============== /ክፍል-አንድ/ =============

የአንዳርጋቸው ፅጌ ጓንትና መልዕክት አስተላላፊ የሆነው ፋሲል የኔዓለም (የአምስተርዳሙ-መስፍን-በዙ)፥ ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንድ ፅሁፍ በፌስቡክ ገፁ ለጥፎ ነበር።

የፅሁፉ ይዘት የእበላ-ባይነት ጥግን ከድንቁርና ጋር ያወዳጀ መሆኑ ሳያንስ፥ ገና ከመግቢያው ድምዳሜ ላይ የደረሰበትን “ኦህዴድ መራሹ መንግስት ኦሮሙማን ለማስፋፋት እየሰራ ነው” የሚለውን ያገጠጠ እውነት፥ እንደማይቀበለው ፍርጥም ብሎ ይገልፅና፥ ከታች ወረድ ብሎ “የኦሮሙማ ትርጉሙ ባይገባኝም” በሚል ከመነሻው ያሳየውን የእግጠኛነት-ድምዳሜ ጥያቄ ውስጥ ይከትተዋል። ከዚያም ለእሱ ክህደት fit የሚያደርግ “የኦሮሙማ ትርጉሙ እንዲህ ማለት ከሆነ…….” ብሎ፥ አዲስ argument የእሱን ድምዳሜ ሊያጠናክር በሚችል መልኩ reconstruct ያደርጋል። “ትርጉሙ አይገባኝም” ያለውን ነገር፥ የቢሆን ትርጉም በመስጠት፥ “ሰዎች እንዲህ ይላሉ” ያለውን ሀሳብ disprove ለማድረግ መሄድ፥ ከፍ ሲል እበላ-ባይ ባንዳነት ዝቅ ሲል ደግሞ ድንቁርና ነው። ለማንኛውም በእነአንዳርጋቸው ፅጌ እየተዘጋጀ በእነ ፋሲል የኔዓለም የሚረጨውን መርዝ በምክንያት እና በዕውቀት መሞገት ግድ ይላል። ሁለት ነገሮች ላይ እናተኩራለን፦

  1. ኦሮሙማ ማለት ምን ማለት ነው?
  2. ኦሮሙማን በአዲስ አበባና በሀገሪቱ ለማንበር እየተሰራ ነው? ወይንስ አይደለም? የሚለውን የምናይ ይሆናል መልካም ንባብ‼‼
  3. “ኦሮሙማ” ማለት ምን ማለት ነው?
  • ለኦሮሞ ምሁራን ካለኝ አድናቆት አንዱ ምክንያት፥ በኦሮሞ ብሔርተኝነት እና በኦሮሞ ፖለቲካ ዙሪያ ከበቂ በላይ መፅሐፎችን መፃፋቸው ነው። ብዙ ነገሮችን አቅልለውልናል።

ከእነዚህ ምሁራንና የኦሮሞ ብሔርተኝነት ideologue መካከል፥ ኦሮሙማን theorize እና conceptualize በማድረግ ከጥናታዊ ፅሁፍ እስከ መፃሀፍት ማሳተም የደረሰው ዶክተር አሰፋ ጃለታ አንዱ ነው።

እ.አ.አ ከኦገስት 1 እስከ ኦገስት 2, 2015 ዓ.ም፥ በዋሽንግተን ዲሲው የሃዋርድ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ በተደረገው 29ኛው የኦሮሞ የጥናት ማዕከል አመታዊ ኮንፍረንስ ላይ፥ ጥናታዊ ፅሁፎቻቸውን ካቀረቡ የኦሮሞ ምሁራን መካከል “THEORIZING OROMUMMAA” በሚል ርዕስ ባለ40 ገፅ ፅሁፍ ያቀረበው ዶክተር አሰፋ ጃለታ ነው።

ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ ከመውጣቱ ስምንት አመት ቀደም ብሎም፥ እ.አ.አ በኤፕሪል 14, 2007 ዓ.ም የኦሮሞ ጥናት ማዕከል በዋሽንግተን ባደረገው የግማሽ-ዓመት ስብሰባ ላይ “Oromo National Political Leadership: Assessing the Past and Mapping the Future” በሚል ርዕስ “ኦሮሙማ” ማለት ምን ማለት እንደሆነ አብጠርጥሮ የተነተነው ሲሆን፥ ይህንን ፅሁፉንም፥ ከአሜሪካዊው ሔርዉድ ሼፈር ጋር በመሆን፥ “The Journal of Oromo Studies” በተሰኘው የጥናት ማዕከሉ መፅሔት ቅጽ 14, ተራ ቁጥር 1, 2007 ላይ አሳትሞታል።

በዚህም ሳይወሰን፥ “OROMUMMAA: Oromo Culture, Identity and Nationalism” የሚል መፅሐፍም አሳትሟል።

ስለሆነም፥ “ኦሮሙማ” የሚባለው ነገር፥ በኦሮሞ ልሂቃን coined, conceptualized and theorized ተደርጎ በአግባቡ የተተነተነና የተሰነደ ጉዳይ እንጂ፥ ደረጄ ሀብተወልድ የተባለ ኔዘርላንድ የሚኖር ገሪባ እንደሚለፈልፈው፥ “ኢትዮ-360” የተሰኘው ሚዲያ የፈጠረው አይደለም‼ አልያም ኮልኮሌ ብአዴናዊያን፥ “ፅንፈኛ የአማራ ብሔርተኞች” እያሉ የሚፈርጁን እኛ የፈጠርነው አይደለንም‼ወይም ተላላኪው ፋሲል የኔዓለም ” ኦሮሙማ የሚባለው ነገር አይገባኝም” ብሎ የማይጨበጥ የማይዳሰስ አስመስሎ እንደነገረን ያለ ጉዳይ አይደለም‼ በመሆኑም የኦሮሞ ልሂቃን conceptualize and theorized ወዳደረጉት የኦሮሙማ ትርጉም በቀጥታ እንገባለን።

በኦሮሞ ብሔርተኞች ልሂቃን ትንታኔ መሠረት፥ “ኦሮሙማ” አምስት /5/ እርከኖች አሉት፦

  1. መሠረታዊ ኦሮሙማ (Basic or apolitical Oromummaa)
  2. ብሔርተኛ የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ኦሮሙማ (Nationalist Political Ideology)

3.ህፅበተ-አዕምሮ የመፈፀሚያ ዕውቀቶች ክምችት ኦሮሙማ

  1. ብሔራዊ ፕሮጀክት ኦሮሙማ
  2. አለማቀፋዊ ተልዕኮ (Global mission) የሰነቀ አለማቀፍ-ኦሮሙማ (Global Orommuma) በመባል ይከፈላል።

የኦሮሞ ብሔርተኛ ልሂቃን አምስቱንም የኦሮሙማ አይነቶችና እሳቤዎች የተነተኑበትን ዝርዝር እንደሚከተለው እንመለከታለን።

  1. መሠረታዊ ኦሮሙማ (Basic or apolitical Oromumma)፦
  • “በሌላ ባህል፣ ቋንቋ፣ ወግ ያልተዋጠና የኦሮሞን ቋንቋ፣ ባህል፣ ወግ፣….የሚናገርና manifest የሚያደርግ ማንኛውም የኦሮሞ ተወላጅ፥ መሠረታዊው ኦሮሙማ (basic Oromumma) አለው ማለት ነው” ይለናል ዶክተር አሰፋ ጃለታ “Theorizing Orommuma” በተሰኘው ጥናታዊ ፅሁፉ። በአጭሩ ይህ “መሠረታዊ ኦሮሙማ” የሚባለው “ኦሮሞነት” በመባል የሚገለፀው፥ ከፖለቲካ ጋር ንክኪ የሌለውና የኦሮሞ ህዝብ መገለጫዬ በሚላቸው በቋንቋ፣ ወግ፣ ባህል፣ ልማድ ……… የሚገለጽ ነው።
  • አንዳንድ ጥራዝ ነጠቆች፥ እኛ “ኦሮሙማ” ስንል፥ የቃሉን ጥሬ ትርጉም ወይም የኦሮሞ ብሔርተኛ ልሂቃን “basic Orommuma” ብለው በሰየሙት ትርጉም ልክ ብቻ በመውሰድ፥ ሰፊውን የኦሮሞ ህዝብ እየተቸን አልያም ጥላቻ በህዝቦች መካከል እየረጨን አስመስለው ሊያቀርቡ ይሞክራሉ። ይህ ፈፅሞ ስህተት ነው‼‼‼ ለሰፊው የኦሮሞ ህዝብና መገለጫ ቋንቋ፣ ባህል፣ወጉና ልማዱ ትልቅ አክብሮት አለን‼‼ የትናንትን ታሪክም በዛሬ ሚዛን የማንለካ የፍርድ አዋቂዎቹ ልጆች ነን‼
  1. ብሔርተኛ የፖለቲካ አይዲዮሎጂው ኦሮሙማ (Nationalist Political Ideology)
  • ይህ ሁለተኛው እርከን ኦሮሙማ purely political ነው። ራሱን manifest የሚያደርገው ልክ እንደ ፋሽዝም፣ እንደ ናዚዝም አንድ የብሔርተኛ የፖለቲካ አይዲዮሎጂ ሆኖ ነው።
    የዚህ አይዲዮሎጂ መሠረታዊ ሀሳብንም ዶክተር አሰፋ ጃለታ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፦ “At the second level, Oromummaa is seen as a nationalist ideology that attempts to mobilize the entire Oromo people to restore their national culture, history, identity, language, human dignity, and freedoms that Ethiopian colonialism has destroyed or suppressed for more than a century.” ግርድፍ ትርጉሙም “ሁለተኛው እርከን ኦሮሙማ፥ መላው የኦሮሞ ህዝብን በማንቀሳቀስ በኦሮሞ ላይ የተጫነው የኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ከመቶ አመታት በላይ ያጠፋውንና የጨቆነውን የኦሮሞን ባህል፣ ታሪክ፣ ማንነት፣ ቋንቋ፣ ሰብአዊ ክብርና ነፃነት ለማስመለስ የሚያገለግል ብሔርተኛ አይዲዮሎጂ ነው”
  • አሰፋ ጃለታም ሆነ መሰል የኦሮሞ ልሂቃኖች “ኢትዮጵያ ቅኝ ገዢ ናት” የሚለው ትርክታቸው ጭምብሉ ሲገለጥ “አማራ በምኒልክ በኩል ቅኝ ገዢ ነው” ማለታቸው ሲሆን፥ ኦህዴድም የዚህ ትርክት ተጋሪ በመሆኑ፥ በኦህዴድ ተደርሶ ዛሬም በተግባር እየተዘመረ ያለው የኦሮሚያ ክልል ብሔራዊ መዝሙር በኦሮምኛ ቋንቋ እንዲህ የሚል ስንኞችን ይዟል፦

“Xurii bara dhibba dhiigaan sirraa dhiqnee
Wareegama qaaliin alabaa kee ol qabne
Gammanne gammadii bokkuu deebitannee”

ትርጉሙም፦ “የመቶ ዓመት እድፍ በደማችን አጠብንልሽ፣
በብዙ እልፍ እልቂት ባንዲራሽን ከፍ አደረግን፣
ደስ ብሎናል ደስ ይበልሽ ስልጣንን መልሰን አገኘን።”

=> የአሰፋ ጃለታ የመቶ ዓመት የቅኝ ግዛት ትርክትና ኦህዴድ “የኦሮሚያ ብሔራዊ መዝሙር” ብሎ በቋጠረው ስንኝ ውስጥ ያለው “የመቶ ዓመት እድፍ” ትርጉም አንድና ያው ሲሆን መሠረቱም ከ political oromumma አይዲዮሎጂ የተቀዳ ነው‼

አሰፋ ጃለታ፥ “nationalist ideology” ነው በማለት የገለፀው “Political ኦሮሙማ” ወይም “2nd level Oromumma” ፥ በዛሬው የአብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ የሚዘወረው ኦህዴድ-መሩ “ብልፅግና” የሚባለው ጭምብል core ideology መሆኑን ለማወቅ፥ የሽመልስን ንግግሮች ወደኋላ መለስ ብሎ ማየቱ እንደተጠበቀ ሆኖ ኦህዴድ ዘጠነኛ ጉባኤውን በጅማ ከተማ ባደረገ ጊዜ በግላጭ የፖለተካ ርዕዮቱ ኦሮሙማ መሆኑን አውጇል።

ይህ political ideology ደግሞ፦

ሀ. አማራን በግላጭም በተዘዋዋሪም በቅኝ ገዢነት ፈርጆ ይነሳል፤

ለ. “ቅኝ ገዢ” በሚላት ኢትዮጵያ ላይ revisionist and revanchist state ሆኖ መቀመጥ ይፈልጋል። ይህንንም ለማስፈፀም established የሆነውን የሀገሪቱን የታሪክና የፖለቲካ ትርክት በማፍረስና በራሱ ትርክት በመተካት ላይ መጠመድን ዋነኛ ስራው አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

*የእኔና መሰል ወንድሞች ሙግትና ፀብም ከዚህ ጠባብ፣ ፋሽስታዊ፣ revisionist, revanchist እና anarchic ከሆነው አይዲዮሎጂ /Political Oromumma/ ጋር ነው። የዚያች ሀገር ዕጣ ፈንታ በዋናነትም የአማራ ህዝብ እንዴት አይነት የህልውና አደጋ እንደተጋረጠበት የምታውቀው ደግሞ ፥ የዚህን ፋሽስታዊ አይዲዮሎጂ መዳረሻ አሰፋ ጃለታ ፍኖተ-ካርታውን በዚህ መልክ ፅፎ፦ “At this level of Oromummaa, Oromo political awareness is transformed into Oromo nationalism and enables Oromo individuals, families, groups, and communities to comprehend the illegitimacy, evilness, and criminality of Ethiopian colonialism and to struggle for their national liberation.” በእነአብይ አህመድ መሬት የረገጠ ስራ ሲሰራበት ስታይ ነው።

:
:
:
:
:
:
:
=============ይቀጥላል==========

ዴቭ ዳዊት።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator