ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ግንቦት 20/2014 ከጠዋቱ 3 ሰዓት አካባቢ ሰሚት ኮንዶምኒዬም አካባቢ ከስራ ባልደረባዋ ቤት ባለችበት በጸጥታ አካላት ታፍና ተወስዳለች።

ሁለት የፌደራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ ፖሊሶች እና 3 ሲቪል ለባሾች ለጥያቄ እንፈልጋታለን በማለት ይዘዋት እንደሄዱ ባለቤቷ አቶ ሮቤል ገበየሁ እና ባልደረባዋ ምስራቅ ተፈራ ከአሚማ ጋር በነበራቸው ቆይታ አስረድተዋል።

በአሁኑ ሰዓት ወደየት እንደወሰዷት እንኳ በትክክል እንደማይታወቅና ፍለጋ ላይ ስለመሆናቸው አስታውቀዋል።

መረጃ እንዳታቀብል በሚል የምስራቅ ተፈራን የእጅ ስልክ ጭምር ነጥቀው ከወሰዱ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሰው ላኪ ብለው በላከችው ሰው በኩል ስልኳን እንደመለሱላት ተናግራለች።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ 17 ጋዜጠኞች ከህግ ውጭ መታሰራቸው ታውቋል።

መንግስት በህግ ማስከበር ስም በተለይም በአማራ እና በአዲስ አበባ እየሄደበት ያለው መንገድ አፈና ነው በሚል ኢሰመኮ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ማህበርን ጨምሮ የተለያዩ አደረጃጀቶችና ህዝብም እያወገዘው ይገኛል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator