በኮምቦልቻ ከተማ የጅምላ መቃብር ተገኘ።
አሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ኃይል በከተማዋ ዘረፋ ፈፅሟል የማይፈልገውን ደግሞ በቻለው አቅም አውድሟል።
የሽብር ቡድኑ በዘረፋቸው ተቋማት ግቢ ውስጥም ጅምላ መቃብር ተገኝቷል።
የኮምቦልቻ ምክትል ከንቲባ አህመድ የሱፍ “በከተማችን የተለያዩ ቦታዎች በርካታ ንፁሃን ሰዎች በግፍ ተረሽነዋል ደብዛቸውም ጠፍተዋል” ያሉ ሲሆን “በከተማ የተለያዩ ተቋማት የጅምል መቃብር ተገኝተዋል” ብለዋል።
ዝርዝሩን መንግሥት አጥንቶ ለከተማው ማኅበረሰብም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚገለፅ ይሆናል ሲሉ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል።
ዋልታ ቴሌቪዥን በኮምቦልቻ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ የጅምላ ቀብርና ለቀብር መቆፈሪያና አፈር መመለሻ የዋለ ኤክስከባተርን ተመልክቷል።
ለጅምላ መቃብር ተቆፍሮ የተዘጋጀ ጉድጓድንም አይቷል።
እስካሁን ባለው ሂደት የጅምላ መቃብሮቹ በኮምቦልቻ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ፣ በቃሉ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅና የተለያዩ አካባቢዎች እንደማገኙ የአይን እማኞች ተናግረዋል።
ወራሪ ኃይሉ በኢንደስትሪ ከተማዋ ኮምቦልቻ በቆየበት አንድ ወር ከአንድ ሳምንት ተቋማትን አውድሟል፤ ዘረፋ ፈፅሟል፤ ሴቶችን ደፍሯል ንፁሃንን ገድሏል።
በከተማዋ የሚገኘውን የደረቅ ወደብ ተርማሚናል ከ800 በላይ ኮንቴነር ሙሉ ዕቃ ጭኖ ወስዷል።
በከተማዋ ከሚገኘው በተለምዶ ጢጣ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ባለ የነዳጅ ማጠራቀሚያ በየቀኑ በቦቲ ጭኖ ይወሰድ እንደነበር የአይን እማኞች ለዋልታ ተናግረዋል።
አሸባሪው ቡድን የኮምቦልቻ ማረሚያ ቤትን ሙሉ ለሙሉ በማቃጠል ማውደሙን ዋልታ አረጋግጧል።