በአድዋ እና በካራማራ ሕዝባዊ የድል በዓል አከባበር ጋር በተያያዘ በጅምላ የታሰሩት የአዲስ አበባ ወጣቶች ለእስር ከተዳረጉ ዛሬ 34 ቀናቸው ነው። በእነኚህ ቀናት ውስጥ በተደጋጋሚ በፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት አራዳ ምድብ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል ። ሆኖም ግን ፈር በለቀቀው ይግባኝ እና የገንዘብ ዋስትና የአዲስ አበባ ልጆች በእስር እየተንገላቱ ነው።

ለጊዜው በግልጽ የታወቀው ስድስት መዝገቦች ፖሊስ የምርመራ መዝገብ የከፈተባቸው ሲሆን ፤ በእያንዳንዱ መዝግብ ከ10 እስክ 15 የሚሆኑ የአዲስ አበባ ወጣቶች ላይ የክስ ዶሴ ተከፍቷል ። በእያንዳንዱ መዝገብ በአማካይ አምስት የተለያዩ ቀናት ፍርድ ቤት ቀርበዋል ፤ ሁሉም የገንዘብ ዋስትና አስይዘው ከእስር እንዲለቀቁ የታችኛው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይሰጣል ፖሊስ ይግባኝ ይጠይቃል፣ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኙን ይቀበላል ፤ በተንዛዛው የፍርድ ሂደት የተጠርጣሪ ሕጋዊ መብቶች እየተጣሱ ይገኛል።

ዛሬ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሦስት መዝገቦች እስከ 40 የሚደርሱ የአዲስ አበባ ወጣች እያንዳንዳቸው በ7 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ የወንጀል ችሎት ትዕዛዝ ሰጥቷል ። የዛሬው ትዕዛዝ ከዚህ ቀደም ከሆነው ይለይ ይሆን ?!

ይህ በእንዲ እንዳለ በእነ ኤርሚያስ ብርሃኑ የክስ መዝገብ 10ኛ ተጠርጣሪ የሆነው ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ፤ እሱ በተጠረጠረበት ወንጀል በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ፣ የዋስትና መብቱ የተፈቀደለት ቢሆንም ፤ፖሊስ በተከታታይ ቀናት የምርመራ መዝገብ ይዤ አልመጣሁም በማለቱ ብቻ ለፊታችን ሰኞ ሚያዚያ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 8 ሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል::

ይህ መሆኑን ተከትሎ ፤ ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ለችሎቱ መናገር እንደሚፈልግ በመግለጽ ” እኛን የከሰሰን የጣሊያን ወይም የሱማሌ መንግስት ቢሆን ክሱን እንቀበለው ነበር ፤ የጀግኖች አባቶቻችን የድል በዓል በማክበራችን፣ መታሰራችን በጣም አዝኛለሁ ። የእኛ የኢትዮጵያዊያን ባለ ሥልጣኖች ከሰውን እዚህ ደረጃ መድረሳችን የሚያሳፍር ነው። ይህ አሳዛኝ ድርጊት በታሪክ ይመዝገባል” ብሏል ። ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለው ይህን በሚናገርበት ወቅት የዕለቱ ዳኛ እና የችሎት ታዳሚ እጅግ በላቀ አግራሞት ንግግሩን ተከታትለዋል ።

ፍትሕ ለአዲስ አበባ ወጣቶች !

በይድነቃቸው ከበደ

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator