0 0
Read Time:1 Minute, 14 Second

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

ጀግናው አርሶአደር ካሴ ባውቄ አልሞ ተኳሽ፣ በሰፈሩ ለሚያልፍ መንገደኛ ሁሉ የድኩላ እና የሚዳቋ ቋንጣ ሸምጥጦ የሚሰጥ፣ እርጎ እንደ ውሃ ቀድቶ የሚያጠጣ፣ በጠንካራ አርሶአደርነቱ እና በአዳኝነቱ ስሙ በሜጫ ወረዳ እና በመርዓዊ ከተማ የታወቀ ነበር። አርበኛ ዘመነ ካሴ የአርሶ አደር የካሴ ባውቄ ልጅ ነው!

ካሴ ባውቄ በአራሽነቱም በተኳሽነቱም የተከበረ እና ስመጥር፣ በወረዳው በጀግንነቱ የሚፈከርለትም ነበር። አርሶአደር ካሴ ባውቄን በልጅነቴ ከማስታውሳቸው ታዋቂ የአካባቢያችን አርሶአደሮች በተለየ አውቀዋለሁ። ቁመናው አጠር እና ቀጠን ያለ፣ ቀልጣፋ አርሶአደር፣ ቁምጣውን ለብሶ፣ በባዶ እግሩ ፈጠን ፈጠን ብሎ የሚጓዝ፣ ከትክሻው የማትለየውን አብራራው አነግቶ በኩራት የሚንጎማለል ልበ ሙሉ አርሶ አደር ነበር። ልጆቹም አርሶአደሮች በጀግንነታቸው ተኳሽ እና ጠንካራ አራሽ፣ ተማሪዎችም በጉብዝናቸው የሚታወቁ ነበሩ። የዘመነ ካሴ ታላቅ እህት ኢለመንታሪ አብራኝ የተማረች፣ ከሆል ሴክሽን የማታስቀምስ ነበረች። ዘሜም ኮከብ ተማሪ፣ የስነ ጽሁፍ እና ኪነ ጥበብ ተሰጥዖ ያለው ሁለገብ ኮከብ ተማሪ ነበር።

የአዲስ አበባ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቲያትር ጥበባት ት/ቤት ኮከቦችን ያፈራው የመርዓዊ ከተማ የመረዋ ኪነጥበብ ክበብ እነ ዘመነም ከፍተኛ ተሳትፎ እና አስተዋጽዖ አድርገውበታል። ዘመነ ካሴ በድምፃዊነት፣ በተወዛዋዥነት እና በድርሰት ተሳትፎ ያደርግ ነበር።

ዘመነ ካሴ ከዩኒቨርሲቲ ሲወጣ የአማራ ወጣቶች ማሕበር ፕሬዚደንት፣ ቀጥሎም ገና በወጣትነት ዕድሜው የዞን መምሪያ ሀላፊነት የተሾመ ነበር።

ዘመነ የዞን መምሪያ ሀላፊ በነበረበት ወቅት ዛሬ አማራን ወክለው ያሉ አብዛኛዎቹ ሚኒስትሮች የወረዳ እና ክፍለ ከተማ ካድሬዎች ነበሩ።

ዘሜ የአማራ ህዝብ በደል ዘልቆ የሚያመው፣ የአገራችን ፓለቲካ መጎሳቆል እንቅልፍ የሚነሳው፤ ትሁት፣ ሰው ወዳድ እና አክባሪ፣ ሀቀኛ እና ጥቅም ቅንጣት ያህል የማያጓጓው አብሮ አደግ ወንድሜ ነው።

ሳያውቁሁ በጥላቻ ጥርሳቸውን የሚነክሱብህ ጥቂቶች ቢኖሩም፣ ማንነትህን የምናውቅ አብሮ አደጎችህ እና በሚሊየን የሚቆጠር የአማራ ወጣት ከጎንህ ነው።

በርታ ወንድሜ፣ እስከመጨረሻው ከጎንህ ነኝ!

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator