0 0
Read Time:31 Second

በግፍ ታስረው የሚገኙ እስረኞች እንዲፈቱ እና በእስር ቤት የሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበር ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ጠይቋል።

ባልደራስ ይህን ያለው በእስር ላይ የሚገኙ የ5 አባላትና ደጋፊዎቹ የእስር አያያዝንና ፍትህ አለማግኘትን በመቃወም ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በጻፈው የአቤቱታ ደብዳቤ ነው።

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በግፍ ታስረው የሚገኙ የባልደራስ መሪዎችን ጠይቀው ሲመለሱ “ፎቶ አንስታችኋል” በሚል ሰበብ ከኅዳር 16 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ አምስት አባላቱ መታሰራቸውን አውስቷል።

እስካሁን ድረስ ያለጠያቂ ቂሊንጦ ክራውን ሆቴል ጀርባ ታስረው እንደሚገኙ የገለጸው ፓርቲው አባላቱ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እና በእስር አያያዛቸው ወቅትም ሰብዓዊ መብታቸው እንዲከበር አሳስቧል።

አባሎቻችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቱ ይገባል ያለው ፓርቲው አቤቱታው የደረሰው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቋል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Translator