0 0
Read Time:46 Second

በጎጃም ቢቡኝ ወረዳ አንድ ፋኖ በመንግስት አካላት ተገደለ፤ በፋኖ ስምም ሌላ የ13 ዓመት ልጅን በጥይት ስለመግደላቸው ተገልጧል።

ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት በምስራቅ ጎጃም ዞን፤ ቢቡኝ ወረዳ፤ የወይን ውሃ ከተማ አቅራቢያ፣ የ13 ዓመት አዳጊ ልጅን ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ተገድሏል።

“ፋኖ ነህ” በሚል በ3 ጥይት ተደጋግሞ ቤት ውስጥ በመደብደብ ነበር ሕፃኑ የተገደለው። ሟቹ የ4ኛ ክፍል ተማሪ ስለመሆኑ ተገልጧል።

በተመሳሳይ፣ በዚያው በቢቡኝ ፋኖ አወቀ መንጌ ከሕፃኑ መሰዋዕት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ በፖሊስ ተገድሏል።

ይህ ግድያ በሜዳ ላይ ሲፈፀም የተመለከተው ሕፃን ድርጊቱን ለመናገር ሩጦ ወደ ቤት ሄዷል።

ይህን ተከትሎ፣ ታጣቂዎቹ በጥይት ተኩስ እያባረሩ ተከትለውት ከቤት ገብተዋል።

ቤት ውስጥም ደጋግመው በቤተሰብ አባላትና በጎረቤት ፊት በጥይት በመደብደብ ገድለውታል።

አስክሬኑን ጎትተው ከቤት አውጥተው በር ላይ በመጣል “ተባራሪ ጥይት ገደለው በሉ” የሚል ማስጠንቀቂያ ተናግረው እንደሄዱ የቤተሰቡ አባላት ገልፀዋል።

የፋኖ አወቀ መንጌ እና የሕፃን ልንገረው አዲስ የቀብር ስነ ስርዓት በዚያው በተሰውበት ዕለት፤ በተገደሉበት ስፍራ ማለትም በቢቡኝ ወረዳ፤ በደብረ ሲና አስማረ ቀበሌ፤ በጋፋት ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።
ዘገባው የባልደራስ ነው።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator