0 0
Read Time:6 Minute, 20 Second

ከፍያለው

ተነስ አማራ
ምክር በጋራ

ሞኝ ከራሱ፤ ስህተት፤ብልህ ከሌላው ይማራል” ይሏልና ፤አማሮች ፤ያለ ፍትህና መቅረትን ከአርመኖች( ወደ 1 ሚሊዮን ሕእልቂት በቱርኮች) ተበትኖ መኖርን ከኩርዶችና ከፈጽሞ ጥፋት(ጆኖሳይድ ተርፎ) ማንነትን አስጠብቆ መኖርን ከእሥራኤሎች(6 ሚሊየን ህዝብ በናዚወች ካለቀባቸው) ልንማር ይገባል።
መንገዱ መዝማዛ ቢሆንም ፤”አብር ለመኖር ” የሚል ቋሚ መሪ መፈክር አንግበን መጓዝ አማራጭ አይገኝለትም።ትናንት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በማጥፋትና በተለይ አማራን ጨፍጫፊና ገዳይ የነበረው ቡድን ከስልጣን ስለተገለለና ዛሬ ፤የኢትዮጵያ ታሪክና ኢትዮጵያዊነት ስለተነበነበና ስለተሰበከከ የአማራ ችግር ተቃለለ ማለት እንዳልሆነ አማራ ለሆነ አማራ ጥርት ያለ እውነታ ነው። “አማራውን አከርካሪውን ሰብረንዋል” የሚለው በ”ነፍጠኛውን ሰብረንዋል” መቀየሩም ግልፅ ማሳያ ነው።መጠነኛ ለውጥ የታየ ቢሆንም ህዝቡ ታግሎና መስዋእትነት ከፍሎ ያገኘው ነው።የአማራው ጉዳይ “ከድጡ ወደማጡ” ለመሆኑም ፤በየግዜው የሚድረገው ፤ግድያ፤ጭፍጨፋ፤ማፈናቀልና ዝርፊያ በቂ ማስረጃ ነው። ከዚህ ቀጣዩ ምን ይሆን? ማን ነው ፣ከአመት፤10 አመታት፤ከ50 አመታት በኋላ የአማራውን ሁኔታ መተንበይ የሚችል?ት ወያኔወች ፣ አጽመ እርስታችንን ባለበት ሁኔታ፤ዛሬው ተረኛ አዲስ አበባ የኔ ናት፤ራያ የኔ ነው፤ወንበራ የኔ ነው ማለት ብቻ ሳይሆን ፤ ድፍን ሸዋ የኔ ነው፤ኢትዮጵያ የብቻየ ናት ፤ቢል እንዴት ይመከት? አማራ አጥንቱን ከስክሶና ደሙን እፍስሶ በቆያት ኢትዮጵያ መጤነህ እየተባለ በመከራ ውስጥ እስከመቼ ሊኖር ነው? የመንግሥት ስልጣንን ጠቅልሎ ይዞ፤መሳሪያ እስከአፍንጫው ታጥቆና፤የአገሪቱን አንጡራ ሀብት ጠቅልሎ ሊያዝ ይችላል። አንድ ሀቅ ግን አለ ልብን ማቸነፍ አይችልም፤ያለተሸፈ ልብ ደግሞ ከተደራጅ፤መከላከል ብቻ ሳይሆን፤አሸናፊም እንደሚሆን ጥርጥር የለውም።

የአማራ መደራጀት ራስን ለመከላከልና ሕልውናን ለማስጠበቅ እንጅ እንደሌሎች፤በሀስት ትርክት፤ክስና ፍረጃ ተነሳስቶ ሌለውን ለመጉዳትና ለመበቀል እንዳልሆነ ተደጋግሞ ተገልጧል።ስንኳንስ የአማራው ወዳጆች፤ጠላቶቹም ጠንቅቀው ያውቁታል።በኢትዮጵያ ውስጥ የተንሰራፋው ጎሳዊነትንና ቋንቋን መሰረት ፤ያደረገው፤ሥርአት በሕዝብ ጥያቄ ወይም በህግ እስታልወገደ ድረስ ፤”እሾህን በእሾህ”ነውና ብቸኛ መፍትሔው መደራጅት አሁንም መደራጅት ነው።

የአማራ አደረጃጀት ከሌሎቹ የ50ና የ60 አመታት ጉዞ እንፃር ሲታይ በተፈለገው ፍጥነት ባይጓዝም እንኳ በአጭር ግዜ የተደረሰበት ደረጃ የሚናቅ አይደለም። ይህም ነፍሳቸውን ይማርልንና በያሌ ወገኖቻችንን መስዋትነት የተገኝ ነው።
የአማራውን ትግል በሁለት ምእራፍ ከፍለን ማስቀመጥ ተገቢ ነው። በአገር ውስጥና ከአገርብውጭ።የመጀመሪውን ወሳኙን ግዳጅ እየተውጣ ላለው ፤ለባለቤቱ(ለአማራው ሕዝብ )እንተወውና ትኩረታችንን በውጭ ባለው አማራና ትውልደ አማራ እናድርግ።

ላለፍልት 27 አመታት በውጭ ያለው አማራ በግል፤ሕብረብሔራዊና አማራዊ በሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት ለወገኑ ድምጽ ሆኖ አገልግሏል። “ባጎረስኩ ተነከስኩ” ሆነ እንጅ በአገርቤት ያለው አማራ በራሱና በሌሎች ወግናቻችንን የሚሰራው ግፍ ይቁም፤ ደማቸው፤ደማችን ነው ብሎ በመነሳት፤ድምጹን ሲያሰማ በውጭ ያለው በየአገሩ ከተሞች በሙውጣት ድምሱን አስተጋብቷል። ይሁን እንጅ “አማራውን አከርካሪውን ሰብረንዋል” የሚለው ወያኔአዊ መፈክር ሳይውል ሳያድር ፤”ነፍጠኛውን ሰብረንዋል” በሚለው ኦነጋዊ መፈክር ተቀየረ፤የአማራውም፤ግፍ ቀጠለ፤ ይህ ለአማራ ዘላለማዊ ትምህርት ነው።እርግጥ ነው የአገር(አካባቢ) ክፉና የሕዝብ መጥፎ የለውም፤የመሰሪ ግለሰቦች፤ድርጅቶችና መሪወች እንጅ።የትግራይ፤የኦረሞም ሆነ ሌላው የአማራ ሕዝብ ወገን ነው፤ኢትዮጵያንም አብረው፤አቆይተዋል።ይሁንና የተነሳ የፅንፈኞች ጉልበት እያየለ በመምጣቱ፤ይህ አብሮነት አማራን ከእልቂት አላዳነውም።

። የአንድም አማራ ቢሆን በሥርአቱ አራማጆች፤በማንነቱ መዋከብ፤መዘረፈ፤መታሰረና መሞት እስካልተገታ ድረስ የመላው አማራ ህልውና አደጋ ላይ መሆኑ ታውቆ በጋራ መመከት ብቸኛው መዳኛ ነው።ይህም እንዲሳካ በውጭ ያለውን አማራ፤ትውልደ አማራና የአማራውን ወዳጆች የሚያስተባብር አለማቀፋዊ ግብረ ሀይል ወይም ምክርቤ(ሸንጎ) ማቋቋም ነው።
እንዴት ይቋቋም?
የእምነት ተቋማትን
ታዋቂነትና ተሰሚነት ያልቸውን ግለሰብ አማሮች
በየአገሩ ያሉ የአማራ ማህበራትንና ድርጅቶችን(እየተጣሩ) ያካተተ ሊሆን ይገባዋል።

ምንም እንኳ በየአገሩ የአማራ ማህበራትና ድርጅቶች ተቋቁመው እየሰሩ ቢሆንም፤ በእሁኑ ወቅት በአመዛኙ የአማራው ጉዳይ በጥቂት ማህበራዊ እንቂወች(አክቲቪስቶች) እና ግለሰቦች ዘንድ ነው ጎልቶ የሚታየው ፤የሚደገፍም ቢሆን ፤ተቋማዊ አሰራር ግን የበለጠ ውጤታማ ያደርጋል። ማህበራዊ እንቂነት ፤የዘመኑ ስልጣኔ(ቴክኖሎጂ) የፈጠረው፤ በፈጣናዊነቱ፤ተደራሺነትና ተጋሪነት ወደር ያልተገኝለት መሆኑና ለማደራጀት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደእበረከተ አይካድም ።ይሁን እንጅ በሌላ በኩል ከባህላችን፤ ስነልቦናችንና ስነምግባራች ባፈነገጠ መልኩ አሰራሩ ጉዳትም እያደረሰ ነው። የራሳችንንና መልካም የሆነውን እርግፍ አድርገን በመተው በዘመናዊ ሥልጣኔ ስም ብቻ የሌሎችን የምንከተል ከሆነ ፤ትውልድን ከፍተኛ ቀውስ ላይ መጣል ነው የሚሆነው።ነገሥታቶቻቻን አኮ ፤ለአውሮጳዊያን በውሀ የሚዘወር መሳሪያ፤ነፍጥና ሌላሌም ላኩልን እያሉ ሲጣጣፉ የነበረው፤ አባቶች፤ሞፈረ ቀንበራቸውን ሰቅለው፤ ጦርና ጋሻቸውን ፤ወርውረው ፤እናቶች እንዝርታቸውንና ደጋናቸውን ወርውረውና ወፍጮቻቸውን አቁመው አልነበረም፤የራሳቸውንም ይዘውና የውጭውንም አዋደው እንጂ።ከውጭ ዘመናዊ ትምህርት አስተማሪወች ይምጡልን ቢሉ፤አማርኛ ቅኔን ትተውና እምነታቸውንና ትተውና የያሬድን ዜማ አሽቀንጥረው አልነበረም። በመሆኑም አለም የፈለገውን ያህል ይሰልጠን፤ የሰው የስልጣኔ ቁንጮ የሆነውን የጠቢቡን አማራ(ኢትዮጵያ) መሰረት ልንለቅ አይገባም፤። አሁን በሚታየው ሁኔታ ከቀጠልንና መንገዳችንን ከሳትን ፤ ኋላ ለማቃናት የሚደረገው ድካም ሰዶ ማሳደድ ሊሆን ይችላል ፤ባህላችንንና ቋንቋችንን አጥብቀን የመያዙን ያህል ጎታችና ጎጂ የሆነውንም እናስወግድ፤ ለምሳሌ “የአበሻ ቀጠሮ”ና የመሳሰሉትን።

ደከመንና ሰለቸን ሳይሉ ግንዛቤአችንን በየግዜው እያሳደጉልን ላሉ የአማራ ማህበራዊ አንቂወቻችን (አክቲቪስቶች)ምስጋና ይድረሳቸው፤ይበርቱልንም።አማራን በጠላትነት ፈርጀው ፤ታሪኩን፤በሚያጠለሹና ባህሉን በሚያንቋሽሹት ላይ የሚያደርጉት ትግልም አጧጡፈው ይቀጥሉ። ቅድሚያ ትኩረት የሚሰጠው ግን እየተከፈላቸውም ሆነ ለግል ዝናና ክብር ሲሉ፤ከማስማማት፤ማጋጨት፤ ከማስተባበር ማናቆር አላማቸው አድርገውና በአውራጃዊነት(ጎጠኝነት) ስሜት ሰክረው ህዝባችንን የሚከፋፍሉትን ስመ አማራወች፤ የየአገሩን ሕግ ሳይሳት እርቃናቸውን ማስቀረትና ለሙላው አማራም ማንነታቸውን ማሳወቅ ፣ሊሆን ይገባል።ምክንያቱም በአማራው ላይ ከፍተኛ ውዥንብር እየፈጠሩ ነውና።

አለማቀፋዊው አማራ ግብረ ሀይል(ምክርቤት ፤ሸንጎ) ባለቤት መሆን ፤በአለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነትንና ተፅእኖ ፈጣሪነትን ያስገኛል። በየአገሩም ቅርንጫፍ ሊኖረው ይገባል።ግብረ ሀይል ይቋቋም ሲባል ፤ሁሉም ተቋማት ፤ይጨፍለቁና አንድ ይሁኑ ማለት አይደለም፤ሊሆንም አይችልም፤አግባቢና አስማሚ የሆኑ እቅዶችን አውጥቶ ፤ገንዘብና ባለሙያ መድቦ ለአንድ አማራ መስራት እንጅ።
ጠቅለል ባለመልኩ ሲታዩ ግብረ ሀይሉን ሊያከናውናቸው ከሚገባቸው ተግባሮች መካከል፤

፩. ምጣኔ ሀብታዊ ጉልበት መፍጠር

ፖለቲካዊና ማህበራዊ ነፃነት፤ያለምጣኔ ሀብታዊ ጉልበት ከንቱ ነው።
በዝህ ጉዳይ በአማራ ባለሙያወች የቀረበብ ጥናት ካለ ይቀርብና ሥራ ላይ ይዋል ወይም ተጥንቶ ይቅረብ።ዛሬ የኛ ሰው ምንአልባች ከጨረቃና ማርስ በቀር ያልደረሰበት አለም አለ?እውቀቱስ ቢሆን? ሁሉም በየግል የሚያደርገው ጥረት እንዳለ ሆኖ ፤በጋራ ጠንካራ ምጣኔሀብታዊ ተቋም ከመፍጠር የሚያግደው ለምንድን ነው?ከሎሎች የዲያስፖራ ማሕበረሰቦች(አይሁዶች፤ሕንዶች፤ሜክሲኮወች፤አይረሾች፤ግብጾች፤ባንግላዴሾች ወዘተ) ምን እንማራለን?
እርግጥ ነው ፤በሕዝባችን ላይ ችግር ደረሰ፤ሲባል፤ሁሉም በሚችለው አቅሙ የሚያደርገው መረባረብ የሚያስመሰግን ነው።ሆኖም እስታሁን በአብዛኛው የተለመደው አሰራር በጥቂት፤ፈጥኖ ደራሽ ወገኖቻችንን ተነሳሽነት እየተሰራ ያለው ነው። ።ገለሰባዊ ጥረት ወደፊትም ሊበረታታ የሚገባው ቢሆንም፤ በባለሙማወች የሚመራ፤፣ታማኝነት ተጠያቂነትና ግልጥነት ያለው ተቋም መገንባት ግን አማራጭነት የሉውም።ይህም በተራው፤

  • የሥራ እድል መፍጠር ያስችላል
    *፣ትውልደ፤አማራውን፤ የአማራውን ወዳጆች በማስተባበር፤ከድርጅቶችና መንግሥታትም ድጋፍ በመጠየቅ ፈጣን ርዳታ ለሕዝባችን ማድረስ ያስችላል፤
    *ቀጣፊወችንና ቀርጣፊወችን ያስወግዳል፤”ሊበሉት ነው”፤”ተበላ'” የሚለውን አሰልቺ ወሬ ያስወገዳል።

ለመንደርደሪያ ያህል ለአንድ ወር “የራቴን ለወገን” (የምሳየንም ሊሆን ይችላል)ብለን በትንሹ እንኳ ብንጀምር፤ከፍተኛ የሞራል መነቃቃት ፈጥራል።

፪.የተጠናከረ ቅስቀሳና የግንዛቤ ማስጨበጥ ዘመቻ

ለመሆኑ በአማራነት መደራጀት፤ለራስ መድሀኒትና ለኢትዮጵያ አንድነት መሆኑን፤ምን ያህሉ ፣በውጭ ያለ አማራ ተርድቶታል?ሌላው በህግ ተደግፎ እንዲደራጅ መፈቀድ ብቻ ሳይሆን እየተደገፈ ባለበት፤ ፤በሁኔታወች አስገዳጅነት የአመራው መደራጀት የሚያንጫጫቸው ለምንድን ነው?

እስቲ መልሱልኝ ከሆነ የሚቻል?
ከደሮና እንቁላል የትኛው ይቀድማል?
ቃልስ ያለ እስትንፋስ ከቶኑ ይኖራል?
ኢትዮጵያ ሳትኖር አማራስ ይኖራል?
አማራ አልቦ ኢትዮጵያስ ከቶ ይታሰባል?

ለአያሌ አመታት አማራው ድምጽ አልባ በመሆኑ የደረሰበት ግፍና መከራ ተዘርዝሮ አያልቅም ።የውጭው አለምም ከጥቂት ዘገባወች በቀር በሌሎች አገሮ የደረሱትን ችግሮች ያህል የአማራው ጉዳይ አልታወቀለትም? ለምን?ይህን ያህል የአማራ ምሁር እያለ እንዴት? በአሁ ወቅትስ እየደረሰ ያለውን ግፍስ አለም ማወቅ የለበትም?ወይስ እንደ አገርቤቱ ሕዝብ ለህዝብ ያነሳሳል በሚል ሰበብ ተሸፍኖ ዳግማዊ ምፅአተ አማራ እስቲፈጸም ልንጠብቅ ነው?ዛሬ ትናንት አይደለም ።ባለፉት ሁለት አመታት የአማራ የዜና አውታሮች ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ሞረሽ ወገኔ፤የአማራ ድምጽ ራዲዮ፤አሥራት ቴሌቪዥን፤አማራ ሚዲያ ማእከል፤በቅርቡ ደሞ ምንይልክ ቴሌቪዥን አሉት(የዘነጋዋችሁ ብትኖሩ ይቅርታ)። ፣በአገር ቤት ሥራቸው የሚደረግባቸው ተጽእኖ እንዳለ ሁኖ፤የእያከናወኑ ያሉት ተግባር አኩሪ ነው፤ለአብነትም ያህል የአሥራትን ሪፖርት በታገቱት ተማሪወች ጉዳይ መጥቀስ በቂ ነው። በውጭ ያለው አማራ እነዚህን ቀጥ አድርጎ መርዳት መቻል አለበት።እነሱን ሳንርዳ ዝግጅታቸውን የምንከታተል አማሮች ብንኖር ፤ራሳችንን እንደባለእዳ ልንቆጥር ይገባል። ከአንዲት ደካማ አማራ ሴት ፤ሻሂ ወይም ቡና አዝዘን ሳንከፍል እንደጠጣን ወይም ይዘን እንደበረርን እንቁጠር።እነሱም አሠራራቸውን ለሕዝብ ግልጽ ያድርጉ። እንከን ቢታይባቸው ገብተን እናስተካክላቸው፤ የ2 አመት ልጅ ቢያጠፍ ቆመጥ እናነሳለን?ግለሰቦች ሲያጠፈ ፤ተቋምን እየወቅሰን አንሽሽ።ቤት ጣራው ቢያፈስ ወይም ግድግዳው መፈራረስ ቢጀምር ይታደሳል እንጂ አይፈርስምና።ይህ ካልሆነ መገንባት ማፍረስ፤ማፍረስ መገንባት ትርፉ ኪሳራ ይሆናል።ሁሉም የዜና አውታሮች ለአማራው እስከቆሙ ድረስ፤ ቢቻል ቢቻል ፤እነሱም ተመካክረው አንዳቸው ፤የእንግሊዝኛ ጣቢያ ቢሆኑ(አብዛኛው የአለም ሕዝብ የሚግባባበት በመሆኑ) ለውጭው አለም ብዙ ማሳወቅ ይቻላል፤ካልሆነምን ተመካክረውም ቢሆን አንድ የእንግሊዝኛ ጣቢያ ማቋቋሙን ቅድሚያ ይስጡ። ።ለውጭ ሰወች ብቻ ሳይሆን ማርኛችንንም በቅጡ የማይረዳ ትውልድ እንዳለን አይዘንጋ።ሞረሽ፤አሥራት፤አማራ ሚዲያ ማከል፤ምንይልክና ሌሎችም ካሉ የአማራ መገናኛ ህዝብ(ሚዲያ) ምክርቤት ሊያቋቃቁሙ ይገባል።ይህም እየተመካከሩና እየተረዳዱ እንዲሰሩ፤ ይረዳቸዋል።አለማችን ኢኮኖሚ በኮቪድ-19 ሳቢያ እያሽቆለቆለ ሰለሆና በኑሮ ውድነት ድጋፋችን ሊቀንስ ስለሚችል ፤ሌሎች በህዝብ የሚደገፋ የመገናኛ ህዝብ(የዜና አውታር) ሊያቋቁሙ የሚያስቡ ቢኖሩ፤ ቆም ብለው ሊያስቡበት ይገባል።ከተቻለ ገንዘባቸውና የሰው ሀይላቸውን (በተለይ ጋዜጠኞችን ) ካሉት የዜና አውታሮች ጋር አቀናጅተው በመመካከር የሚሰሩበት ሁኔታ ይመቻች፤ከህዝብም ጋር ይምከሩ።

ይቀጥላል


ከፍያለው

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
50 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
50 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator