በዘረኛው ትህነግ/ ኢህአዴግ እና በጠባብ ኦነጋዊያን ተኮትኩቶ ያደገው አማራ ጠል የፖለቲካ አደረጃጀት በህገ መንግስት እውቅና አግኝቶ በጋሃድ ስራ ላይ ከዋለ ሰላሳ አመት ሊሞላው ነው።
መንግስታዊ መዋቅርን ተጠቅሞ በአማራ ላይ የሚደረገው የዘር ማጥፋት ተግባር ዛሬም ቤንሻንጉል ክልል ተብሎ በተከለለው በንፁሃን አማሮች ላይ የተፈፀመውና ካለፈው የቀጠለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፤ ልባችን ደምቶ በከፍተኛ ቁጭትና ሀዘን ላይ እንገኛለን።
የኦሮሞን የመስፋፋትና ሀገር የመሆን ቅዠትን ለማሳካት በሌሎች አካባቢዎች እንደሆነው ሁሉ፤ ጉምዝን እንደ መሳሪያነት በመጠቀም ባለርስቱን አማራ በአባቶቹና በራሱ ርስት ላይ በግፍ ተገደሏል፤ ተፈናቀሏል።
የመንግስት ዋነኛ ስራ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ ነበር። እየሆነ ያለው ግን ላለፉት ሰላሳ አመታት አማራውን ሀገር አልባ የሚያደርግ፥ አማራ ጠል የሆነ ህገ መንግሥት በማዕከላዊም በክልልም ተቀርፆ የአማራ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ነው።
በዚህ መንግስታዊ መዋቅር የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሲሰሩ እና ሲያሰራጩ የኖሩት ቡድኖች ዛሬ ያፈሩት ትውልድ ከስክቢርቶ ይልቅ ገዠራ ያዥ፥ ከፍቅር ይልቅ ጥላቻ የሚያስቀድም፥ ካርቆ አሳቢነት ይልቅ ውስነት፥ ከሰፊነት ይልቅ ጠባብነትን የተጋተ፥ በተሳሳተ መንገድ የሚነጉድ ነው። ለዚህም ነው በመላው ኢትዮጵያ አማራ በሰላም መኖር ያልተቻለው።ስለዚህ የአማራ ህዝብ መንግስት አልባ መሆኑን አምኖ እራሱን የመከላከል ተፈጥሮአዊ መብቱን እንዲጠቀም ያደራጀው ወይም የሚከላከልለት ባለመኖሩ የዘር ጭፍጨፋ እየተካሄደበት ይገኛል።
የአማራ ጠሉ መንግስትም በንፁሃን አማሮች ላይ እያሰለሰ የሚደረገውን የማንነት ተኮር ጭፍጨፋዎች ተባባሪና አስተባባሪ ሆኖ አሁን ድረስ ቀጥለዋል። ብአዴንም በዋናነት የአማራው ጠላት መሆኑን በየጊዜው በሚያከናውናቸው ተግባሮች እንገነዘባለን።
በመተከልም ሆነ በሌሎች አካባቢዎች በአማራዎች ላይ አሰቃቂ ጭፍጭፋ ሲካሄድ ጥቃቱን ያስቆመምም ሆነ የተከላከለ የመንግስት ባለስልጣን አለመኖሩና፥ የፀጥታ ሀይሉም ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ እንደሚባለው ለአስከሬን ስብሰባ የሚላክ አንፑላንስ ሆኗል። ስለዚህ አማራው ከራሱ በስተቀር የሚደርስለት ማንም እንደሌለ ያሳያል።
የአማራ ማህበር በዩኬ በሀገራችን በአራቱም አቅጣጫ አማሮች ላይ እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ የመንግስት ድጋፍ ያለውና ቀጣይ እንደሆነ ያምናል።
ይህን ማስቆም የሚችለው ደግሞ አማራው በሚያደርገው እራሱን የመከላከል ትግል ብቻ ነው። ለዚህ ጥቃት መንግስት አልባ ሆኖ ያለተከላካይ እንዲገኝ ብቻ ሳይሆን በጠላትነት ተፈርጆ በገዛ ሀገሩ እንዲሳደድ ያደረጉትን ጠላቶቹን አንድ በአንድ ለይቶ መታገል አለበት እንላለን።
የአማራ ማህበር በዩኬ በፅንፈኞችና በተረኞች ላይ ተገቢው የትግል አቅጣጫ በመያዝ የሕዝባችን ዘለቂታዊ ሠላም እንዲረጋገጥ በማሳሰብን የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አኑረናል ።
1ኛ. መተከል ላይ በግፍ ተጨፍጭፈውና ታርደው ህይወታቸውን ያጡት ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ፈጣሪ በአፀደ ገነት ያሳርፍልን። በህይወት የተረፉትንም መፅናናትንና ጥንካሬን ይስጥልን። አበው እንደሚሉት የጊዜ እንጂ የሰው አሸናፊ የለውም። የአማራ ደም በእጃቸው ላይ ያለባቸውን ተጠያቂዎች ሁሉ ጊዜው ሲደርስ የገቡበት ገብተን ለፍርድ ለማቅረብ የአማራ ህዝብ የአባቶችህን ዘዴ ተጠቅመህ ልትንቀሳቀስ ይገባል።
2ኛ. የአማራ ህዝብ፣ መንግስት ነኝ ከሚለው አካል ምንም የሚጠብቀውና ተስፋ የሚያደርገው ነገር እንደሌለ አውቆ እራሱን መከላከል ተፈጥሮአዊ መብቱ መሆኑን እየጠቆምን፣ ስለዚህ አማራው ከራሱ በስተቀር የሚደርስለት ማንም እንደሌለ አውቆና የአባቶቻችንን ጥበብ ተጠቅሞ እራሱን እንዲከላከል እናሳስባለን። በዚህ ጉዳይ ለሚፈጠረው ማንኛውም ቀውስ ተጠያቂው አማራ ጠሉ መንግስት መሆኑን እንገልፃለን።
3ኛ. በአማራነታችው ብቻ ታስረው የሚገኙ የአማራ ጦር መኮንኖች፣ አንቂዎች፤ፓለቲከኛና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ እንጠይቃለን። አማራው በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉትን አደረጃጀቶች አጠናክሮና አቀናጅቶ ነፃነትና ክብሩን እንዲያስመልስ ጥሪ እናቀርባለን።
4ኛ. በአማራነታቸው ብቻ የታገቱትና እስካሁን ድረስ ያሉበት ሁኔታ ከቤተሰባቸውና ከህዝብ ተሸሽጎ ያሉት አማሮች እህቶቻችን ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱና ፍትህ እንዲያገኙ አጥብቀን እንጠይቃለን ።
5ኛ. የአማራ ህዝብ የመከራ ዘመኑን ያረዘመው የመጀመሪያና ዋናው ጠላቱ ብአዴን መሆኑን ተገንዝቦ በጉያው ስር ሆኖ ላለፉት ሰላሳ አመታት ለጠላት እጀታ በመሆን ያገለገለው ብአዴን የተባለ ስብስብ ነው።
ብአዴን/አዴፓ/ የአሁኑ የኦነግ/ኦዴፖ ተላላኪው የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ተብዬው ጥያቄዎቻችንን ይመልስልናል ብሎ አማራ ፈፅሞ እንዳይዘናጋ። ብአዴን አቅሙም ፍላጎቱም የለውም። ብአዴን እስካለ የአማራ ውርደት ይቀጥላል።
የአማራ ህዝብ የተላላኪዎችን ስብስብ ከጫንቃው ላይ አሽቀንጥሮ ጥሎ በእውነተኛ ልጆቹ ለመተካት በሰላማዊ እንቢተኝነት ታግለህ በአሸናፊነት ለመወጣት ዘዴ እንድትቀይስ እናሳስባለን።
6ኛ. በእነ እስክንድር መታሰር የአዲስ አበባን ህዝብ ወደራስ ፖለቲካ ለማምጣት መሯሯጥ ከትዝብት ያለፈ ፖለቲካ ትርፍ እንደማያመጣ እየገለፅን እንዲሁም የአዲስ አበባን ህዝብ እንደማያገናዝብ ማሰቡ እራሱ ወንጀል በመሆኑ እናወግዛለን።
7ኛ. አቶ ልደቱ አያሌው ረዘም ያለ የፓለቲካ ልምድ እና ብቃት ያለው መሆኑን እንገነዘባለን። ይህን ሰው በማይመስል ክስ ቢጤ አስሮ ህክምና እንዳያገኝ ማድረግ በፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ላይ ከተፈፀመው በደል ጋር ይመሳሰላል። ስለዚህ ፍትህ አግኝቶ እንዲታከም እንጠይቃለን ።
የአማራ ማህበር በዩናይትድ ኪንግደም
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
መስከረም 2013 ዓ.ም