በሰኔ 15ቱ የባለስልጣናት ግድያ ተጠርጥረው 2 ዓመት ከ8 ወራት በላይ በባህር ዳር ሰባታሚት ማ/ቤት በእስር ላይ የከረሙት የጦር መኮንኖችና የአማራ ልዩ ኃይል አባላት
የካቲት 29 ቀን 2014 በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርበው የተፈረደባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

በሌሉበት የተከሰሱትን 3 ሰዎችን ጨምሮ በድምሩ በ31 ተከሳሾች ላይ ነው ፍርዱ የተሰጠው።

በዚህም በሌሉበት የተከሰሱት:_
ሀ)
1) ሻምበል መማር ጌትነት፣
2) አስር አለቃ ልቅናው ይሁኔ እና
3) ኮንስታብል በላይሰው ሰፊነው
ዕድሜ ልክ ተፈርዶባቸዋል።

ለ) 20 ተከሳሾች 16 ዓመት ከ6 ወር፣
ሐ) 3 ተከሳሾች 15 ዓመት፣
መ) 2 ተከሳሾች_አምሳ አለቃ አበበ መልኬ እና ሻምበል ውለታው አባተ 16 ዓመት፣
ሠ) ሻለቃ አዱኛ ወርቄ 17 ዓመት፣
ረ) 2 ተከሳሾች ደግሞ 18 ዓመት በድምሩ በ31 ተከሳሾች ላይ ፍርድ ተሰጥቷል።

“ፍርዱ በእጅጉ አሳዛኝና አሳፋሪ ነው፤
በጅምላ ነው የተሰጠው” ያሉት የጦር መኮንኖቹ “በአማራ ምድር ላይ ይህ ይሆናል ብለን አናስብም ነበር” ሲሉ በፍርድ ሂደቱ ላይ ቅሬታቸውን ለአሚማ ገልጸዋል።

በወያኔ ዘመን ከነበረው የፍትህ አሰጣጥ ሂደት የተለዬ ያልሆነ የጅምላ ፍርድ መሆኑን ደግመን አይተንበታል፤
ፍርዱን ከፈጣሪ ነው የምንጠብቀው ብለዋል።

የመጀመሪያዎቹ ዳኞች ሶስት ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን በዋና ወንጀል አድራጊነት የለዩ ቢሆንም ተቀይረው የመጡት ዳኞች ሌሎችንም በመጨመር በዋና ወንጀል አድራጊነት ሲያካትቱ ለመቅጣት እንደተፈለገ ቀድመን ተረድተነው ነበር ብለዋል ለአሚማ ባደረሱት መልዕክት።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator