ቀን: እሁድ, 15 ኖቬምበር 2020
በአማራ ማህበር ዩናይትድ ኪንግደም የተጠራ የተቃውሞ የዙም ሰልፍ ላይ በአለም አቀፍ አማራና የአማራ ወዳጅ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠ የአቋም መግለጫ
በአማራ ማሕበረሰባችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ዘመቻ ለመቃወም የወጣው የአማራ ልጆች እና አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥተናል ።
1). በኢትዮጵያ መንግሥት የተደገፈውን የአማራን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ; ማፈናቀል እና ማሳደድ በአስቸኳይ እንዲቆም እና በዚህ የሰብአዊ መብት ጥሰት የተሳተፉ ወንጀለኞች የኦሮሞ, የትግራይ አክራሪዎች እና የብልፅግና ፓርቲ የመንግሥት መዋቅር አካላት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንጠይቃል
2). በዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል ውስጥ የተሳተፉ የኦሮሞ ነፃአውጭ ግንባር (ኦነግ) እና ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) አክራሪ የፖለቲካ አደረጃጀቶች እና ግለሰቦች በቴረሪስት መዝገብ ውስጥ እንዲገቡና ከማንኛውም ሰላማዊ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲታገዱ እንጠይቃል
3). ከመንግሥት ተፅእኖ ነፃና ገለልተኛ የሆነ ጠንካራ አካል ተደራጅቶ; በማንነታቸውና በእምነታቸው በሃይማኖታቸው ተለይተው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ወንጀል የተፈፀመውን እንዲመረመር እና ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃል
4). ከክልሉ ውጭ የሚገኘው አማራ ሕገ መንግስታዊ ውክልና እንዲኖረው እና በአገሩ ሙሉ መብት ኖሮት እንዲደራጅ ፣ እንዲሁም የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ተከባብሮ ከሁሉም ማሕበረሰብ ጋር; በጋራ የሕግ የበላይነት ተከብሮ ሁሉም ዜጋ ከሕግ በታች ሆኖ የሚተዳደርበት ሕገ መንግሥት እንዲተካ እንጠይቃለን።
5). በአማራው ህዝብ ላይ ያለውን የዘር ማጥፋት አደጋ ግምት ውስጥ በማስገባት በየትኛውም ክልል ያለው አማራ እራሱን መከላከል እንዲችሉ እንዲደራጅና ታጥቀው እራሳቸውን እና አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ መንግስት እንዲወስን እናሳስባለን
6). በኦሮሚያ ክልል ፣ በቤኒሻንጉል-መተከል ፣ ጉራፈርዳ ፣ ወለጋ-ሆሮጉድሩ; ወልቃይት-ማይካድራ ፣ እንዲሁም መከላከያ ውስጥ ያሉ የአማራ ተወላጆች ላይ በማንነታቸው የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ወንጀል በእኛው ዘመን የተፈጠረ ትውልድ የማይረሳው የታሪክ ጠባሳ; በአማራ እና በኦርቶዶክስ አማኞች ላይ በሰፊው ተፈፅሟል ፣ ይህንንም መንግሥት አምኖ ጉዳት የደረሰባቸው እና ለተፈነቃሉ አማራና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መንግስት በአስቸኳይ መልሶ እንዲያቋቁማቸውና ካሳ እንዲከፍል; እንዲሁም አለምአቀፍ አጣሪ ቡድኑን ወደቦታው ገብቶ እንዲያጣራና ወንጀለኞችን ለሕግ እንዲቀርቡ እንጠይቃል::
7). ለሞቱት ሰዎች በአጠቃላይ መከላከያ ውስጥ ላሉትም ይሁን መሳሪያ ያልታጠቁ በወልቃይት ማይካድራ ወገኖች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል መከላከያን ከአካባቢው እንዲወጣና የኦነግ ጦር አስገብቶ ሰላማዊ ሕዝብን ማስፈጀትና አልሰማሁም ነበር; በማለት ሲስተማቲክ ዘር ማፅዳት እና ከአውሬ የተረፈን አካል መሰብሰብ ሕዝብን አስተዳድራለሁ ከሚል ከመንግሥት አይደለም ከጠላትም አይጠበቅም ለጠፋው ሕይወት ሁሉ ተጠያቂው መንግስት ነው
8). የብሔራዊ ደህንነት መዋቅሩ ይህ ሁሉ ተንኮል በመከላከያው ውስጥ ሲሰራበት የት ነበር? ፥ የመከላከያው ውስጥ የነበረው የእራሱ ደህንነትስ ምን ይሰራ ነበር ? የት ነበር? ይህ ጉዳይ ከፌደራል መንግስት እስከ ክልል መዋቅር የተንሰራፋ ዘር ተኮር ወንጀል የተፈፀመበት ክህደትና በአማራ ማንነታቸው የታረዱና የአገር ልዋላዊነትን ያስደፈረ በጦር ወንጀለኛነት የሚያስጠይቅ ስለሆነ በገለልተኛ አካል እንዲታይ እንጠይቃለን
9). በወያኔ እና በኦነግ አርባ አምስት አመት በወልቃይት አማሮች ላይ ግድያና ማፈናቀል ሲፈፀም ኖሯል አሁን እስከአሉት መሪዎች ድረስ የአማራ ጀኖሳይድ ፈፃሚና አስፈፃሚዎች በሕይወት ያሉ፣ በስልጣንና በአማካሪነት ስም ተሸፍነው በአማራ ሕዝብ ሥቃይ ላይ ተፈናጠው ቆሻሻ ሥራቸውን ቀጥለዋል; ለምሳሌ፡ ዲማ ነግኦ፥ ሌንጮ ለታ፥ ሌንጮ ባቲ፥ ዳውድ ኢብሳ ወዘተ…
10). በውጭም ሆነ በአገር ውስጥ የሚገኘው አማራ የመኖር አለመኖር ህልውናውን ለማስቀጠል እና የተደቀነበትን አደጋ ለመከላከል በጋራ ተጠናክሮ እንዲደራጅ እራሱን እንዲከላከል, ቀሪውን አጋር ማህበረሰቡን እንዲያነቃ; በአማራው ላይ እየደረሰበት ያለውን ችግር ለአለም አቀፍ ማሕበረሰብ እንዲያሳውቅ እና ድጋፍ እንዲያስተባበር እናሳስባለን::
11). ለመላው ኢትዮጵያዊያን የአማራ ሕዝብ በማንነቱ ተለይቶ በሕይወት የመኖር ተፈጥሮአዊ መብቱ ተገፎ በተገኘበት ቦታ ሁሉ ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ሲጨፈጨፍ ድርጊቱን ለመቃወምና በቃ ለማለት ሰው መሆን ብቻ በቂ ስለሆነ ከዛም በላይ አገር የሚባለው ያለ ሕዝብ ዋጋቢስና ባዶ ስለሆነና, ዛሬ ለአገር ተቆርቋሪ የሆነውን ሰፊው የአማራን ሕዝብ በትብብር ከጨፈጨፉና ካዳከሙ በኋላ ወደሌላው ማህበረሰብ መቀጠላቸው አይቀሬ ነውና በጋራ የጋራ ቤታችንን ከመፍረስ እናድን በመንግስት እውቅና የሚንቀሳቀሱ ስብዕና የጐደላቸው ሰው መሳይ መንጋ አውሬዎችን በትብብር ለፍርድ እናቅርብ
ይህን በመገንዘብ የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ያለውን መንግስታዊ ጭፍጨፋ ለመቃወም የተጠራውን የዙም ሰልፍ በመቀላቀል እንደሰው እንደ ሕዝብና እንደ ሀገር የሚያስተሳስረን አብሮነትና አጋርነታችን እንደ አገር እንዲቀጥል እንጠይቃለን።
የአማራ ሕዝብ በልጆቹ ትግል ነፃነቱን ያስመልሳል!!!!!!!!