አሸባሪ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያን በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ጀብውሃ፣ ቁርቁር፣ ጀጀባ እና ሰንበቴን ጨምሮ በአጣዬ ዙሪያ በቡድን መሳሪያ የታገዘ ወረራ ሲፈጽሙ ውለዋል፤ ጀብውሃን መቆጣጠሩም ተሰምቷል።
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ጥር 15 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ
አሸባሪ እና ተስፋፊ ኦነጋዊያን በኤፍራታ እና ግድም ወረዳ ጀብውሃ፣ ቁርቁር፣ ጀጀባ እና ሰንበቴን ጨምሮ በአጣዬ ዙሪያ በቡድን መሳሪያ የታገዘ ወረራ ጥር 15/2015 ሲፈጽሙ መዋላቸውን ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ውለዋል።
ከፍተኛ የሰው ኃይል በማሰማራት ጥር 15/2015 በፈጸመው ወረራም ጀብውሃን መቆጣጠሩ ተሰምቷል።
አሸባሪው ኦነጋዊያን ከአካባቢው የመንግስት አካላት ጋር በመተባበር የወረራ ጥቃታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል።
ጥር 13/2015 ዓ/ም በኤፍራታና ግድም ወረዳ ጀብውሃ ቀበሌ በሚገኘው በአማራ ልዩ ኃይል ካምፕ ላይ በቡድን መሳሪያ በመታገዝ ባደረሱት ጥቃት ከ25 በላይ የአማራ ልዩ ኃይል እና 5 የፌደራል ፖሊስ አባላት መገደላቸው እና በርካቶች መቁሰላቸው ይታወሳል።
የወረራ ጥቃቱ በተለያዩ አቅጣጫዎች ተጠናክሮ ስለመቀጠሉ ለአሚማ የገለጹት ምንጮች ተጨማሪ ኃይል አስፈላጊ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
ከአጣዬ ወደ ጀብውሃ የሚወስደው መንገድ በአሸባሪ ኦመነጋዊያን በመዘጋቱ ችግሩን አሳሳቢ አድርጎታል ተብሏል።
የቆሰሉ ወገኖችን ወደ ሸዋሮቢት ለማጓጓዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተመላክቷል።
ማህበረሰቡ የወራሪዎችን ጥቃት በመመከት ረገድ አካባቢውን ነቅቶ እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።