1 0
Read Time:8 Minute, 25 Second

Mohammed Hassen

ስለ ሰሜኑ ጦርነት ከጀምሩ አሁን እስከ አለበት ሁኔታ በጣም ፣በጣም ሰፋ ያለ ዝርዝር የቀረበበት ፅሁፍ በ FEBRUARY 12, 2022 በ The Tigray War: A comprehensive analysis of the conflict from June – December 2021 በሚል ርእስ Eritrean Hub በሚል ድህረ ገፅ ላይ የተለቀቀ ፅሁፍ እያነበብኩ ነበር። የዚህን ጦርነት እንቆቅልሽ ለማወቅ የአንድ ወገንን ትርክት ማዳመጥ በቂ አይደለም። ይህ ግጭት ይዞት የመጣው ጦስ የኢትዬጵያን ጂኦ–ፖለቲክስ መልክና ቅርፅ ሊቀይር የሚችል ፍፃሜ ሊኖረው የሚችልበት መንገድ አለ። የጦርነቱ አጀማመር በፌደራል መንግስትና በትግራይ ብሄርተኞች መካካል የተፈጠረ የስልጣን ሽኩቻ ቢመስልም በጊዜ ሂደት ግን ለ 34 አመት በበላይነት ሲገዙ ከነበረበት መንበር የተባረሩት የትግራይ ብሄርተኞች የግጭቱን መሰረት የአማራ ክልልና ህዝብ ህልውናን የሚፈታተን፣ ርስት የሚቆራርስ፣ማለቂያና ማቆሚያ የሌለው የሚመስል ትርምስ ውስት የሚከት ችግር ከሆነ ሰንብቷል።

በዚህ ፅሁፍ ላይ ወያኔዎች የግጭታቸው መነሻ ምክኒያቱ የመከላከያ ሰራዊትን የሰሜን እዝን መጨፍጨፋቸው ቢሆንም ቅሉ ይህ ግጭት ከፌደራል መንግስቱ ከነበረ ግጭት በጊዜ ሂደት መልኩን ቀይሮ አማራውን የመውጋት ጦርነት እንደሆነ ያሳያል። በዚህ ውስጥ ወያኔዎች የአማራ ክልልና ህዝብን በጠላትነት እኩል ከፌደራል መንግስቱ ፈርጀው በተንቀሳቀሱባቸው ወቅቶች ያም ማለት ከትግራይ ደብረ ሲና ድረስ ደርሶ በነበረው ወረራቸው በአጋርነትና በአጋዥነት አብረዋቸው የተሰለፉ ብሄርተኛ በወያኔዎች አጠራር ፌደራሊስት ሀይሎች እነማን እንደነበሩ በግልፅ ተቀምጧል።
ወያኔዎች የአማራ ህዝብን ፖለቲካል ኢኮኖሚ ህይወትና ከዚያም አለፍ ሲል የህልውና መሰረቱን ለመናገድ በቀጥተኝነት የጠላትነት ትርክት ( arch enemy narratives) የሚጠቀሙ ሲሆን ከዚያ ባለፈ የተለያዩ ቡድኖችን በአማራ ህዝብ ላይ በጠላትነት ማነሳሳት ሌላው የወያኔዎች አማራን የማዳከሚያ ስልት ነው። እዚህ ላይ በግልፅ ወያኔ ስልጣን ላይ በነበሩት ጊዜ ጀምሮ ወሎ ላይ የ ወሎ ኦሮሞ ነው የሚለውን ትርክት በኦነግ በኩል፣ አሁን ወሎ ላይ አገው በክልልነት ለመገንጠል ዋግኽምራ አካባቢ ያሉ አንቅስቃሴዎች ፣ ጎጃም ላይ አዊ ልዩ ዞን የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችና ጎንደር ላይ በቅማንቶች በኩል የሚደረጉ የፖለቲካ ዱለታዎች ለዚህ ምስከር ነበሩ። አሁን በቅርቡ በወያኔ የ ስድስት ወር ወረራ ወቅት ወያኔዎች በስልጣን ዘመናቸው ከኋላ ሆነው ይዘውሯቸው የነበሩ ሀይሎች በዚህ ወረራ ከወያኔ ጋ በመቆም በወረራው የወያኔን እቅድ ለማሳካት አብረው ተሰልፈው ታይተዋል።

እስኪ ከፅሁፉ ላይ የተወሰነ ነገር እንይ!

ይህ ወያኔ ደሴ ደጃፍ ቆሟ በነበረበት ሰአት የነበረውን ሁኔታ ያስቃኘናል።

“However, Tigrayan forces, who had been well prepared for the anticipated offensives, weathered the storm. Subsequent counterattacks saw the TDF quickly advance to take over Dessie and Kombolcha. The capture of these two strategic cities of South Wollo opened the gateway to Shoa and, with the ENDF seriously weakened, for the first time since the war began, the federal government’s hold on power was threatened.”

የዚህ አንቀፅ ሀሳብ ከበፊት ከነበረው አንቀፅ የቀጠለ ሲሆን ከበፊት የነበረው አንቀፅ ሀሳብ መከላከያ፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ፋኖዎች የወልዲያ ከተማን ከወያኔ ነፃ ለማውጣት በተደጋጋሚ ስላደረጉት የማትቃት ጦርነት ነው የሚያወጋው።

ከዚያ ይላል ፀሀፊው በዚህ አንቀፅ: –
“ቢሆንም ወያኔዎች ለጦርነቱ ከመዘጋጀታቸው አንፃት ከመንግስት በኩል የተጠበቀውን የማጥቃት እንቅስቃሴ ማእበል በአግባቡ መቋቋም ችለው ነበር። ወያኔዎች በመቀጠልም ባደረጉት የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ደሴን እና ኮምቦልቻን ለመቆጣጠር ፈጥነው መገስገሳቸው ተመልክቷል። ወያኔዎች እነዚህን ሁለት የደቡብ ወሎ ስትራተጂክ ከተሞች መቆጣጠር የሸዋን በር ወለል አድርጎ የከፈተላቸው ሲሆን የመከላከያ በጠና መዳከም ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የፌደራል መንግስት የስልጣን ይዞታ ስጋት ላይ ሊወድቅ እንዲችል አድርጎታል።” ይላል ፀሀፊው።

የዚህ ፅሁፍ ሀሳብ የሰሜኑን ጦርነት መተረክ ሳይሆን በስድስት ወር ወረራ ውስጥ ማንና ማንን በመጠቀም የአማራ ህዝብ ላይ አስከፊ የተባለውን ጉዳት እንዳደረሱ ማሳየትና ህዝባችን ከወያኔ ጋ ያበሩና የወያኔን ሀሳብ ያራመዱ ቡድኖች እነማን ነበሩ የሚለውን ያውቅ ዘንድና አሁንም ድረስ መጨረሻው ላልታወቀው ክራሲስ ግንዛቤ ያገኝ ዘንድ ለማስቻል ነው።

“Tigrayan forces then linked up with Oromo Liberation Front (OLA) to launch offensives on Mille and North Shoa. The attacks on the Mille front, however, proved futile and were repulsed by the ENDF and Afar Special Forces who were provided with aerial cover by drones. To the south, the TDF, joined by OLA, quickly captured areas along the A2 highway and managed to advance as far as Debre Sina.”

“ከዚያም የትግራይ ሃይሎች ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ጋር በመገናኘት በሚሌ እና በሰሜን ሸዋ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል። ወያኔ በሚሌ ግንባር ላይ የሰነዘሩት ጥቃት በሰው አልባ የድሮን ሽፋን አማካኝነት በመከላካያና በአፋር ልዩ ሀይል ርብርብ ወረራው ሊከሽፍና ሊመክቱት ችለዋል። ከአፋር ወደ ደቡብ በኩል ወያኔ ከ ኦነግ ሀይሎች ጋር በመቀላቀል በA2 አውራ ጎዳናዎች ላይ ያሉ ቦታዎችን በፍጥነት በመያዝ እስከ ደብረ ሲና ድረስ መገስገስ ችሏል።” እያለ ዘገባው ይቀጥላል።

ወያኔ ጋ አብረው ወያኔን ደብረሲና ድረስ ያገዟት ሀይሎቸወ ዛሬ በአጣዬ፣ሸዋሮቢት፣ ኤፍራታና ግድም ወረዳ የሚታየውን ተደጋጋሚ ወረራ በአማራ ህዝባችና ላይ የሚፈፅሙ ሀይሎች ናቸው።

“Meanwhile, a new front opened up to the northwest, as Tigrayan forces, in alliance with a few battalions of the newly formed Agaw Liberation Army (ALA) (which drew its support from ethnic Agaw populations in Wag Himra and Agew Awi Zones of Amhara region) attempted to wrestle control of Sekota from the hands of Amhara SF. The TDF-ALA offensive reportedly took place around mid-August as a joint TDF-ALA detachment advancing from Korem, was joined by another TDF detachment from Lalibela. By August 17th , 2021, Sekota, the capital of Wag Himra zone came under the control of TDF-ALA troops.”

“ይህ በእንዲህ እንዳለ ወያኔዎች በቅርብ ከተፈጠረው አነስተኛ ባታሊዮን ካለው የአገው ነፃ አውጪ ( ይህ የአገው ነፃ አውጪ ወታደር በዋግክምራና ጎጃም አዊ ዞን ባሉ ነዋሪዎች የሚደገፍ ሀይል ነው) ወታደርች ጋ በመተባባር ከአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እጅ የዋግ ኽምራ ልዩ ዞን ዋና ከተማ የሆነቸውን የሰቆጣን ከተማ ለመቆጣጠር ትግል ጀምረው ነበር። ይህ ሰቆጣን የመቆጣጠር ዘመቻ የተጀመረው ነሀሴ አጋማሽ ከኮረም ከተማ በተነሳ የወያኔማ የአገው ነፃ አውጪ ሰራዊት ጥምር ጦር ሲሆን ሌላ ከላሊበላ ከተማ የተነሳ የወያኔ ጦር ጋ በመቀናጀት ነሀሴ 17 የወያኔና የአገው ነፃ አውጪ ጦር በጥምረት የሰቆጣ ከተማን መቆጣጠር ችለዋል። “
ይላል ዘገባው።

“The OLA, meanwhile, took control of Kemisse town, cutting off the A2 highway from Addis Ababa to Dessie.”

“በዚህ መካከል ደግሞ የኦነግ ጦር ከአዲስ አበባ ደሴ የተዘረጋውን የ A2 አውራ ጎዳና በመቁረጥ የከሚሴን ከተማ መቆጣጠር ችለው ነበር። “

The TDF-OLA link up and the march on Addis Ababa

“After consolidating their control of Dessie and Kombolcha, the TDF launched offensives in three directions along the B11, A2, and B21 highways. The TDF advance along B11 highway was intended to capture the town of Mille and sever the Addis Ababa – Djibouti highway, the main economic artery of the federal government. The latter two offensives were intended to advance to Addis Ababa, the country’s capital, and unseat Abiy’s government.”

“ወያኔዎች ደሴን እና ኮምቦልቻን ከተቆጣጠረ በኋላ በሶስት አቅጣጫ ማለትም በ B11፣ A2 እና B21 አውራ ጎዳናዎችን ተከትለው የማጥቃት እርምጃቸውን አስፍተው ነበር። በአውራ ጉዳና B11 አውራ ጎዳና ላይ የተጀመረው ጥቃት የፌደራል መንግስት ዋና የኢኮኖሚ የደም ቧንቧ የሆነውን የአዲስ አበባ – ጅቡቲ አውራ ጎዳና ማእከል የሆነውን የሚሌ ከተማን ለመያዝ እ ታስቦ ነበር። ቀሪዎቹ ሁለቱ ጥቃቶች ወደ አዲስ የሀገሪቱን ዋና ከተማ ለመቆጣጠርና እና የአብይን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ የታሰበ ነበር።”

“By early August, the TDF and OLA had announced that they had struck a military alliance to bring down the incumbent federal government. They had since been synchronizing their offensives to maximize the impact on the federal forces. After the fall of Dessie, reports indicated that the TDF and OLA had made a physical link-up around Bati and Habru, areas dominated by ethnic Oromos who had strong sympathies with the OLA.”

“በነሀሴ ወር መጀመሪያ ላይ ወያኔና እና ኦነግ በስልጣን ላይ ያለውን የፌደራል መንግስት ለማፍረስ ወታደራዊ ህብረት እንደፈጠሩ አስታውቀዋል። (ፌደራሊስት የሆነው መንግስት) በፌዴራሊስት ሃይሎች ላይ የሚያደርሰውን ጫና ለመቀነስ በማሰብ መንግስት ላይ የሚወስዱትን ጥቃት በተቀናጀ ሁኔታ ለማድረግም ተስማምተው ነበር። ከደሴ ውድቀት በኋላ የኦሮሞ ተወላጆች ከፍተኛ ቁጥር ያለባቸውና የኦነግ ትግል ቀንደኛ ደጋፊ ናቸው በሚባሉት የባቲና ሀርቡ ከተሞች የወያኔና የኦነግ ተዋጊዎች በአካል ተገናኝተው መምከራቸውም መረጃዎች ያመላክታሉ።”

“On November1st 2021, a joint TDF-OLA operation captured the towns Gerba and Bati. No information has been disclosed regarding how their alliance translated into action on the battlefield. However, since the OLA lacked combat experience, the involvement of its units in conventional battles was likely limited to reinforcing gains and conducting ambushes to distract the adversary.”

“ከላይ በተጠቀሰው አብሮ የመስራት ውል ስምምነት መሰረት በህዳር 1 2021 የወያኔና ኦነግ ጥምር ኦፕሬሽን ገርባ እና ባቲ ከተሞችን ያዘ። ትብብራቸው ወደ ጦር ሜዳ engagement እንዴት አንተቀየረ የሚያስረዳ ሰነድ ባይኖርም ኦነጎች የውጊያ ልምድ ስለሌላቸው የኦነግ ተዋጊ ክፍሎቹ በመሰረታዎ የጦርነት ውጊያዎች ውስጥ ከመሳተፍ ይልቅ በወያኔዎች ጥቃት የተያዙ አካባቢዎች ማስጠበቅና የመንግስት ጦርን ለማዘናጋት ሽምቅ ውጊያዎችን በማካሄድ ላይ ብቻ የተገደበ ሊሆን እንደሚችል ግምት ነበር።”

“Along the A2 highway, Tigrayan forces advanced unimpeded all the way to Kemisse where they joined the OLA forces which had secured the town a couple of days previously. The TDF-OLA alliance significantly facilitated TDF relations with the locals of Oromo Special Zone. Consequently, the TDF-OLA advance along the A2 highway to Gerbe and Senbete, border towns of the Oromo zone, was swift and unobstructed by any local resistance.”

“በA2 አውራ ጎዳና ላይ የተሰማራው የወያኔ ሰራዊት ያለምንም እንቅፋት ወደከሚሴ በመዝመት ከቀናት በፊት ከተማዋን የተቆጣተረውን የኦነግ ሰራዊት መቀላቀል ችለዋል። በኦነግ ሀይሎች የኦሮሞ ልዩ ዞን ማህበረሰብና ነዋሪ ከማግባባታቸው የወያኔና የኦነግ ጥምር ጦር ከኦሮሞ ልዩ ዞን ማህበራብና የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር የነበራቸውን ግንኙነት በእጅጉ ቀላል አድርጎት ነበር። ስለሆነም የወያኔና የኦነግ ጥምር ጦር በA2 አውራ ጎዳና ለይ ገርባን፣ ሰንበቴና ሌሎች የኦሮሞ ዞን አዋሳኝ ከተሞችን ለመቆጣት ያደረጉት ግስጋሴ ፈጣን እና በአካባቢው ምንም አይነት ተቃውሞ ያልገጠመው ነበር።”

“On November 5th, 2021, the TDF and OLA jointly announced the formation of a new coalition, the United Front of Ethiopian Federalist and Confederal Forces, to include seven other military organizations representing Afar, Gambella, Agaw, Sidama, Benishangul, Somali and Qimant nationalities.”

“እ.ኤ.አ. ህዳር 5፣ 2021 ወያኔና ኦነግ በጋራ በመሆን የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት እና ኮንፌዴሬሽን ሃይሎች የተባሉ የአፋር፣ የጋምቤላ፣ የአገው፣ የሲዳማ፣ የቤኒሻንጉል፣ የሶማሌ እና የቅማንት ብሄረሰቦችን የሚወክሉ ሰባት ወታደራዊ ድርጅቶችን ያካተተ አዲስ ጥምረት መመስረታቸውን አስታውቀው ነበር።”

ይላል ዘገባው።

አስቡት:–
የፌደራልን መንግስት ከስልጣን ለማውረድ ተማምለው የነበሩት ሰባት ሀይሎች ከላይ የተገለፁት ሲሆን የወያኔ ወረራ ተመክቶ ወያኔ ወደ ትግራይ ከተመለሰች በኃላ ህግ ማስከበር በሚል ዘመቻ የሚሳደዱትና የሚታሰሩት ለዚያውም ወያኔን ወደ ትግራይ በመመለስ ሂደት ውስጥ ከፌደራል መንግስት ጎን በመቆም መስዋእትነት የከፈሉት የአማራ ህዝብ ልጆች የሆኑት ፋኖዎች ሲሆን ከላይ በተጠቀሱት ሰባት ሀይሎች ላይ መንግስት ምን አይነት እርምጃ እንደወሰደ እስከ አሁን የታወቅ ነገር የለም። አሁንም ድረስ ከወያኔዎች ድጋፍ እንደሚያገኙ የሚነገርላቸው የቅማንት፣አገውና የኦነግ ሀይሎች የአማራ ክልልን በተለያየ ሁኔታ በመነቅነቅ ላይ ናቸው። የሰሞኑ የኦነግ ኤፍራታና ግድም ወረዳ እንዲሁም ጅሌ ጥሙጋ ወረዳዎች ግርግርና ከሰሞኑ በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የሚታየወ የአገው ነፃ አውጪ ሰራዊት የምረቃ ፕሮግራም ስነስርአቶች ኦነግ ኦሮሚያ ክልል በነፃነት ሰራዊት ከማሰለወጠን እስከ የአማራ ተወላጆችን እስከ ዘር ማጥፋት የደረሰ ጭፍጨፋ የዚህ ሁሉ የፖለቲካ ድብልቅልቅ ሆኖ ሳለ የዶር @Abiy Ahmed Ali መንግስት ከነኚህ ሀይሎች ላይ የወያኔ አጀንዳ ተቀባይና አራማጆች መሆናቸውን አውቆ እርምጃ ከመውሰድ ይልው ህዝቤን ከወረራ ልከላከል ያለውን ፋኖን መሳደድ የፖለቲካ ቅሽምናቸው ጥግ መሆኑን ማሳየታቸውን ቀጥለዋል።

የአማራ ህዝብ በዚህ ሁሉ ችግርና መከራ፣ የፖለቲካ ውስልትና ውስጥ ይገኛል። የችግር አፈታታችን መነሻምና የትግላችን አላማ ይሄን ሁሉ ታሳቢ ያደረገ መፍትሄ ማበጀት ላይ ያተኮረ ሊሆን ግድ ይላል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator