0 0
Read Time:59 Second

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ክሱን በንባብ ያሰማው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብርና የሕገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ነው።

በጋዜጠኛው ላይ ክሱ ሰኔ 21/2014 የተከፈተ ሲሆን ሰኔ 22/2014 ለተከሳሽ ደርሶ በችሎት መነበቡን ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ገልጸዋል፡፡

ዐቃቤ ሕግ ጋዜጠኛው ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በሚሰራበት ፍትሕ መጽሔት በተለያዩ የህትመት ቀናት ” የመከላከያ ሰራዊትን ሚስጥራዊ ተግባራትን በማውጣትና እና ሀሰተኛ መረጃዎችን ማሰራጨት”በሚል ነው የከሰሰው፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ሀሳብን ከመግለጽና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ለማድረግ ከመጻፍ ባለፈ ምንም ወንጀል ፈጽሞ እንደማያውቅ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡

ከዚህ በፊት በነበረው የመንግስት ሥርዓት ታስሮ ዋስትና ተፈቅዶለት፤ ለሶስት ዓመታት ሕግን አክብሮ እየተመላለሰ ፍርድ ቤት ይቀርብ እንደነበርም ጠበቃው አቶ ሄኖክ አንስተዋል፡፡

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ደንበኛቸው በወንጀለኛ መቅጫ ስነ ስርዓት ሕግ አንቀጽ 67/ሀ እና በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 19 ንዑስ ቁጥር 6 መሰረት የዋስትና መብቱ እንዲከበርለት ጠይቀዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ከሀገር እንዲወጣ በተለያዩ አካላትና መንግስታት ሳይቀር ግፊት ቢደረግበትም ጋዜጠኛው ግን “ስራዬና ሞቴ በሀገሬ ላይ ነው” ብሎ ከሀገር ሳይወጣ መቅረቱን ጠበቃው ተናግረዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ቋሚ አድራሻ ያለውና ህግን የሚያከብር በመሆኑ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብቱን እንዲፈቅድለት ጠበቃው ጠይቀዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት ለአርብ ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል የዘገበው አል ዐይን ነው።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator