0 0
Read Time:58 Second

ሀገር ለማፍረስ አልመው የተነሱት የአሸባሪው ትሕነግና የኦነግ ሸኔ ጥምር ኃይል በአማራ እና በአፋር የተለያዩ አካባቢዎች ግልጽ ወረራ እና ጦርነት ከከፈቱ አንድ ዓመት አልፎታል።

ከህዳር 23 ቀን 2014 ጀምሮ በርካታ አካባቢዎችን ነጻ ያወጣው የወገን ጦር የሚያደርስበትን ጥቃት ለመቋቋም የሽብር ቡድኖች ጥምረት ሙት እና ቁስለኛ ከሆነው ውጭ ብዙዎች እጅ እየሰጡ ነው።

የተረፉት እና መውጫ ያጣው ወራሪ ኃይል ህዳር 25 ቀን 2014 በወረኢሉ ከተማ ዙሪያ፣በአንጾኪያ ገምዛ መኮይ ተራራ አካባቢ፣ በራያ ዞብልና አካባቢው ተኩስ ከፍቶ መዋሉ ተገልጧል።

በደቡብ ወሎ ወረኢሉ ዙሪያ ወደ ግሼ መሀል ሜዳ መውረጃ ኩርፊት ማርያም፣ከታሪ ዋሻና ለገጅዳ አካባቢ ተኩስ መኖሩ ታውቋል።

በተጨማሪ በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ መኮይ ከከተማው ወጣ ብሎ ተራራማ አካባቢዎች ላይ ተኩስ መክፈቱን ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።

ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ ምሽግ እየቆፈሩ መሆኑም ተሰምቷል።

ያገኙትን ሰው በቡድን መሳሪያ በመግደል፣ በማቃጠልና በመዝረፍ የተሸነፉና ተስፋ የቆረጡ መሆናቸውን እያሳዩ መሆኑን የገለጹት ምንጫችን ደግሞ በራያ ዞብልና አካባቢው የሽብር ቡድኑ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ አስረድተዋል።

በራያ አካባቢ ጠላት ከፍተኛ ብዛት ያለው ጦር በማስጠጋት ንጹህ ዜጋን ማፈን ጀምሯል፤ ለምን እኛን ታፍናላቹህ ብለው ጥያቄ ሲያቀርቡም ፋኖንና ሚሊሻውን መንገድ እንዳይዘጋ ካላደረጋቹህ ከዚህም በላይ ሰቆቃ እናደርስባችኋለን እያሉ ጉዳት እያደረሱባቸው ነው ተብሏል።

መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ እንዲያደርግላቸውም ጠይቀዋል።

የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የአማራ ልዩ ኃይልም በአቀስታ በኩል ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ መሆኑ ተሰምቷል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator