0 0
Read Time:36 Second

በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሰኔ 17/2014 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ እስከ 6 ሰዓት ድረስ የቆዬ ፍጹም ሰላማዊ የሆነ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጓል።

ሰላማዊ ሰልፉ በሶስቱም ካምፓሶች በሚገኙ ተማሪዎች እና በመምህራንም ጭምር ነው በግቢ ውስጥ የተደረገው።

ለሰልፉ እንደደራሽ ምክንያት የሆነው በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሚኖሩ አማራዎች ላይ በአሸባሪው ኦነግ ሸኔና በዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ የተፈጸመው
አሰቃቂ የዘር ፍጅት መሆኑ ተገልጧል።

በአጠቃላይ በአማራ ህዝብ ላይ ሀገር እና መሪ አልባ ተደርጎ እየተፈጸመበት ያለውን የጅምላ የዘር ማጥፋት ወንጀል በአስቸኳይ እንዲቆም ነው የተጠየቀው።

ሰልፉም በከፍተኛ ጥንቃቄ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መልኩ መከወኑን አሚማ ከመምህራንና ከተማሪዎች ያገኘው መረጃ አመልክቷል።

ከፋሲል ግቢ ተነስተው ወደ ማራኪ ካምፓስ በማቅናት በጋራ መፎክር በማሰማት የተገለጸው ይህን ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለማደናቀፍ የሞከሩ አንዳንድ የጸጥታ አካላት እንደነበሩና በኋላ ግን በመግባባት ከድርጊታቸው እንደተቆጠቡ ተገልጧል።

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Translator