታደጋትም። ሰርቢያንና ሰርቦችን ግን ዛሬም ዋጋ እያስከፈላቸው ይገኛል።

  • የኢትዮጵያው ሰርብ የሆነው አማራዊው ህዝባችን ከዚህና ከራሱ ተሞክሮ ፈጥኖ መማር ካልቻለ፥ ከሰርቦችም የከፋ ፈተና ከፊቱ ተደቅኗል‼‼‼

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator