0 0
Read Time:39 Second

ስለሀገር እና ስለወገኑ በመታገሉ በካድሪዎች በመሳደድ ላይ የሚገኘው የፋኖ ማስተር ብርሃኑ ታላቅ ወንድም በቁጥጥር ስር ዋለ።

የሕልውና ዘመቻውን ተከትሎ በማይጠብሪ እና በላሊበላ ግንባር ተሰልፎ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገው የላይጋይንት ጀግና ዘውዱ ተፈራ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ዘውዱ ተፈራ ከሕልውና ዘመቻ ማግስት ጀምሮ በደካማ ካድሪዎች እየተሳደደ የሚገኘው የፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሰልጣኙ የፋኖ ማስተር ብርሃኑ ታላቅ ወንድም ነው።

ግንቦት 18/2014 ከቀኑ 8:30 አካባቢ በላይጋይንት ወረዳ ታች ነገላ ቀበሌ 23 ከስራ ቦታው በመያዝ እንደ ህመምተኛ በአምቡላንስ ጭነው ወደ ነፋስ መውጫ ወስደውታል ተብሏል።

የ23 ቀበሌ ሊቀመንበር በመሆን ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ እና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ ተገልጧል።

ሽባባው ደርብ የተባለ ሚሊሻ ወንድሙን በማይጠብሪ ግንባር የተነጠቀው ዘውዱ ተፈራ በትግሉ ላይ ትልቁን ሚና የተወጣ ነው።

የፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሰልጣኙና በርካታ ፋኖዎችን በማሰልጠንና በማብቃት የሚታወቀው ፋኖ ማስተር ብርሃኑ ከዘመቻ ህልውና ማግስት ጀምሮ በወረዳው ውስጥ ባሉ ደካማ ካድሪዎች እየተሳደደ እንደሚገኝ ይታወቃል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Translator