0 0
Read Time:7 Minute, 7 Second

ወንደሰን

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ ልዩ ስብሰባ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽህፈት ቤት ተካሄዷል።

በዛሬው ልዩ ስብሰባ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ የተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰጡት መልስ፡

“መንግሥት ደካማ ነው”

አሁን ያለው ጠቅላይ ሚስትሩ የሚመሩት መንግሥት ደካማ ነው የሚባለው የተሳሳተ ነው በማለት ምላሽ ሰጥተው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ “በደንብ የገረፈ ጥሩ አባት፤ ቁጫ አድርጎ የመከረ አባት እንደ አባት የማይታይበት የቆያ ብሂል አለ። ይህ ብሂል ትክክል አይደለም” ካሉ በኋላ “ኮሽ ባለ ቁጥር ሥልጣኔ ተወሰደ ብሎ የሚደናገጥ መንግሥት አይደለም” ሲሉ ስለአስተዳደራቸው ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ የጤና ባለሙያዎችና ድጋፍ ሰጪዎች ቁጥር 97 ደረሰ
ከዚያ ይልቅ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአገሪቱን ኢኮኖሚን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ጥረትንና ያገኘውን ውጤት ኢትዮጵያ ከብድር አንጻር የነበረችበት ደረጃን በመለወጥ እንዲሁም የተሰሩ ፕሮጀክቶች ውጤት ላይ የተገኘውን ውጤት በመጥቀስ የመንግሥታቸውን ጥንካሬ ከኢኮኖሚና እድገት አንጻር ምላሽ ሰጥተዋል።

ስለታገቱት ተማሪዎች ጉዳይ

ከስድስት ወራት በፊት ታግተው የደረሱበት ስላልተወቁ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በተመለከተ ጠቅላይ ሚንስትሩ በሰጡት ማብራሪያ መንግሥት ተማሪዎቹን ፈልጎ ለማግኘት ጊዜ እና ገንዘብ በማፍሰስ ሲያፈላልጋቸው መቆየቱን ጠቅሰው “ይሄ ግን ተራ እገታ” አይደለም ብለዋል።

“መረጃ በደሰረን ቁጥር እየፈለግን ነው። አሁንም ተማሪዎቹን ካሉበት ለማግኘት የሚገኙ መረጃዎችን መሰረት አድርገን ፍለጋችንን ቀጥለናል” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ “እኛም ሴት ልጆች አሉን፤ ይሰማናል ይሁን እንጂ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚጽፉ ነገሮች” እንዳሉ አመልክተው መንግሥት ግን አሁንም ፍለጋ ላይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ትግራይን በሚመለከት

“አንድ ሰው ወይም ሁለት ሰው ሲወቀስ ጉዳዩን ወደ ትግራይ አንወስደው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “በህውሓት እና በብልጽግና መካከል ረብ የሌላቸው ንግግሮች አሉ ይሄን መተው አለብን።”

ጨምረውም “ለውጡ ከመጣ በኋላ የትግራይ ሕዝብ እንዳይጠቀም ተደርጓል የሚለው የተሳሳተ አመለካከት ነው” ብለው ጠቅላይ ሚንስትሩ “ባለፉት ሁለት ዓመታት እንኳ የትግራይ ክልል በጀት በ42 በመቶ አድጓል። በጀቱ ምን ያህል የሚፈለገው ቦታ ላይ ውሏል የሚለውን ግን የክልሉ ምክር ቤት ነው የሚገመግመው” ብለዋል።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለምን ተስፋፋ?
ትግራይን ሕዝብ ለመጉዳት ፍላጎት የለንም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ “ኮሮናቫይረስ ለመላከል 46 ሚሊዮን ብር ከበጀት ውጪ በጥሬ ገንዘብ እና በቁሳቀሱ ተረድቷል፤ ይሁን እንጂ ለኮሮናቫይረስ ለትግራይ ክልል ድጋፍ አልተደረገም የሚሉ አሉ። ማዳበሪያ ለገበሬው እንዳይቀር 445 ሚሊዮን ብር ተበድረን ለሌሎች ክልል ያልተደረገውን ማዳበሪያ ልከናል” ብለዋ ጠቅላይ ሚንሰትሩ።

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በትግራይ ውስጥ እየተካሄዱ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት በትግራይ ላይ በደል ይፈጽማል መባሉ ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል።

በሱዳን ድንበር ላይ ስላለ ጉዳይ

“ከሱዳን ጋር ወድማማች ሕዝቦች ነን” ያሉት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ሕዝብ ብዙ ችግሮችን አብረው አልፈዋል። ከሱዳን ጋር ጦርነት አንሻም ግን “ሱዳን እና ኢትዮጵያን ለማዋጋት የሚፈልግ ኃይል የለም ማለት ግን አይቻልም” ብለዋል።

ከሳምንታት በፊት በድንበር አካባቢ ተከሰተ ስለተባለው ችግርም ሁለቱ አገራት በሰላም ይፈቱታል በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ሰጥተዋል።

የ አምነስቲ ሪፖርት

“የኢትዮጵያውያን መብት እየተጎዳ ነው ካለ ሪፖርቱ ፤ አይረባም ሳይሆን፤ የእኛም የጸዳ ተቋም ስላልሆነ ችግር ሊከሰት ይቻላል። እሱን ፈትሾ ማስተካከል ያስፈልጋል” በማለት ከሪፖርቱ ጋር የተለያዩ አላማዎች ቢኖሩም የሚስተካከለውን ለማረም ፈቃደኝነቱ እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

“ካጠፋን መሸፈን አያስፈልግም፤ ስለዚህ መለስ ብሎ ለመፈተሽ ብዙ የሚያስጨንቀን ጉዳይ ግን አይደለም” ብለዋል።

ሕዳሴ ግድበ

ስድስት ዓመት በዘገየው ግድብ 6 ቢሊዮን ዶላር ኢትዮጵያ ማጣቷን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ ስምንት ኮንትራት 6 ተቋራጮች እንደሚሰሩት በማስታወስ አንዱ ተቋራጭ ከሥራ ቢዘገይ ለሌላው ተቋራጭ እንቅፋት እንደሚሆን አስታውሰዋል።

ሥራ ሲሰራ ዲፕሎማሲው ይጠነክራል። ሥራ ሳይሰራ ሲቀር ዲፕሎማሲውም ቀላል ይሆናል።

የሕዳሴ ፕሮጀክት ከጥንስሱ ጀምሮ የተወሰኑ ውሳኔዎችን ማጥናታቸውን እና በግድቡ ላይ ሜቴክ እንዲገባ መደረጉ ስህተት መሆኑን ተረድተናል ብለዋል ጠቅላይ ሚንሰትሩ።

“በጣም እርግጠኛ ሆነን ያወጣነው ሪፖርት ነው” አምነስቲ ኢንተርናሽናል
ጠቅላይ ሚንስትሩ የኤልክትሮ መካኒካል ሥራዎቹ እንደ አዲስ እንዲሰራ መደረጉን ተናግረዋል። በመጪው ክረምት ግድቡ 4.9 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዝ እንደሚቻል ተናግረዋል።

ከለውጡ በኋላ ፕሮጅክቱ እንዴት እንደዳነ፤ “የምክር ቤት አባላት ሄዳችሁ ማየት ትችላላችሁ” ብለዋል ጠቅላይ ሚንሰትሩ።

ዲፕሎማሲን በተመለከተ፤ የግብጽ የተሻለ የኤሌእከትሪክ እና የንጹሕ ውሃ አቅርቦት ለዜጎቿ ማቅረብ እንደምትችል ያስታወሱ ሲሆን፤ ኢትዮጵያም ይህን ከማድረግ የሚከለክላትን አገር አትቀበልም ብለዋል።

“እጅግ የሚያኮሩ ኢትዮጵያዊያን” ያሏቸው ግለሰቦች አሁንም የሕዳሴ ገድብ ጉዳይ እየተደራደሩ እንደሚገኙ አስታውሰዋል።

ምርጫ

ምርጫ ቦርድ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ምርጫ ማድረግ አልችልም የሚለው ሪፖርት ሲደርሰኝ፤ “ከወ/ሪት ብርቱኳን ጋር ባልተለመደ መልኩ ጠንከር ያለ ንግግር አድርገናል” በማለት ከምርጫ ቦርድ ውሳኔ ጋር ተስማምተው እንዳልነበረ ተናግረዋል።

ፓርቲያቸው ምርጫው እንዲካሄድ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበረው የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንሰትር፤ “ብልጽግና ምርጫ የሚያስፈረው ፓርቲ እንዳለሆነ ለሁሉም ግልጽ ነው” ብለዋል።

ወ/ሪት ብርቱኳን፤ “እስካሁን ከነበረው በማንም መስፈርት የማያሳፍር ምርጫ ለማካሄድ ነው ኃላፊነት የተቀበልኩት። ከዚህ ውጪ የሆነ ምርጫ ይደረገረ የሚሉ ከሆነ ሥራዬን እለቃለሁ። ምርጫ እንዲደረግ አታዙኝም ብለው ስልኩ ተዘጋ” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተናግረዋል።

ደቡብ ሱዳን በግዛቷ ግብጽ የጦር ሰፈር እንድታቋቁም ፈቅዳለች?
ጠቅላይ ሚንስትሩ ምርጫ መካሄድ የማይቻልበት ሁኔታ መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የመንግሥትን የሥራ ዘመን በማራዘም ምርጫ ማካሄድ የሚቻልበትን አራት ሕገ-ምንግሥታዊ አማራጮች መቅረባቸውን አስታውሰዋል።

እምቦጭ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ ሐይቁ በአካል ሄደው አረሙ ያለበትን ሁኔታ መመልከታቸውን አስታወሰው፤ አምቦጭ ሁለት አይነት መከላከያ መንግድ አለው ብለዋል።

ይህም በሰው እና በማሽን በመጠቀም በጊዜያዊ መከላከል መሆኑን ጠቁመው፤ መሠረታዊው መከላከያ ግን የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ነው።

ከጉና ተራራ ስራ የሚነሱ ተፋሰሶች ጣናን የሚመግቡ መሆኑን ያስታወሱት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ በሰው ልጆች ምክንያት እየተራቆተ መሆኑን አስረድተዋል። የተራራው መራቆት ለአካባቢው ሰው በጎርፍ መጥለቅለቅ እና የጣና ሐይቅ አምቦጭ መወረር ምክንያት ነው ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው ማሽን ብዙ ውጤታማ እንደልነበረ እና 200 ሚሊዮን የሚፈጅ የተሻለ ማሽን ለመግዛት ጥረት እየተደረገ ነው።

በቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን በተመለከተ

ቻይና በኮሮናቫይረስ ክፉኛ ተጠቅታ በነበረችበት ወቅት፤ በአገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከቻይና ይውጡ የሚሉ አስተያየቶች እና እንቅስቃሴዎች እንደነበሩ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፤ ነገር ግን “መሰል አስተያየቶች ሙሉ መልከታ ያልነበራቸው ነበሩ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት በቻይና የሚገኘ አንድም ኢትዮጵያዊ ተማሪ በቫይረሱ አልተያዘም። ከቻይና ፕሬዝደንት ጋር መነጋገራቸውን እና ተማሪዎቹ ለከፋ ችግር ሳይጋለጡ ማለፋቸውን ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ ለተማሪዎቹ ገንዘብ ተልኮ እንድነበረ እና የቻይና መንግሥት ለተማሪዎቹ ላደረገው እንክብካቤ ምስጋና ይገባዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድን በተመለከተ

ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨመረው እንዳሉት የቫይረሱ ስርጭት በቫይና ተስፋፍቶ በነበረበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና መብረር የለበትም የሚለው ትችት ትክክል እንዳልነበረ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ እንዳሉት፤ አየር መንገዱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለከፍተኛ ወጪ ቢዳረግም አንድም ሠራተኛ ሳይቀንስ ከመንግሥት ድጎማ ሳይጠይቅ ሥራውን እያስቀጠለ ይገኛል።

በተጨማሪም አምስት የአየር መንገዱ ሠራተኞች ባቫይረሱ ተይዘው እንደነበረ አስታውሰው ሁሉም ማገገማቸውን ተናግረዋል።

በምዕራብ ትግራይ በመሬት ካሳ ጉዳይ ለተቃውሞ የወጡ ’45 ሰዎች ታሰሩ’
“የውጪ አገር መሪዎች ከእኔ ጋር በስልክ ሲነጋገሩ ቅድሚያ የሚያመሰግኑት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ “አስተዳደሩ እና ሠራተኞቹ ምስጋና ይገባቸዋል” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨምረውም “ቻይና ለአየር መንገዱ በሳምንት 90 በረራን እንዲያደርግም ፈቅዳለች” ያሉ ሲሆን፤ ይህም የሆነው “በችግር ጊዜ ረድቶኛል [አየር መንገዱ] ብላ ነው ይህን ያደረገችው” ብለዋል።

ችግኝ

አምስት ሚሊዮን ችግኝ መትከል የምንችል ከሆነ ምርጫ ማካሄድ እንዴት ይሰነናል የሚል “ውሃ የማይቋጥር” ሐሳብ የሚያነሱ አሉ ብለዋል ጠቅላይ ሚንሰትሩ።

ምርጫን የሚያስፈጽሙ 100 ሺህ ሰዎች ማሰልጠን ስለማይቻል እንጂ፤ ድምጽ ሄዶ ለመስጠት ስለማይቻል አይደልም ምርጫው የተራዘመው ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ።

“ግለሰቦች ርቀት ጠብቀው ድምጽ ሊሰጡ ይቻላሉ ግን ለምርጫ ዝግጅት ማድረግ አይቻልም” ያሉት ጠቅላይ ሚንሰትሩ፤ ከ5 ቢሊዮን በላይ ዝግጁ የተደረጉ ችግኞችን ግን በ90 ቀናት መትከል ከባድ እንደማይሆን ጠቅሰዋል።

ኮሮናቫይረስና በድንበር አካባቢ ያለው እንቅስቃሴ

ከአዋሳኝ ጎረቤት አገራት በአፋር፣ በአማራ ክልል መተማ እና ሶማሌ ክልል በኩል የሚገቡ ሰዎች በአከባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የጤና ስጋት ደቅነዋል። መንግሥት ይህን ለመቅረፍ ምን አስቧል ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ “ኮሮናቫይረስ 213 በላይ አገራት ያጠቃ እና ትልቅ ትንሹን ያነጋገረ፤ የ21ኛ ክፍለ ዘመን ቴክኖሎጂ ሊመክተው ያልቻለ ክስተት ነው” በማለት ጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ምንም እንኳ በሁሉም ክልሎች አና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቢኖሩም፤ ቫይረሱ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳትን የመናቅ እና የመዘናጋት ሁኔታ ይታያል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በስፓኒሽ ፍሉ ምክንያት ከ500 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ማጥቃቱን እና ወረርሽኙ በሦስት ዙር መከስቱን አስታውሰው፤ ከመጀመሪያው ይልቅ በሁለተኛው ዙር የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ የገደለው ሰው ቁጥር የላቀ እንደነበረ በማስታወስ፤ ኮሮናቫይረስም በሁለተኛው ዙር ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል በማስጠንቀቅ ካለፈው ትምህርት ወስዶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

እያደጉ ባሉ አገራት የሚደርሰው ኢኮኖሚያዊ ጫና ከአደጉ አገራት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ እያደጉ ባሉ አገራት ላይ ከሚደርሰው ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመውጣት ግን ረዥም ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረዋል።

እንደ ተቀሩት አገራት ሁሉ የኢትዮጵያ የጤና ሥርዓትም በቫይረሱ መፈተኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ቫይረሱን ከተከሰተ ወዲህ ኮሮናቫይረስን የመመርምር 31 ላብራቶሪዎችን በማቋቋም በቀን 8ሺህ ሰው ናሙና መውሰድ የሚያስችል ደረጃ ላይ ኢትዮጵያ መድረሷን ተናግሯል።

በመጪው ሐምሌ ወር ላይም በቀን ከ14 ሺህ ሰዎች ናሙና በመወሰድ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ የሚቻልበት አቅም ላይ እንደሚደረስ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ጨምረው እንደተናገሩት በአጭር ጊዜ ውስጥ መንግሥታቸው፤ በቫይረሱ የተያዙ 15 ሺህ ሰዎች ማከም የሚያስችል የጤና ሥርዓት መዘጋጀቱን፣ የቫይረሱ ምልክት የሚያሳዩ 30ሺህ ሰዎች ለይቶ ማቆያ እና ከውጪ ለሚመጡ 45 ሺህ ለይቶ ማቆያ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ክልሎችን እና የከተማ አስተዳደሮች በላብራቶሪ ማቋቋም እና የቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።

“ኮሮናን በተመለከተ መንግሥት ከሕዝብ የደረቀው አንዳቸው ነገር የለም። ሁሉም መረጃ ለህዝብ በግልጽ ይነገር የሚል አቋም ይዘን ሁሉንም እየተናገርን ነው” በማለት መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት የተመለከተ መረጃ እያቀበ አይደለም የሚባል ስህተት መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢኮኖሚ

ጠቅላይ ሚንስትር በቫይረሱ ስርጭት ምክንያት የ170 አገራት ኢኮኖሚ የእድገት መጠን ከዜሮ በታች እንደሚሆን የዓለም የገንዘብ ተቀወም (አይኤምኤፍን) በመጥቀስ ተናግተዋል። የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት 9 በመቶ ይሆናል ተብሎ የተጠበቀ ቢሆንም እድገታችን እስከ 6 በመቶ ይሆናል። አይኤምኤፍ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 3 በመቶ ያድጋል ሲል ተንበየዋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የዓለም ኢኮኖሚ እድገት ከዜሮ በታች ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አድገት አዎንታዊ የሆነበትን ምክንያት ሲያስረዱ፤

የበጀት ዓመት ሐምሌ መጀመሩ፣ የተለየ የጊዜ አቆጣጠር በኢትዮጵያ መኖሩ፣ ከኮረናቫይረስ በፊት ኢትዮጵያ ወደ ውጪ ትልከው የነበረው ምርት እድገት እያሳየ እንደነበር የጠቀሱት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ የኢትዮጵያ የንግድ ሥርዓት ከተቀረው ዓለም ጋር የተሳሰረው ከ30 በመቶ በታች ነው ብለዋል። ይህም በመላው ዓለም ላይ የሚደርሰው ጫና ከፍተኛ ላይሆን እንደሚችል ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቁመዋል።
(ምንጭ:- ቢቢሲ )

About Post Author

Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

By Admin

Amhara elites must be militant democrat to stop anti democratic fascism act on our people by those extremist nationalists(TPLF ,OLF), and also name covered prosperity,EPRDF. ትንሳኤ አማራ በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል።

Translator