ቀን:ሰኔ 27/2012 ዓ.ም
‘ከድጡ ወደ ማጡ’
ከሩብ ምዕተ አመታት በላይ የኢትዮጵያን ታሪክ ሲያንቋሽሽ፤ሲያረክስ፤ በፋሽስት ወረራ ወቅት ተወጥኖ የነበረውን ፤ቋንቋንና ጎሳን መሰረት ያደረገ ያፈና ሥርአት ዘርግቶ፤ሕዝብ ፤ሲፈጅ፤ሲያስር፤ሲያሰቃይና ወጣቱን ለስደት ሲዳርግ የነበረው አርመኔያዊ የትነግ አገዛዝ፤በሕዝባዊ አመጽ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም መገርሰሱ አይካድም።ይህንን አስከፊ ሥርአት ያለማቋረጥ በመታገል ፤ ረገድ የአማራ ሕዝብ ከማንም የበለጠ ከፍተኛ መስዋእትነት መክፈሉ የሚካድ አይደለም።
ይሁን እንጅ አማራው ጥቅሙን የሚያስከብሩለት ሐቀኛ መሪወች አልባ በመሆኑ፤ታግሎ ያመጣውን ድል ተነጥቆ ፤ነገሩ ሁሉ ‘ከድጡ ወደ ማጡ’ ሆኖበት ፤ለሁለተኛ ዙር ዘመነ መከራ ለባለተረኛው ኦነግ መር አገዛዝ ተዳራጓል። ኢትዮጵያ ያያሌ ነጋዶች የጋራ ቤት ሆና ሳለ፤ተረኛው አገዛዝ በሁሉም መስክ የኦሮሞን የበላይነት ለማሳፈን ሌት ተቀን በመሥራት ላይ ነው።ይህን አላማውንም ለማሳካት ፤ የአገሪቱን አስተዳደራዊ መዋቅር እየጠቀለለ በመያዝ ላይ ይገኛል። ብአዴን ፣ አዴፓን ፣ ዛሬም እንደ ትነግ እየተጠቀመበት፤ አማራን ተወካይ ያለው ቢያስመስልም፤እውነታው ግን አማራው እንደትናንቱ መሪ አልባ መሆኑ ግልፅ ነው።
“ትጥቅ አስፈችም ሆነ ትጥቅ ፈቺም የለም” ያለው ኦነግ ፣ አማራ እና ኢትዮጵያን ጠል በሆነ የፖለቲካ መሰረት ላይ የተደራጀው የኦነግ ሰራዊት ፣ ከጽፅንፈኛው ቄሮ ጋር ጣምራ በመፍጠር ከ15 ሚሊዮን በላይ የሆነ አማራ በኦሮሚያ ክልል በሚባለው በሚኖርበት አካባቢ ሁሉ ተዘርዝሮ የማያልቅ መከራ እየተፈጸመበት ነው።
የሰኔ ወር ይዟቸው የሚመጣቸው ክስተቶች፤ የባለተረኛው አገዛዝ ልዩ መገለጫወች ሲሆን ፤ የዘንድሮው ሰኔ 22 ፤ በኦሮሞ ፅንፈኛች እና የኢትዮጵያን አብሮነት ወይም አንድነት በማይፈልጉ ቡድኖች በተቀነባበረ ሴራ በታዋቂው ድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈፀመው አሳዛኝ ግድያ አንዱ ማሳያው ነው ።
በሌላ በኩል፤ ከዝሁ አሳዛኝ ክስተት ጋር በተያየዘ፤ ዛሬም ‘ከጦስ ዶሮነት’ ያለወጣው አማራው ወገናችን በኦነግ ሸኔና ፅንፈኛ በሆነው የቄሮ ቡድን ከአዲስ አበባ ጀምሮ ኦሮሚያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዘግናኝ ግፍ እየተፈጸመበት ይገኛል። የተረኛው ኦነግ መር አገዛዝ፤ የኦሮሞን የበላይነትን የማስፈን አላማውን ከሰሞኑ ክስተት ጋር አያዞ እያሳየ ነው። በሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ታዋቂ የሆነውና የባልደራስ መሪ የሆነውን እስክንድር ነጋንና ተቀናቃኙ የሆኑትን እንደ እነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፤ ልደቱ አያሌውና የመሳሰሉትን ማሳርና ማሳደድ ጀምሯል። ኢትዮጵያውያን ላይ እየተካሄደ ያለው የዘር ፍጅት በሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ምክንያት የተፈጠረ ክስተት ብቻ አይደለም።
የሐጫሉ ግድያ በአማራ ላይ ለሚካሄደው የዘር ፍጅት ሰበብ እንጂ ምክንያት አይደለም። ቄሮ የሚባለው የወጣቶች ድርጅት በአማራ ላይ እያካሄደው ያለው የዘር ፍጅት መንስዔው ዘር ማጥፋትን እንደ ዋና ዓላማ የያዘው የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ ነው።
ቀደም ሲል በማስጠንቀቂያ ጀምሮት የነበረውን ፣ አማራውንም ተቋም አልባ የማድረግ ዘመቻውን የአሥራት ቴሌቪዥን ጣቢያን በመዝጋት ጀምሮታል።
ፅንፈኛ የሆነውና አሸባሪው የቄሮ ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ በአማራው ላይ እየፈጸመው ካለው ግፍ አልፎ ድንበር ተሻጋሪነቱንም እያሳየ ነው። የኦሮሞ ፅንፈኞች ከሁለት አመታት በፊት እዚህ ለንደን ውስጥ ተሰባስበው ፣”ኢትዮጵያ መፈራረስ አለባት” ውሳኔ አሳልፈው እንደነበር ይታወሳል፤ ሰሞኑን ደግም የዛ እኩይ ዘመቻቸው ቀጣይ የሆነ ፤ወደ አለማቀፋዊ ሽብርተኝነት እየተሸጋገረ ያለውን ፅንፈኛ የሆነውን ቄሮ በማስተባበር ፤እዝህ በታላቋ በርታኒያ የሚገኘውን የቀዳማዊ ሀይለ ስላሴን ሀውልት ያፈረሰ ሲሆን፤ በሎንደን ኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ይውለበለብ የነበረውን ሰንደቅ አላማ በማውረድና የኦነግን አርማ በመተካት ጥላቸውን ከማሳየቱም በላይ፤ተሰልፎ የመጣው ጀሌ ከመንጋ ባልተለየ ሁኔታ ‘ነፍጠኛ ዋ!ዋ!ዋ!’ እያለ የጥፋት ደወል ምልክቱን አሰምቷል። ይህ ድርጊቱ ከእንግሊዝ ህግ እንደማያመልጥ ብናውቅም ፤ በአገርቤት ያለው አማራው ወገናችን ምን ያህል ያልተነገረ ግፍ እየተፈፀመበት መሆኑንን አመላካች ነው።
በመሆኑም የዩኬ አማራ ማሕበር የሰሞኑን ክስተቶች በጥሞና ከመረመረ በኋላ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል:
፩.በአማራ ሕዝብ ላይ የሚደረገው፤ ግድያ፤ እስር፤ መፈናቀል ውድመትና ዘረፋ በአስቸኳይ እንዲቆምና ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ። ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብም ለተጠቂው አማራውም በግልፅ ወንጀለኛቹ በፍትህ አደባባይ ላይ ቀርበው እንዲታዩ ማድረግ።
፪.በአገር ውስጥ ያሉ የአማራ ፖለቲካ ፓርቲወች ፤ የወጣቶች፤ የሴቶች ድርጅቶችና የሙያ ማሕበራት፤ የጋራ ግንባር በመፍጠር ሁኔታወች እየከፉ ሳይሄዱ መክቶ ለማስቆም በሚያስችል ሁኔታ የተቀናጅ ተግባር እንዲያከናውኑ ።
፫.በአማራው ሕዝባችን ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ ለአለም አቀፉ ማህበረስብ ማሳወቁ መቀጠል ያለበት ቢሆንም ፤ የወደፊት የአማራ ሕልውና የሚረጋገጠው በራሱ በአማራው ብቻ በመሆኑ፤ በውጭ ያሉ አማሮችና ትውለደ አማሮች፤ በአንድ አለማቀፋዊ የአማራ ግብረ ሀይል ሥር በመሰባሰብ፤ ለሕዝባችን እንድንደርስለት ።
፬.በውጭው አለም እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ የአማራ ማህበራትና ድርጅቶች፤ ሕዝባችን ያለበትን አስከፊ ሁኔታ በመረዳት፤ አለምአቀፋዊ ጥምረት በመፍጠር ፤ ወጥ በሆነ አመራር ተጨባጭ የሆነ ተግባር ማከናወን እንድንጀምር፤፣
፭.በውጭው አለም የሚገኙ የአማራ፤የዜና አውታሮች(ሚዲያወች)ና የማሕበራዊ አንቂወች የጋራ ግምባር በፈጠር ፤ በአማራ ጠል ሀይሎች በአማራ ማንነትና ታሪክ ላይ የሚያካሂዱቱን፤ የሀሰት ፕሮፓጋንዳና ውዥንብር ለመመከት በጋራ እንዲሱሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
“በህወሓትና ኦነግ ተዘጋጅቶ አማራ የሚባልን ብሄር በጠላትነት ፈርጆ ለ30 ዓመታት ስራ ላይ ያለው ህገመንግስት” በስራ ላይ እስካለ ድረስ አማራን የማጥቃቱና የማሳደዱ ስራ በመንግስት የተደገፈ ነው። በመሆኑ በየትኛውም አካባቢ የምትገኙ አማራዎች ራሳችሁን ከጥቃት እንድትታደጉ ማሳሰብ እንወዳለን!!!
የአማራ ማሕበር በዩናይትድ ኪንግደም