0 0
Read Time:1 Minute, 6 Second

ባህርዳር ላይ ላለፉት 3 ቀናቶች ሲካሄዱ የነበሩ የተቃዉሞ ሰልፎችን መንግስት በሃይል ለማስቆም ብዙ መሞከሩ ተነግሯል።

በዚህም የተነሳ እራሱ መንግስት ከተማዉ ላይ የቦንብ ፍንዳታዎች በማድረግ የአማራ ፋኖ በባህርዳርና የከተማዉን ወጣት በድጋሚ ለማሰር አቅዶ እየሰራ መሆኑን መረጃዎች ወጠዋል፤ እንዳሰበዉም ማሰሩን ቀጥሎበታል ተብሏል።

ዉድ ህይወታቸዉን ለሃገር ብለዉ መሰዋት የከፈሉና እየከፈሉ ያሉ ጀግና የባህርዳር ፋኖዎችን ከሰኔ 20/2014 ምሽት ጀምሮ አምስት አባላት መታሰራቸው ተገልጧል።

ከታሰሩት መካከልም:_

1) ፋኖ ማንችሎት እሱባለዉ፣
2) ፋኖ ሃብታሙ ማንደፍሮ፣
3) ፋኖ ቴዎድሮስ ፣
4) ፋኖ ኖላዊት ይልሃል እና
5) መንግስቱ አማረ ይገኙበታል።

ተከሰተው ስለፍንዳታዉ ሃላፊነቱን የሚዎስድ እራሱ መንግስት እንጅ ታሳሪዎች ወይም ፋኖ አይደለም ያለው የአሚማ ምንጭ ይህ ከአሁን ቀደም የተበላበት ነገር ግን አሁንም ድረስ የተለመደ የመንግስት አካሄድ ነው ብሎታል።

በአብዛኞች ፋኖዎች ቤት አካባቢም እንቅስቃሴ እየታዬ በመሆኑ ሁሉም የአማራ ፋኖ በባህርዳር አባል በተጠንቅቅ እንዲጠብቅ የሚል ጥሪ ቀርቧል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር መሰረት ደባልቄ በሰጡት መግለጫ ሰኔ 20/2014 ዓ.ም ምሽት ኅብረተሰቡን ለማሸበር ያለመ ወንጀል መፈፀም የፈለጉ ቀሪ ኀይሎች ሲል ፖሊስ የጠራቸው በባሕርዳር ከተማ በአራት ቦታዎች ላይ ተከስቷል ካለው የቦንብ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ከሕዝብ ጋር በመቀናጀት አድርጌዋለሁ ባለው ክትትል ወዲያውኑ ስድስት፣ ተባባሪ ደግሞ 14 ይዣለሁ፤ የክልልና የፌዴራል የፀጥታ አካላት ምርመራ እያደረጉ ይገኛሉም ብለዋል።

በመጨረሻም አሚማ ያነጋገራቸው ፋኖዎች ይህ የመንግስት የተለመደ የማጥቂያ መንገድ ነው ሲሉ ውድቅ አድርገውታል፤ ይልቁንስ ህዝቡ እንዳይዘናጋ መክረዋል።

ፎቶ 1ኛ_ፋኖ ማንችሎት ከወራቶች በፊት በሞርታር ቆስሎ፣

ፎቶ2 ፋኖ_ማንችሎት አሁንም በ9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የሚገኝ፣

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator