ከአማራ ህዝብ ጋር ሂሳብ አወራርዳለሁ፤ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ብሎ ተማምሎ ወደ ክልሉ የገባው የጥፋት ቡድን ንጹሀንን በጅምላ መግደሉ፣ ከህጻን እስከ አዛውንት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሴቶችን መድፈሩ፣ ሀብት ንብረታቸውን መዝረፉና ማቃጠሉ፣ እንስሳትን መግደሉ፣ እጽዋትን መጨፍጨፉ አልበቃ ብሎት ይህንን ግፍ በላልይበላ ፈጽሞ ወጥቷል።
ከዘረፋ የተረፋቸውን የላልይበላ ኤርፖርት ንብረት የቡድኑ ታጣቂዎች በዚህ መልክ ማውደማቸውን የኢፕድ ዘጋቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል።