0 0
Read Time:1 Minute, 8 Second

የአማራ ድምጽ ሚዲያ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በሲቪል እና በታጠቁ የመንግስት አካላት ታፍኖ ከተወሰደ እና አድራሻው እንዳይታወቅ ከተደረገ 6ኛ ቀኑን ይዟል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ

ቀደም ሲል በኢሳት በመቀጠልም በየኛ ቲቪ ያገለገለው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ የአማራ ድምጽ ሚዲያ በሚል ለአድማጭ ተመልካቾቹ በመልካም አቀራረብ መምጣት ጀምሮ እንደነበር ይታወቃል።

ይሁን እንጅ ሚያዝያ 22/2014 ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ አያት አካባቢ ከስራ ቦታው ሲወጣ መንገድ ላይ የአዲስ አበባ ፖሊሶች ለደቂቃዎች ይዘውት እንደነበርና በመጨረሻም ስሙን ጠይቀውና መታወቂያ አይተው በስህተት ነው በሚል እንደለቀቁት የስራ ባልደረባው ጋዜጠኛ ጌትነት አሻግሬ ተናግሯል።

ምንአልባትም እንዲሸሽ እና ከዛም ሊያመልጥ ሲል ያዝነው በሚል የተለመደ ማካበጃ ለመስራት ተፈልጎ ሊሆን እንደሚችል የተጠቆመ ሲሆን በማግስቱ ሚያዝያ 23/2014 ከረፋዱ 4 ሰዓት ላይ በመኖሪያ ቤቱ እያለ ታፍኖ ተወስዷል።

በሲቢል እና በታጠቁ የመንግስት አካላት ታፍኖ የተወሰደው ጋዜጠኛ ጎበዜ አድራሻው እንዲጠፋ ከተደረገ 6ተኛ ቀኑ ተቆጥሯል።

መላው ቤተሰቦቹ፣ የስራ ባልደረቦቹ፣ ጓደኞቹ እና አድናቂዎቹ የመንግስት አካላት በፈጸሙት የለየለት አፈና በእጅጉ በማዘንና በመጨነቅ ላይ ይገኛሉ።

የተለያዩ ተቋማት ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ባስቸኳይ ያለበት እንዲታወቅና ከአፈና እንዲወጣ እየጠየቁ ነው።

እንደአብነትም ኢሰመኮን ጨምሮ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር፣ የአማራ ማህበራት የጋራ መድረክ በጀርመን እና ሌሎችም የተቃውሞ መግለጫ አውጥተዋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከጠበቃ አዲሱ አልጋው ጋር የነበረው ቆይታ እንዳመለከተው በየካቲት 12 ሆስፒታል ታክሞ ተወስዷል የተባለው ስህተት ነው።

ጠበቃ አዲሱ ወደ ሆስፒታሉ በመሄድ ከድንገተኛ የህክምና ክፍል እና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገራቸውንና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ስህተት ነው፤ እንዲህ ዓይነት አሰራርም የለንም የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን ነው ለአሚማ የተናገሩት።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator