በፍትህ መፅሄት ቁጥር 101 ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ “አባ ብላ ገመዳ” በሚል ርዕስ ስር በኦዴፓ ግምገማ ወቅት አዳነች አቤቤ በአካዉንቷ 40 ሚሊየን ብር እንደገባላትና እንደተገመገመችበት የሚገልፅ መረጃ ተጠቅሷል። ተሙ በፖሊስ የታሰረዉ ይህን መረጃ በማንሳቱ አይደለም። የአዳነች አቤቤ ክስ ሽፋን ነዉ። ተሙ የጠቅላይ ሚንስትሩን የመጋረጃ ጀርባ ተግባራት በፍትህ መፅሄት በተደጋጋሚ ያጋልጣል። የመከላከያን ወገንተኝነት በመረጃ ይተቻል። ይህን በማድረጉ በተደጋጋሚ ዛቻ ደርሶበታል። የእንገድልሃለን ዛቻ አይናችን እያየ፣ ጆሯችን እየሰማ በሚዲያ ተላልፏል። ተሙ ግን የሚንበረከክና የሚፈራ ሰዉ አይደለም። የዛሬዉ የተሙ እስር “አባ ብላ ገመዳ” በሚለዉ ፁፉ ጠቅላይ ሚንስትሩ የለየለት የህወኃት አሽከር እንደነበረ በመፃፉ ነዉ። ተሙ እንደሚለዉ አብይ አህመድ በ1999 ዓ. ም የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር በነበረበት ወቅት በአንድ አጋጣሚ አቦይ ስብሃት ታሞ ደቡብ አፍሪካ ለህክምና በነበረበት ወቅት አቦይ ስብሃትን ካልጠየቅሁ ሞቸ እገኛለሁ በማለት ማመልከቻ ለህወኃታዉያን አስገብቷል። ይህን ለስልጣን ሲባል የተፈፀመ አድርባይነት ተሙ ፅፎታል።በተጨማሪም አብይ አህመድ ኢንሳ በነበረበት ወቅት ተመስገን ደሳለኝን ይሰልለዉ እንደነበር <… በተረፈ፣ አብይ ኢንሳ እያለ ይሰልልህ ነበር ሲሉኝ አይደንቀኝም። በኢህአዴግ ቤት የስልጣን መወጣጫዉ ዉስብስብ አይደለም።> በማለት የአብይን ለስልጣን ሲል ግለሰቦችን ሳይቀር ይሰልል እንደነበረ ጠቅሷል። ባናቱም የመከላከያ ጀኔራሎችን በሚከተለዉ መልክ ሸንቆጥ አድርጓል። <….. ዛሬ እንደ ጎረምሳ የሚፈነዱብን ጄኔራሎችም፣ ለሳሞራ የኑስ የነበራቸዉን “መንፈሳዊ ታዛዥነት” እያስታወስኩ ጊዜ ደጉን አመሰግናለሁ።> እናም የተሙ እስር የአዳነች አቤቤ ስም መነሳቱ አይደለም። እዉነታዉ ትችት የማይወደዉ ጠቅላይ ሚንስትር ለምን እተቻለሁ በሚል ግፊት የተሰጠ ትዕዛዝ ነዉ። የአዳነች አቤቤ ክስ ሽፋን ነዉ።
Journalist Temesgen Dessalegn got arrested today and is taken to Addis Ababa Police Commission in Addis Ababa. Fitih magazine editor Misgan Zinabe is also taken along with Temesgen. A large number of police rounded Temesgen’s office around 2 pm and asked for Temesgen. Temesgen, who wasn’t in his office at the time, received a call from his editor informing him about the situation. Temesgen tried to talk to the police over the phone, asking them if they have a warrant or any charge, and told them to leave it for him at his office. The police insisted they only want to talk to him and wanted to know where to find him. Temesgen, therefore, decided to go back to his office to speak in person. However, the police put him in their car and took him to Addis Ababa Police station, commonly known as Sostegn. I also confirmed that Temesgen is at the Addis Ababa police commission. Tariku Desalegn – miki (Brother of Temesgen Desalegn)CC:
Amnesty InternationalAmnesty, International AfricaHuman Rights Watch, CPJ Middle East and North Africa / لجنة حماية الصحفيين, U.S. Embassy Addis AbabaBritish Embassy, Addis Ababa – UK in EthiopiaEmbassy of Sweden, Addis AbabaGerman Embassy Addis Ababa