አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ታህሳስ 18 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ጉዳይ ፖሊስ በድጋሚ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ 2ኛ ልዩ ልዩ ችሎት ታህሳስ 15 ቀን 2014 ፖሊስ ተጠርጣሪዋን ይዞ እንዲቀርብ ትዕዛዝ የተሰጠው መሆኑ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ በእለቱ ተጠርጣሪዋን ከማቅረብ ይልቅ ከፍ/ቤቱ ግቢ ከደረሰች በኋላ ከበላይ ትዕዛዝ ተሰጥቶኛል በሚል ኮማንድ ፖስቱ ስለያዛት እኔ ለማቅረብ አልችልም የሚል ይዘት ያለው በደብዳቤ ምላሽ ይዞ መቅረቡ አይዘነጋም።

ችሎቱም ትዕዛዝ በማክበር ተጠርጣሪን በማቅረብ ፈንታ በደብዳቤ ምላሽ ማቅረቡ አግባብ አለመሆኑን በመግለጽ መርማሪ ተጠርጣሪዋን ታህሳስ 18 ቀን 2014 ይዞ በመቅረብ ለችሎት እንዲያስረዳ ሲል ድጋሚ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር።

ይሁን እንጅ ፖሊስ አሁንም በድጋሚ ትዕዛዙን አክብሮ አልተገኘም።

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ 2ኛ ልዩ ልዩ ችሎትም በጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ የእስር ጉዳይ ላይ በዋለው ችሎት ተጠሪ ትዕዛዝ ለምን እንዳልፈጸመ ታህሳስ 19 ቀን 2014 ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ቀርቦ እንዲያስረዳ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator