የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዋጋው መንበር እንደገለጹት የእውቀት ማዕድ የሚፈልቅባቸውን የትምህርት ተቋማቶች የጅምላ መቃብር ፈጽሞባቸዋል።

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በወረዳው ውስጥ ወሯቸው በነበሩ 85 የትምህርት ተቋማት ላይ ዘረፋና ውድመት ከመፈጸም ባሻገር ተማሪዎች ህጻናት ተማሪዎች ቀብር ፈርተው ትምህርት እንዳይገቡ ያደረገው የአስከፊነት ጥጉ አንዱ አካል ነው ብለዋል አቶ ዋጋው መንበር።

በመቄት ወረዳ የደብረ ዘቢጥ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት የጅምላ ቀብር የተፈጸመበት ት/ቤት አንዱ የደብረ ዘቢጥ የመጀሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት ሲሆን በአካባቢው ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴትን በጣሰ መልኩ የተማሪዎች የእውቀት መቅሰሚያ በመቃብር አጥሯቸው መሄዱ የሚያሳዝን ነው ብለዋል።

ት/ቤቱን ወደ መደበኛ ስራው ለማስገባት የትምህርት ቤቱን አካባቢ ከቀብር ነጻ አድርገን ተማሪዎቻችንን ለማስተማር ተዘጋጅተናል ብለዋል የደብረ ዘቢጥ ነዋሪዎች።

በተመሳሳይ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይል ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ዘረፋና ውድመት ፈጽሟል ሲል በሰሜን ወሎ ዞን የዋድላ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አስታውቋል።

የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋየ ፈንታሁን እንደገለጹት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይል ወረዳውን ተቆጣጥሮ በነበረብት ወቅት በሆስፒታሉ ላይ ከፍተኛ የንብረት ዘረፋና ውድመት ፈጽሟል።

ሆስፒታሉ ከ200ሽህ ህዝብ በላይ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን በወራሪው ሃይል 42ሚሊዮን 500ሽህ ብር የሚገመት ንብረት ዘረፋና ውድመት ተፈጽሞበታል።

በአሁኑ ወቅት ሆስፒታሉ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት የማይችል በመሆኑ ድንገታዊና ተከታታይ ህክምና የሚፈልጉ ዜጎች እየሞቱና በበሽታ እየተሰቃዩ ይገኛሉ ያሉት አቶ ተስፋዬ ሆስፒታሉ ወደ መደበኛ ስራው ተመልሶ በበሽታ የሚሰቃዩ ዜጎችን ለመታደግ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ማንኛውንም ድጋፍ እንዲያደርጉለት ጠይቀዋል።

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator